Skip to main content
x

ዜና

ዶ/ር መረራ ጉዲና በኢትዮጵያ አዲስ የዴሞክራሲ ምዕራፍ መጀመር አለበት አሉ
ዶ/ር መረራ ጉዲና በኢትዮጵያ አዲስ የዴሞክራሲ ምዕራፍ መጀመር አለበት አሉ
ለ14 ወራት በእስር ከቆዩ በኋላ ሐሙስ ጥር 9 ቀን 2010 ዓ.ም. በፌዴራል ደረጃ ክሳቸው እንዲቋረጥ ተደርጎ ከእስር ከተፈቱ 115 ተጠርጣሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ በኢትዮጵያ አዲስ የዴሞክራሲ ምዕራፍ መጀመር አለበት አሉ፡፡ ዶ/ር መረራ ከእስር ከተፈቱ በኋላ ሪፖርተር አነጋግሯቸው በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹ጃንሆይ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሲጀመርና ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን ለቆ ሲወጣ ለሚመሩት ሕዝባቸው ባደረጉት ንግግር ‹አዲስ ዘመን ጀምረናል ብለው ነበር፡፡ አሁንም የኢሕአዴግ አራቱ ድርጀቶች ሊቃነ መናብርት በነካ እጃቸው ሌሎቹንም እስረኞች ፈትተው አዲስ የዴሞክራሲ ምዕራፍ መጀመር አለባቸው፤›› ሲሉ አሳስበዋል፡፡  
የቢራ ፋብሪካዎች የዋጋ ጭማሪ ሊያደርጉ ነው
የቢራ ፋብሪካዎች የዋጋ ጭማሪ ሊያደርጉ ነው
የቢራ ፋብሪካዎች የዋጋ ጭማሪ ሊያደርጉ እንደሆነ ታወቀ፡፡ ቢጂአይ ኢትዮጵያ በምርቶቹ ላይ የዋጋ ጭማሪ አድርጎ ማከፋፈል መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአገሪቱ ውስጥ ቢራ ፋብሪካዎች ከዚህ ሳምንት ጀምሮ በማከፋፈያ ዋጋቸው ላይ የዋጋ ጭማሪ ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ መሆኑን የሪፖርተር ምንጮች የገለጹ ሲሆን፣ ቢጂአይ ግን ይህንን የዋጋ ጭማሪ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ አድርጓል፡፡
በወልዲያ በተፈጠረው ግጭት ታስረው የነበሩ ሰዎች በሙሉ ተፈቱ

በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ የቃና ዘገሊላ በዓል ለማክበር በወጡ ሰዎችና በፀጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ታስረው የነበሩ ሰዎች

በወልዲያ በተከሰተው ግጭት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ሰባት ደረሰ

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ ትናንት ጥር 12 ቀን 2010 ዓ.ም. እና ዛሬ ጥር 13 ቀን 2010 ዓ.ም.

ከፀረ ሽብር ሕጉ ውስጥ ስድስት አንቀጾች እንዲሰረዙ የቀረበለትን ጥያቄ ኢሕአዴግ ውደቅ አደረገ
ከፀረ ሽብር ሕጉ ውስጥ ስድስት አንቀጾች እንዲሰረዙ የቀረበለትን ጥያቄ ኢሕአዴግ ውደቅ አደረገ
በአገር አቀፍ ተደራዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከፀረ ሽብር ሕጉ ስድስት አንቀጾች እንዲሰረዙ የቀረበለትን ጥያቄ ኢሕአዴግ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አደረገው፡፡ ኢሕአዴግን ጨምሮ አሥራ ስድስት አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በፀረ ሽብር ሕጉ ላይ ሐሙስ ጥር 10 ቀን 2010 ዓ.ም. በፌዴሬሽን ምክር ቤት ለአራተኛ ጊዜ ድርድር ያደረጉ ሲሆን፣ ተቃዋሚዎች ከፀረ ሽብር ሕጉ ሊሰረዙ ይገባል ብለው ያቀረቧቸውን ስድስት አንቀጾች ኢሕአዴግ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጓቸዋል፡፡በአገር አቀፍ ተደራዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከፀረ ሽብር ሕጉ ስድስት አንቀጾች እንዲሰረዙ የቀረበለትን ጥያቄ ኢሕአዴግ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አደረገው፡፡ ኢሕአዴግን ጨምሮ አሥራ ስድስት አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በፀረ ሽብር ሕጉ ላይ ሐሙስ ጥር 10 ቀን 2010 ዓ.ም. በፌዴሬሽን ምክር ቤት ለአራተኛ ጊዜ ድርድር ያደረጉ ሲሆን፣ ተቃዋሚዎች ከፀረ ሽብር ሕጉ ሊሰረዙ ይገባል ብለው ያቀረቧቸውን ስድስት አንቀጾች ኢሕአዴግ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጓቸዋል፡፡
የኤርትራ ፕሬዚዳንትን መግለጫ መንግሥት አጣጣለው
የኤርትራ ፕሬዚዳንትን መግለጫ መንግሥት አጣጣለው
የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙኃን የሰጡትን መግለጫ መንግሥት አጣጣለው፡፡ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጠረው ቀውስ የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 ምክንያት መሆኑን ገልጸው፣ የሻዕቢያ መንግሥት የኢትዮጵያን መንግሥት አፍርሶ የሽግግር መንግሥት እንደሚያቋቁም ገልጸዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም የፕሬዚዳንቱ መግለጫ ፍሬ አልባና ትኩረትን ከመፈለግ የመጣ ነው ብለው፣ ፕሬዚዳንቱ አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም ለማለት ፈልገው መሆኑን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
የፌዴራል የፀጥታ ኮማንድ ፖስት በአዲስ አበባና በሌሎች አካባቢዎች  ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳሰበ
የፌዴራል የፀጥታ ኮማንድ ፖስት በአዲስ አበባና በሌሎች አካባቢዎች  ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳሰበ
የፌዴራል መደበኛ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት በጥምቀት በዓልና በአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ወቅት፣ የፀጥታ ችግር ሊፈጠር እንደሚችል በመግለጽ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳሰበ፡፡ የፀጥታ ኮማንድ ፖስቱ ባወጣው መግለጫ፣ የጥምቀት በዓልም ሆነ የኅብረቱ የመሪዎች  ጉባዔ በየዓመቱ ያለምንም ችግር ሲከበር እንደቆየ በማስታወስ፣ ዘንድሮ ግን ሁነቶቹ በሰላም እንዳይከናወኑ ለማድረግ በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች እንቅስቃሴ መኖሩን ጠቁሟል፡፡
ማስታወቂያ
ማስታወቂያ

ዓለም

አወዛጋቢው የትራምፕ ንግግር
አወዛጋቢው የትራምፕ ንግግር
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዓመት በፊት ከነበረው የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻቸው ጀምሮ ለስደተኞች ያላቸው አቋም አሉታዊ ነው፡፡ ‹‹ወንጀለኞች ናቸው›› የሚሏቸውን የሜክሲኮ ስደተኞች ለመቆጣጠር በአሜሪካና በሜክሲኮ ድንበር መካከል ግንብ እንደሚያስገነቡም የተናገሩት በምረጡኝ ዘመቻቸው ወቅት ነበር፡፡ ስደተኞች ላይ ማዕቀብ እንደሚጥሉም እንዲሁ፡፡
የዶናልድ ትራምፕን የመምራት ብቃትና የዋይት ሐውስን ውጥንቅጥ ያብጠለጠለው አወዛጋቢ መጽሐፍ
የዶናልድ ትራምፕን የመምራት ብቃትና የዋይት ሐውስን ውጥንቅጥ ያብጠለጠለው አወዛጋቢ መጽሐፍ
የሰሜን ኮሪያው ፕሬዚዳንት ኪም ጆን ኡን የኑክሌር መሣሪያ ፕሮግራማቸውን የሚያዩት አገራቸውን ከአሜሪና ከደቡብ ኮሪያ ሊሰነዘር ከሚችል ጥቃት እንደ መከላከያ አድርገው ነው፡፡ ሁለቱ የሰሜን ኮሪያ ተቀናቃኞች ግን ይህን አይቀበሉትም፡፡ ሁሌም የሰሜን ኮሪያን የኑክሌር ፕሮግራም እንደ ኮነኑ፣ በልሳነ ምድሩም የጋራ ወታደራዊ ልምምድ እንዳደረጉ ነው፡፡
ዓለማችንን በትምባሆ ኢንዱስትሪ ከተደቀነባት አደጋ እንዴት እንታደጋት?
ዓለማችንን በትምባሆ ኢንዱስትሪ ከተደቀነባት አደጋ እንዴት እንታደጋት?
ትምባሆና ከትምባሆ ጋር ተያያዥ የሆኑ ምርቶች ለጤና አደገኛ በሆነ ሁኔታ ጠንቅ አንደሆኑና በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት እየቀጠፈ፣ እንዲሁም ከዚህ የበለጠ ቁጥር ያላቸውን ሰዎች እየጎዳ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ትልልቅ ዓለም አቀፍ የትምባሆ አምራች ኩባንያዎች፣ ምርታቸው ጤና ላይ ሰለሚያደርሰው ጉዳት ለዘመናት አሳሳች የሆነና የውሸት መረጃዎችን ሲያወጡና ሲፈበርኩ እንደቆዩ የሚታወቅ ሀቅ ነው፡፡
ሊቢያ ውስጥ መፈናፈኛ ያጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን የመታደግ አዲስ ጅምር
ሊቢያ ውስጥ መፈናፈኛ ያጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን የመታደግ አዲስ ጅምር
በቅርቡ በሲኤንኤን አማካይነት የተሠራጨው ተንቀሳቃሽ ምሥል ሊቢያን የስደተኞች የምድር ገሃነም አድርጓታል፡፡ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ለማሰብ የሚከብድ የባሪያ ንግድ የሚካሄድባት አገር መሆኗ ብዙዎችን አስደንግጧል፡፡ በተለይ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ አገሮች ስደተኞች በሊቢያ ውስጥ በሕገወጥ አዘዋዋሪዎች ታግተው መከራ የሚያዩበት፣ በአገሬው ሰዎች ሳይቀር ጉልበታቸው በነፃ የሚበዘበዝበት፣ በተጨናነቁ እስር ቤቶች ስቃይ የሚፈጸምባቸው፣ ከዝርፊያ በተጨማሪ ግድያ ሳይቀር የሚፈጸምባቸው ስደተኞች በመቶ ሺዎች ይቆጠራሉ፡፡
የኤኤንሲ አዲሱ መሪ ሲሪል ራማፎሳ
የኤኤንሲ አዲሱ መሪ ሲሪል ራማፎሳ
የደቡብ አፍሪካ አውራ ፓርቲ ‹‹አፍሪካን ናሽናል ኮንግረስ›› (ኤኤንሲ) በፓርቲው ውስጥ የተፈጠረውን ክፍፍል ወደ አንድ ያመጣሉ የተባሉትን ሲሪል ራማፎሳ መሪ አድርጎ መርጧል፡፡ በደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ የሚመራውን ኤኤንሲ የሚረከቡት ባለሀብቱ ራማፎሳ፣ በአገሪቱ የተንሰራፋውን ሙስናም ያስተነፍሳሉ ተብሎ ተስፋ ተጥሎባቸዋል፡፡ አገሪቱም እ.ኤ.አ. በ2019 ለምታደርገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫም  ራማፎሳ ተስፋ ተጥሎባቸዋል፡፡ ሆኖም በፓርቲው ውስጥ ክፍፍል ሊፈጠር ይችላል ተብሏል፡፡
ቨላድሚር ፑቲን በዶናልድ ትራምፕ ላይ የበላይነት ያስገኘላቸው የመካከለኛው ምሥራቅ ድንገተኛ ጉብኝት
ቨላድሚር ፑቲን በዶናልድ ትራምፕ ላይ የበላይነት ያስገኘላቸው የመካከለኛው ምሥራቅ ድንገተኛ ጉብኝት
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ መሰንበቻውን በመካከለኛው ምሥራቅ ነውጥ የፈጠረ ድርጊት ከፈጸሙ ከቀናት በኋላ፣ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ደግሞ በመካከለኛው ምሥራቅ ያልተጠበቀ ጉብኝት በማድረግ የበላይነቱን ይዘዋል፡፡ ትራምፕ የእስራኤል ዋና ከተማ ኢየሩሳሌም መሆኗን ዕውቅና በመስጠት የአሜሪካ ኤምባሲ ወደዚያ እንደሚዛወር አስደንጋጭ ውሳኔ በማስተላለፋቸው፣ ከመካከለኛው ምሥራቅ ጀምሮ በዓለም ዙሪያ ተቃውሞ ተቀስቅሶባቸዋል፡፡
ማስታወቂያ
ማስታወቂያ

ምን እየሰሩ ነው?

የሦስት አሠርታት የረድዔት ጉዞ
የሦስት አሠርታት የረድዔት ጉዞ
የካናዳ ክርስቲያናዊ የሕፃናት መርጃ ድርጅት ኢትዮጵያ ውስጥ በተወሰኑ አካባቢዎች ተሠማርቶ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ማከናወን ከጀመረ 30 ዓመት ሆኖታል፡፡ ድርጅቱ እስካሁን ባከናወናቸውና ወደፊት ሊሠራ ባቀዳቸው እንቅስቃሴ ዙሪያ የድርጅቱ የኢትዮጵያ ተጠሪ ፈለቀ ታደለ (ዶ/ር)ን ታደሰ ገብረማርያም አነጋግሯቸዋል፡፡
‹‹ለየት የሚያደርገን ሰሊጥን በብቸኝነት ወደ ደቡብ ኮሪያ መላካችን ነው››
‹‹ለየት የሚያደርገን ሰሊጥን በብቸኝነት ወደ ደቡብ ኮሪያ መላካችን ነው››
ተወልደው ያደጉት በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ ነው፡፡ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአክሱም ከተማ በመማር ላይ እያሉ በድንገት ታላቅ ወንድማቸውን ፍለጋ በ1966 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ ይመጣሉ፡፡
ለወደፊት ስኬት መሠረት የሚጣልበት ልጅነት
ለወደፊት ስኬት መሠረት የሚጣልበት ልጅነት
ወ/ሮ አሰፋች ኃይለ ሥላሴ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሳይኮሎጂ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሳውዝ አፍሪካ (ዩኒሳ) በሳይኮሎጂ ከሰዎች ሕገወጥ ዝውውር ላይ አተኩሮ አግኝተዋል፡፡ ሥራ የጀመሩት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን በማማከር ነው፡፡ በአዲስ አበባ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ አካል ጉዳተኛ ሕፃናትና ወጣቶች ላይ ሠርተዋል፡፡
የአካል ጉዳተኞች ድምፅ
የአካል ጉዳተኞች ድምፅ
ተስፋዬ ገብረማርያም የቲኤፍቲ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር ነው፡፡ የሚንቀሳቀሰው በክራንች በመታገዝ ነው፡፡ ሁለት እግሩን ያለ ድጋፍ እንዳይንቀሳቀስ ያደረገው የአካል ጉዳት የደረሰበት ገና ልጅ ሳለ ነበር፡፡ አጋጣሚው ሮጦ ላልጠገበው ተስፋዬና ቤተሰቦቹ ከባድ ሐዘን ውስጥ የከተታቸው ነበር፡፡ በተለይ እናቱ ዳግመኛ ልጅ ለመውለድ እስኪወስኑ ድረስ አጋጣሚው አስደንግጧቸው እንደነበር ተስፋዬ ይናገራል፡፡
‹‹የአይቲ ኢንዱስትሪ በዓለም መሪ ሆኖ ሳለ በአገራችን ግን እንደ ዝቅተኛ ኢንዱስትሪ ይቆጠራል!››
‹‹የአይቲ ኢንዱስትሪ በዓለም መሪ ሆኖ ሳለ በአገራችን ግን እንደ ዝቅተኛ ኢንዱስትሪ ይቆጠራል!››
 ሳይበርሶፍት ባለፉት 19 ዓመታት ለተለያዩ ተቋሞች ልዩ ልዩ ሲስተሞችን የሠራ የአይቲ (ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ) ተቋም ነው፡፡ የመንግሥትና የግል ተቋሞች በዲጂታል ሲስተም የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻልም የድርሻቸውን እየሰጡ ነው፡፡ የፍትሕ፣ የትምህርትና የጤና ተቋሞችን ጨምሮ የ702 ድርጅቶችን ሲስተም አልምተዋል፡፡ በተቋሙ እንቅስቃሴ ዙሪያ የሳይበርሶፍት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተከስተብርሃን ሀብቱን ምሕረተሥላሴ መኰንን አነጋግራቸዋለች፡፡
ሕፃናት የተሻለ እንዲኖሩ የማድረግ ስንቅ
ሕፃናት የተሻለ እንዲኖሩ የማድረግ ስንቅ
የሕፃናት አድን ድርጅት (ሴቭ ዘ ችልድረን) በዓለም ላይ ያሉ ሕፃናት የተሻለ የመኖር ዕድል እንዲያገኙ መሥራት ከጀመረ ከ60 ዓመታት በላይ ተቆጥረዋል፡፡ በየአገሮቹ በተቋቋሙ የሕፃናት አድን ድርጅቶች ሥራዎች ሲከናወኑ  ቢቆዩም፣ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ሰባቱ ድርጅቶች ተዋህደው በአንድ ጥላ ሥር ሆነዋል፡፡ ድርጅቱ ሕፃናት በተለይም ለችግር የተጋለጡ ከችግራቸው እንዲወጡና የተሻለ ሕይወትን እንዲኖሩ ይሠራል፡፡ ከድርጅቶቹ ውህደት በኋላም የተሻለ ውጤት እንደተመዘገበ የድርጅቱ ኃላፊዎች ይናገራሉ፡፡