ከ20 ዓመታት ቆይታ በኋላ እንደ አዲስ የተጀመረውን የኢትዮ ኤርትራ ግንኙነት በማስመልከት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመርያዎቹን የአስመራ ተጓዦች ሐምሌ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. አሳፍሮ ኤርትራ አድርሷል፡፡ ጉብኝት ከተደረገባቸው መካከል የአስመራ ከተማ ሃይማኖታዊ ተቋማት፣ ጥንታዊ መስህቦች፣ የምፅዋ ባህር ዳርቻዎች፣ የዶጋሊ ጦርነት መታሰቢያ ሐውልትና ሌሎችም የመዝናኛ ሥፍራዎች ይገኙበታል፡፡ ፎቶዎቹ ከፊል ገጽታውን ያሳያሉ፡፡