በጥሩነህ ዜና (አምባሳደር)
በዓለም ላይ እ.ኤ.አ በ1940 ከነበረው 2.3 ቢሊዮን ሕዝብ ውስጥ 60 ሚሊዮን ያህል የተገደለበትና የሰው ልጅ በሺሕ የሚቆጠሩ ዓመታት ፈጅቶ ከገነባው ሥልጣኔ ገሚሱን ያህል በአምስት ዓመታት ውሰጥ ያወደመውን ሁለተኛውን የዓለም ጦርነት በአሸናፊነት የተወጡ ኃያላን አገሮች፣ ተመሳሳይ እልቂት ለወደፊት እንዳይከሰት ለማድረግና የበላይነታቸውን አረጋግጠው ለማቆየት የገነቡት ዓለም አቀፍ ሥርዓት ባለፉት ሰባት አሥርተ ዓመታት አንፃራዊ ሰላም፣ መጠነ ሰፊና ጥልቀት ያላቸው የፖለቲካ የሶሻልና የኢኮኖሚ ዕድገቶች በምድራችን እንዲከሰቱ አስችሏል፡፡