Thursday, December 7, 2023

ርዕሰ አንቀጽ

ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማት የደንብ ልብስ አለባበስ የጌጣጌጥና መዋቢያ አጠቃቀም ደንብን ማውጣት ለምን አስፈለገ?

በዳንኤል ንጉሤ በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ባለሙያዎች የደንብ ልብስ አለባበስ፣ የጌጣጌጥ አጠቃቀም የገጽታና የውበት አጠባበቅን አስመልክቶ በተዘጋጀው ረቂቅ ደንብ ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡ ረቂቅ ደንቡን ያዘጋጀው...

ትኩረት ለሕዝብና ለአገር ደኅንነት!

ኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በቅርብ ርቀት ባሉ አገሮች፣ እንዲሁም ራቅ ባሉ የአፍሪካና የዓለም አገሮች ውስጥ የሚስተዋሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮች የተፅዕኖ አድማሳቸው እየሰፋ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ሌላው...

የአስተሳሰብና የአስተዳደር ዘይቤ ለውጥ ያስፈልጋል!

ኢትዮጵያ ውስጥ ሕዝቡን በጋራ አስተሳስረው የሚያኖሩ በጣም በርካታ ማኅበራዊ እሴቶች አሉ፡፡ እነዚህ ለዘመናት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሸጋገሩ የኖሩ እሴቶች አገር ለማቆም ትልቅ አስተዋፅኦ ነበራቸው፣...
- Advertisement -
- Advertisement -

ግጭቶች በሙሉ ሁሉን አሳታፊ መፍትሔ ይፈለግላቸው!

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተገቶ የተስፋ ጭላንጭል መታየት ሲጀምር፣ በአማራ ክልል ሌላ ዙር ዕልቂትና ውድመት ሊያደርስ የሚችል ግጭት መነሳቱ ብዙዎችን ያሳስባቸዋል፡፡ በአማራ ክልል የቀጠለውና ወራት ያስከተለው ግጭት ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት እያስከተለ ሲሆን፣ በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ያለው ሁኔታም ከፍተኛ ሥጋት ያጠላበት ነው፡፡ እንደ ልብ ተንቀሳቅሶ መሥራትም ሆነ መዘዋወር በማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ ያለችው ኢትዮጵያ፣ በኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፉ...

የባለሥልጣናትና የባለሀብቶች ግንኙነት ሥርዓት ይኑረው!

በሕዝብ ድምፅ ሥልጣን የያዘ ፓርቲ የሚመሠርተው መንግሥት ከምንም ነገር በፊት ለሕግና ለሥርዓት መከበር ኃላፊነት ሊኖረው ይገባል፡፡ ይህንን ኃላፊነት በሚገባ ሊወጣ የሚችለው ሥራውን በግልጽነትና በተጠያቂነት መርህ ሲያከናውን ነው፡፡ የመንግሥት አሠራር በግልጽነትና በተጠያቂነት መርህ ሲመራ በሥልጣን መባለግም ሆነ፣ ለሕገወጥነት የሚገፋፉ ድርጊቶች በሙሉ ይመክናሉ፡፡ በቅርቡ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ያከናወነው ገዥው የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ የአመራሩ ዲሲፕሊን መሻሻል ማሳየቱንና የመፈጸምና የማስፈጸም አቅሙም...

የመላው ሕዝባችን የአብሮነት ፀጋዎች ይከበሩ!

ሕዝበ ሙስሊሙና ሕዝበ ክርስቲያኑ የመውሊድ፣ የደመራና የመስቀል በዓላትን እያከበሩ ነው፡፡ በኢትዮጵያ አገረ መንግሥት ግንባታ ውስጥ እኩልና ጉልህ ድርሻ ያላቸው ኢትዮጵያውያን፣ በዓላቱን እንደ እምነታቸው ሕግጋት መሠረት በፍቅርና በመተሳሰብ መንፈስ ሲያከብሩ ለኢትዮጵያ እንደ ትልቅ በረከት ይቆጠራል፡፡ አዲሱ ዓመት ከባተ ወዲህ በተለያዩ አካባቢዎች የዘመን መለወጫ በዓላት በታላቅ ድምቀት እየተከበሩ ነው፡፡ በተለይ በደቡብ አካባቢዎች እየተከበሩ ያሉት የዘመን መለወጫ በዓላት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን፣ የምግብ፣...

በአገር ጉዳይ የሚያስቆጩ ነገሮች እየበዙ ነው!

በአሁኑም ሆነ በመጪው ትውልድ ዕጣ ፈንታ ላይ እየደረሱ ያሉ ጥፋቶች በፍጥነት ካልታረሙ፣ የአገር ህልውና እጅግ አደገኛ ቅርቃር ውስጥ ይገባና መውጫው ከሚታሰበው በላይ ከባድ መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡ የአገር ጉዳይ ያገባናል የምትሉ ምሁራንና ልሂቃን አገር አንዴ ካመለጠች እንደማትገኝ አውቃችሁ፣ በከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜትና ኃላፊነት የሚጠበቅባችሁን ተወጡ፡፡ ኃላፊነታችሁን በአግባቡ መወጣት አቅቷችሁ ችግሮች ተባብሰው አገር ካመለጠች፣ በመጪው ትውልድና በታሪክ የሚያስጠይቅ ወንጀል እንደ ሠራችሁ...

የትምህርት ጥራት የሚረጋገጠው የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ሲወገድ ነው!

ወጣቶቻችን የክረምቱን ወቅት በእረፍት፣ በማጠናከሪያ ትምህርት፣ በበጎ ፈቃድ ሰብዓዊ አገልግሎትና በልዩ ልዩ ክንውኖች አሳልፈው ወደ ትምህርት ገበታቸው እየተመለሱ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ሰኞ መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ.ም. የትምህርት ዓመቱ ሲጀመር፣ በሌሎች አካባቢዎችም ተማሪዎች ሰሞኑን የትምህርት ገበታቸው ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከመደበኛ ትምህርት በተጨማሪ በምሽትና በርቀት የሚከናወኑ ትምህርቶችም ይጀመራሉ፡፡ ዘንድሮ ለተማሪዎች የግብረ ገብነት ትምህርት መስጠት እንደሚጀመር ተሰምቷል፡፡ ይህ በእጅጉ...

ዘመኑን የሚመጥን ሐሳብና ተግባር ላይ ይተኮር!

ኢትዮጵያ በአዲሱ ዓመት ዋዜማ ሁለት ታላላቅ ክስተቶች ተስተናግደውባት ነበር፡፡ አንደኛው የታላቁ ህዳሴ ግድብ አራተኛ የውኃ ሙሌት ሲሆን፣ ሁለተኛው ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ከተማ ያስጀመረው ፈጣኑ የ5ጂ ኢንተርኔት አገልግሎት ነው፡፡ በታላቅ ጉጉት ይጠበቅ የነበረው የኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ፕሮጀክት የሆነው የታላቁ ህዳሴ ግድብ አራተኛ የውኃ ሙሌት መሳካቱ፣ እንዲሁም ኢትዮጵያን ከዓለም ቀዳሚ አገሮች አንዷ የሚያደርጋት ፈጣኑ የ5ጂ አገልግሎት ዕውን መሆን መጀመር አዲሱን ዓመት...

ለሕዝብና ለአገር ክብር የማይመጥኑ ድርጊቶች ገለል ይደረጉ!

የአዲሱ ዓመት ጉዞ በቀናት ዕርምጃ ሲጀመር የሕዝብና የአገር ጉዳይን በየቀኑ ማስታወስ ግድ ይላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም፣ ዴሞክራሲ፣ ልማትና ዕድገት ያስፈልጋሉ ከሚባሉ ግብዓቶች ውስጥ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱት የመንግሥት አገርን በብቃት የመምራት አቅምና የሕዝብ እርካታ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለቱ ባልተጣጣሙበት ኩርፊያ፣ ግጭት፣ ሕገወጥነትና ሥርዓተ አልበኝነት ይነግሣሉ፡፡ ኢትዮጵያ ያለችበት ተጨባጭ ሁኔታ ሲቃኝ ደግሞ የተለያዩ ማንነቶች፣ ባህሎች፣ ቋንቋዎች፣ እምነቶች፣ የፖለቲካ አመለካከቶችና የመሳሰሉት...

በአዲሱ ዓመት ለሰላምና ለአብሮነት ቁርጠኝነት ይታይ!

ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መልካም አዲስ ዓመት እንዲሆን፣ እንዲሁም ሁሉም ዜጎች በየተሰማሩበት መስክ ፍሬያማ ውጤት እንዲያገኙ ከወዲሁ መልካም ምኞታችንን እንገልጻለን፡፡ አሮጌው ዓመት አልፎ ለአዲሱ ዓመት አቀባበል ሲደረግለት ብሩህ ተስፋ መሰነቅም ሆነ በመነቃቃት ስሜት መነሳት፣ ከወዳጅ ዘመድ ጋር በዓልን በደስታ ማሳለፍ፣ የተቸገሩ ወገኖችን ባለ አቅም ማገዝ፣ ለአገር መልካም የሆኑ ነገሮችን መመኘት፣ መተሳሰብና አንድነትን ማሳየት የኢትዮጵያውያን ዘመን ተሻጋሪ የአብሮነት መገለጫ እሴት ነው፡፡...

ማህበራዊ ሚዲያዎች

167,329FansLike
276,491FollowersFollow
13,800SubscribersSubscribe
- Advertisement -

ትኩስ ዜናዎች ለማግኘት

ትኩስ ዜናዎች

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...

ኦሮሚያ ኢንሹራንስ በግሉ ኢንሹራንስ ዘርፍ ሁለተኛውን የገበያ ድርሻ ለመያዝ ያስቻለውን ውጤት ማስመዝገቡን ገለጸ

ኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ የባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት፣ የመለዋወጫ ዕቃዎች...