Friday, September 29, 2023

ርዕሰ አንቀጽ

የመላው ሕዝባችን የአብሮነት ፀጋዎች ይከበሩ!

ሕዝበ ሙስሊሙና ሕዝበ ክርስቲያኑ የመውሊድ፣ የደመራና የመስቀል በዓላትን እያከበሩ ነው፡፡ በኢትዮጵያ አገረ መንግሥት ግንባታ ውስጥ እኩልና ጉልህ ድርሻ ያላቸው ኢትዮጵያውያን፣ በዓላቱን እንደ እምነታቸው ሕግጋት...

በአገር ጉዳይ የሚያስቆጩ ነገሮች እየበዙ ነው!

በአሁኑም ሆነ በመጪው ትውልድ ዕጣ ፈንታ ላይ እየደረሱ ያሉ ጥፋቶች በፍጥነት ካልታረሙ፣ የአገር ህልውና እጅግ አደገኛ ቅርቃር ውስጥ ይገባና መውጫው ከሚታሰበው በላይ ከባድ መሆኑ...

የትምህርት ጥራት የሚረጋገጠው የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ሲወገድ ነው!

ወጣቶቻችን የክረምቱን ወቅት በእረፍት፣ በማጠናከሪያ ትምህርት፣ በበጎ ፈቃድ ሰብዓዊ አገልግሎትና በልዩ ልዩ ክንውኖች አሳልፈው ወደ ትምህርት ገበታቸው እየተመለሱ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ሰኞ መስከረም...
- Advertisement -
- Advertisement -

የዋጋ ንረቱ በጥናት ላይ የተመሠረተ ልጓም ይበጅለት!

ከዚህ ቀደም በኮሮና ወረርሽኝ፣ በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች፣ በሰሜን ኢትዮጵያ አውዳሚ ጦርነት፣ አሁን ደግሞ በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ግጭት ሳቢያ የምግብና የምግብ ነክ ምርቶች፣ የግንባታ ዕቃዎችና ሌሎች ሸቀጣ ሸቀጦች ዋጋ በየቀኑ ወደ ላይ እያሻቀበ ነው፡፡ ከቅርብ ቀናት ወዲህ ደግሞ በጤፍና በሌሎች የምግብ ምርቶች ላይ እየታየ ያለው አስደንጋጭ የዋጋ ንረት መግቻ ካልተደረገለት፣ የዜጎች ሕይወት ከድጡ ወደ ማጡ እየሆነ ሰብዓዊ ጉዳት...

ሕዝብና አገርን ሰላም ከመንሳት መቆጠብ ይገባል!

በተለያዩ ጎራዎች የተሠለፉ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ሕዝብና አገር ሰላም መንሳት ማቆም አለባቸው፡፡ ሥልጣን ላይ ያላችሁም ሆናችሁ ለሥልጣን የምትፋለሙ በሙሉ መጀመሪያ ለራሳችሁ ሰላም ስጡ፡፡ ራሳቸው ሰላም ሳይኖራቸው ለሕዝብም ሆነ ለአገር ሰላም ማምጣት እንደማይችሉ ይገንዘቡ፡፡ ስለዚህም ከዚህ በፊት የነበሩትንም ሆነ በዚህ ዘመን የተቀፈቀፉ ችግሮችን በቅደም ተከተል ለማቃለል፣ ተቀምጦ ለመነጋገር የሚያስችል ቁመና ይኑራቸው፡፡ ልዩነትን በሠለነጠነ መንገድ የመፍታት ልማድና ወግ ሳያዳብሩ፣ ስለዴሞክራሲም ሆነ ስለሰብዓዊ...

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም ግልጽነት ይላበስ!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ያወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ ነሐሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ16 ተቃውሞ፣ በ12 ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈጻጸም ለመከታተልና ለመቆጣጠርም መርማሪ ቦርድ በምክር ቤቱ ተሰይሟል፡፡ አዋጁ በአገሪቱ ሕግ አውጭ አካል ፀድቆ ወደ ሥራ ሲገባ ሊታሰብባቸው ከሚገቡ ጉዳዮች መካከል አንዱ፣ በማናቸውም ሁኔታ ውስጥ የማይገደቡ መብቶችን...

ዘለቄታዊ ሰላም የሚሰፍነው በንግግርና በድርድር ብቻ ነው!

አገራዊ የምክክር ኮሚሽን በቅርቡ ባወጣው መግለጫ በተለያዩ አካባቢዎች የሚካሄዱ ግጭቶች ተልዕኮውን ለማከናወን መሰናክል እንደሆኑበት ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ ለአገር ዘለቄታዊ ሰላም ተስፋ ይፈነጥቃል ተብሎ የሚጠበቀው ብሔራዊ የምክክር ሒደት ሲደናቀፍ፣ መጪው ጊዜ ብሩህ ይሆናል ብሎ መጠበቅ በፍፁም አይቻልም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሐሳብ ልዩነቶችንና አለመግባባቶችን በንግግርና በምክክር መፍታት ሲገባ፣ በተለያዩ አካባቢዎችና በተለያዩ ወገኖች እየተወሰዱ ያሉ የኃይል ዕርምጃዎች የአገርን ህልውና እየተፈታተኑ መሆናቸውን ኮሚሽኑ በከፍተኛ...

የሕዝብ ሰላምና ደኅንነት ጉዳይ ይታሰብበት!

አገር ሰላም አጥታ ከግጭት ወደ ግጭት ስትሸጋገር ሁሌም የሚጎዳው ሕዝብ ነው፡፡ በተለይ በቀላሉ ተጋላጭ የሚሆኑት ግጭት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ናቸው፡፡ ከዚህ ቀደም በትግራይ፣ በአማራ፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በደቡብ፣ በሲዳማና በሶማሌ ክልሎች በተፈጸሙ ጥቃቶችም ሆነ በተከናወኑ ግጭቶች የተጎዱት ንፁኃን ናቸው፡፡ በግጭትም ሆነ በጥቃት ጊዜ ከማንም በላይ ተጋላጭ የሚሆኑት ነፍሰ ጡሮች፣ አጥቢ እናቶች፣ ሕፃናት፣ አዛውንቶችና አቅመ ደካሞች...

ከትናንት ስህተቶች አለመማር ከባድ ዋጋ እያስከፈለ ነው!

በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ብዙዎችን ከሚያግባቡ ጉዳዮች መካከል አንዱ፣ ከትናንት ስህተቶች ለመማር አለመፈለግ ሊያስከትል የሚችለው ጦስ ነው፡፡ ብዙዎች እንደሚስማሙበት ትናንት የተፈጸሙ ስህተቶች ኢትዮጵያን ከማሽመድመድ አልፈው፣ ለዘመናት ቁስሉ የማይሽር ደዌ ተክለውባት አልፈዋል፡፡ የዚህ ዘመን ትውልድ የራሱ ተግዳሮቶች ሳይበቁት፣ ከትናንት በተላለፉ የታሪክ ዝንፈቶችና ትርክቶች ምክንያት ከባድ ዋጋ እየከፈለ ነው፡፡ በዚህ የሠለጠነ ዘመን የቀድሞ ስህተቶችን በማረም በልማትና በዕድገት ወደፊት መራመድ የሚገባት...

ከግጭት አዙሪት ውስጥ መውጣት ያስፈልጋል!

ኢትዮጵያ አሁንም ከፖለቲካ ውጥረት መገላገል አልቻለችም፡፡ የፖለቲካ ውጥረቱ ኢኮኖሚውን እያኮማተረው ነው፡፡ ኢኮኖሚው ሲኮማተር የምግብ፣ የአልባሳት፣ የመጠለያ፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ እንዲሁም የሌሎች ሸቀጦችና አገልግሎቶች አቅርቦት እጥረት ይባባሳል፡፡ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በጋምቤላና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በየቀኑ ግጭቶች ይስተዋላሉ፡፡ ኢትዮጵያን ካደቀቀው የሰሜኑ አውዳሚ ጦርነት በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሠረት አንፃራዊ ዕፎይታ ቢገኝም፣ አሁንም ከግጭት አዙሪት ውስጥ መውጣት ባለመቻሉ ንፁኃን እየተገደሉ የአገር አንጡራ ሀብት እየወደመ...

ከረሃብ ጋር የተፋጠጡ ወገኖችን ለመታደግ ቅድሚያ ይሰጥ!

ለበርካታ ሚሊዮኖች በቀን አንዴ ምግብ ማግኘት ከፍተኛ ችግር እየሆነ ነው፡፡ በግጭቶች፣ በድርቅ፣ እንዲሁም በተለያዩ ሰው ሠራሽ ችግሮች ሳቢያ ለምግብ እጥረት የተጋለጡ ወገኖች ለከባድ መከራ ተዳርገዋል፡፡ በመኖሪያ ቀዬአቸው ውስጥ የሚኖሩም ሆኑ ተፈናቅለው በየመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ 30 ሚሊዮን ያህል ወገኖች የዕለት ደራሽ ዕርዳታ ቢጠባበቁም፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የዓለም ምግብ ፕሮግራምና የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት በዘረፋ ምክንያት ዕርዳታ በማቆማቸው...

ማህበራዊ ሚዲያዎች

167,329FansLike
274,262FollowersFollow
13,700SubscribersSubscribe
- Advertisement -

ትኩስ ዜናዎች ለማግኘት

ትኩስ ዜናዎች

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...

ማን በማን ላይ ተስፋ ይኑረው?

በአንድነት ኃይሉ ችግሮቻችንን ለይተን ካወቅን መፍትሔውንና ተስፋ የምናደርግበትን ማወቅ እንችላለን፡፡...