| 20 February 2019 የናይጄሪያ ምርጫ መራዘም አብዛኛው ናይጄሪያውያን ባለፈው ቅዳሜ የሚካሄደውን የአገሪቱን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለመሳተፍ ከነበራቸው ጉጉት የተነሳ ከምርጫው አምስት ሰዓት ያህል ቀድሞ የተነገረውን ‹‹የምርጫው ተላልፏል›› ዜና ‹‹የውሸት ዜና ነው›› በሚል ነበር ያለፉት፡፡ ሆኖም ይህ ዜና እውነት ነበር፡፡ ናይጄሪያውያን በጉጉት ሲጠብቁት ነበር የተባለው ምርጫ ለአንድ ሳምንት ያህል ተራዝሟል፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ
| 13 February 2019 የኢራናውያኑ አብዮት ሲታወስ እ.ኤ.አ. 1979 ለኢራናውያን ልዩ ዓመት እንደነበር ይነገራል፡፡ የኢራናውያን አብዮት የተቀጣጠለበትና ድል የተቀዳጀበት ይኸው ዓመት፣ ኢራን አሁን ላላት ጥንካሬ መሠረት የተጣለበትም ወቅት ነበር፡፡ ይህ ከሆነ ከትናንት በስቲያ 40 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ
| 6 February 2019 የቬንዙዌላ ቀውስ በቬንዙዌላው ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮ እና በተቀናቃኛቸውና የሽግግር መንግሥትነትን ለራሳቸው ባቀዳጁት ሁዋን ጋይዶ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ቬንዙዌላውያንን ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ መንግሥታትንም ከፋፍሏል፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ
| 30 January 2019 የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አል በሽር የግብፅ ጉብኝት የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አል በሽር ከግብፅ አቻቸው አብዱል ፈታህ አልሲሲ ጋር ለመምከር እሑድ ጥር 19 ቀን 2011 ዓ.ም. ወደ ግብፅ አምርተዋል፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ
| 23 January 2019 እስራኤልና ኢራን በምድረ ሶሪያ አሜሪካና ሩሲያ ጎራ ለይተው የእጅ አዙር ጦርነታቸውን የሚያካሂዱባት ሶሪያ ከትናንት በስቲያ (ጥር 12 ቀን 2011 ዓ.ም.) የእስራኤልን ሚሳይሎች ስታስተናግድ አድራለች፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ
| 16 January 2019 በዚምባቡዌ ተቃውሞ ያስከተለው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ዚምባቤያውያን የቤንዚንና ናፍጣ ዋጋ መጨመርን ተከትሎ በዚምባቡዌ ዋና ከተማ ሃራሬና በቡላዋዮ ለተቃውሞ ወጥተዋል፡፡ መንግሥት በነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ማድረጉን ካሳወቀ በኋላ ለተቃውሞ የወጡት ዚምባቤያውያን በየመንገዱ ጎማ ሲያቃጥሉና ድንጋይ ሲወረውሩ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ተስተውለዋል፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ
| 9 January 2019 የሰሜን ኮሪያው ኪም ጆን ኡንግ የቻይና ጉብኝት የሰሜን ኮሪያው ፕሬዚዳንት ኪም ጆን ኡንግ ለአራት ቀናት ጉብኝት ቻይና ገብተዋል፡፡ ከአሜሪካ ጋር ለሁለተኛ ጊዜ ለመገናኘት ዝግጅት እየተደረገ ባለበት ወቅት ፕሬዚዳንት ኪም ቻይና የገቡት፣ በቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂፒንግ ግብዣ እንደሆነ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ
| 2 January 2019 የአሜሪካ ጦር ከሶርያ መውጣት አሜሪካ በሶርያ ያሏትን ወታደሮች በሙሉ እንደምታስወጣ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተናገሩት ከሁለት ሳምንታት በፊት ነበር፡፡ ‹‹ሁሉም ወደ አገራቸው ይመለሳሉ፡፡ አሁን ይመለሳሉ፤›› ብለው ፕሬዚዳንቱ ሲናገሩ፣ የአገሪቱ ባለሥልጣናትም የአሜሪካ ወታደሮች ሶርያን በ30 ቀናት ውስጥ እንዲለቁ ጊዜ መሰጠቱን አሳውቀው ነበር፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ
| 26 December 2018 በተጠናቀቀው 2018 ትኩረት ያገኙ ዘገባዎች የፈረንጆቹ ዓመተ 2018 አመፆች፣ ጦርነቶች፣ ስምምነቶች፣ አደጋዎችና ሌሎችንም ክስተቶች አስተናግዷል፡፡ ዓመቱ ለማብቃት የሳምንት ያህል ዕድሜ ሲቀረው፣ በዓመቱ በዓለም መነጋገሪያ የተባሉ ክንውኖች በየመገናኛ ብዙኃኑ ተዘግበዋል፡፡ የተለያዩ መገናኛ ብዙኃንና ብሎገሮች እንደራሳቸው ዕይታ ዋና ነበሩ ያሏቸውን አትተዋል፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ
| 19 December 2018 ሳዑዲ አሜሪካ በአገሬ ጉዳይ ጣልቃ ገብታለች ስትል አወገዘች የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት፣ በየመን ላይ በጥምር ለከፈተው ጦርነት የጀርባ አጥንት ሆና ስትደግፍ የነበረችው አሜሪካ ከጦርነቱ ራሴን አገላለሁ ማለቷን አወገዘ፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው፣ የአሜሪካ ሴኔት የአሜሪካ መንግሥት ሳዑዲ ዓረቢያ የምትመራውን ወታደራዊ ጥምረት መደገፍ የለበትም በሚል ሰሞኑን ውሳኔ ካሳለፈ በኋላ ሳዑዲ ከወዳጇ አሜሪካ ጋር የቃላት ጦርነት ገብታለች፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ