Skip to main content
x
ወቅት ሽግግር በኢሬቻ

ወቅት ሽግግር በኢሬቻ

ኢሬቻ ከተከበሩትና ከተቀደሱት የኦሮሞ ክብረ በዓሎች አንዱ ሲሆን፣ ከጥንታውያኑ የኦሮሞ አባቶች ሲወርድ ሲዋረድ እንደመጣ ይነገራል፡፡ ‹‹ኢሬቻ እርጥብ ሣር፣ ቅጠል ቄጠማ አበባ ማለት ነው›› የሚሉት የኦሮሞ አባ ገዳ ዋና ሰብሳቢ የሆኑት አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ፣ ኢሬቻው ለእግዚአብሔር ምስጋና የምናቀርብበት ሥርዓት ነው ይላሉ፡፡

‹‹አምና በሰላም በጤና 13ቱን ወር አስጨርሰኸናል፡፡ መጪውን ዓመት ደግሞ በሰላም እንድታደርሰን ይሁን፡፡ ይኸንን ለሰው ልጅ ለሁሉም ፍጥረት ብለህ የፈጠርከውን ንፁህ ውኃ በአንተ ኃይል አጣርተህ ያስቀመጥከውን በሐይቅህ ላይ ምስጋናህን እናቀርባለን፡፡ ውኃ ንፁህ ነውና፡፡›› ምርቃቱ በየዓመቱ ከመስቀል በዓል በኋላ በሚመጣው እሑድ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓል ተከትሎ የሚመጣ ነው፡፡ ምርቃቱም የሚዥጎደጎደው መራቂው በባህላዊ የኦሮሞ አለባበስ ተውበው የአንበሳ ለምድ አጥልቀው አንፋሮ ደፍተውና ጋሻ ይዘው ነው፡፡

‹‹ኢሬቻ ሣሩን አበባውን እግዚአብሔር ነው ያበቀለው፡፡ ይኸንን አበባውን አብቅለህ ለከብቶች ሣር አብቅለህ፣ ለሰው ልጅ ደግሞ ዘር ሰጥተህ፣ ፍሬ አሰጥተህ ስላደረስከን ለአንተ ኢሬቻ እናቀርባለን፡፡ በክረምቱ መልካው ወንዙ ሞልቶ ዘመድ ከዘመድ ተለያይቶ አሁን ስለተገናኘ እግዚአብሔር ለአንተ ኢሬቻ እናቀርባለን፡፡››

የመመረቂያው ቦታ አድባር ‹‹ድሬ›› ይባላል፤ የተስተካከለ ቦታ ማለት ነው፡፡ ከዚህ ካልተመረቀ ወደታች ወደ ሐይቁ አይኬድም፡፡ ዱለቻ በሬ ይታረዳል፡፡ ከመልካውም ሲኬድ ኮርማ ይታረዳል፡፡ ምርቃቱም ‹‹እንኳን በሰላም ከክረምቱ ወደ ብርሃኑ አወጣኸን፡፡ ዘመኑን በሰላም ያድርግልን፡፡ የእኛን ሕዝብና አገሪቷን ይባርክልን›› ይባልበታል፡፡ ሆራ አርሴዲ የክብረ በዓሉ ዋነኛ ስፍራ ነው፡፡ ሰፊና ክብ ነው፡፡ አካባቢው ዙርያው በዛፎች ተሸፍኗል፡፡

ለበዓሉ አክባሪዎችና ሥነ ሥርዓቱ ተከታዮች ምቹ ስፍራ ነው፡፡ ታዳሚዎቹ ለምለም ቅጠል ቀጤማ ርጥብ ሣር አደይ አበባ ይዘው ሐይቁ ውስጥ እየነከሩ ይረጫሉ፤ ወደራሳቸውም ያስነካሉ፡፡ ከሐይቁ ዳርቻም ያስቀምጣሉ፡፡ ክርስቲያኖችም፣ ሙስሊሞችም፣ የዋቄ ፈታ ተከታዮችም አሉበት፡፡ ዝማሬና ምርቃት ልዩ ልዩ ሥነ ሥርዓት በሐይቁ ዳርቻ በሚገኘው ዋርካ ሥር ያደርጉታል፡፡ ዋርካውን ‹‹ኦዳ›› ይሉታል፡፡

የባህል ባለሙያው አቶ ገዛኸኝ ግርማ በድርሳናቸው እንደጻፉት፣ የኦሮሞ የገዳ ሥርዓት ልዩ ልዩ ቁሳዊ መገለጫዎች አሉት፡፡ በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት የቅርሱ ቁሳዊ መገለጫዎች መካከል የኦዳ ዛፍ አንዱ ነው፡፡ በኦሮሞ ባህል የኦዳ ዛፍ የእምነትና የፖለቲካ ማዕከል ሲሆን፣ ዛሬም ድረስ ለብሔሩ አባላት የተለየ ተምሳሌታዊ ፋይዳ አለው፡፡ ኦዳ ለጉባዔ ማስኬጃነት የተመረጠው በግርማ ሞገሱና በጥላው ስፋት ብቻ አይደለም፡፡

የኦሮሞ ሽማግሌዎች እንደሚናገሩት፣ ኦዳን ከሌሎች ዛፎች ይበልጥ ተመራጭ ያደረገው ከክረምት እስከ በጋ ሳይደርቅ (ቅጠሉን ሳያራገፍ) መቆየት የሚችልና የሕዝቡን ተስፋና የአገሩን ልምላሜ የሚጠቁም ምልክት በመሆኑ ጭምር ነው፡፡

ኢሬቻ ከተከበሩትና ከተቀደሱት የኦሮሞ ክብረ በዓሎች አንዱ ሲሆን ከጥንታውያኑ የኦሮሞ አባቶች ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ነው፡፡ ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ዞኖች የመጡ በዓል አክባሪዎች የአካባቢያቸውን ባህል የሚያንፀባርቁ አልባሳት ለብሰው ጫማ ተጫምተው ጌጣጌጥ አጥልቀው የሚታዩበትም ነው ኢሬቻ፡፡

‹‹ኢሬቻ እርጥብ ሣር፣ ቅጠል ቄጠማ አበባ ማለት ነው›› የሚሉት የኦሮሞ አባ ገዳ ዋና ሰብሳቢ የሆኑት አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ፣ ኢሬቻው ለእግዚአብሔር ምስጋና የምናቀርብበት ሥርዓት ነው ይላሉ፡፡ ‹‹ኢሬቻ ሣሩን አበባውን እግዚአብሔር ነው ያበቀለው፡፡ ይኸንን አበባውን አብቅለህ ለከብቶች ሣር አብቅለህ፣ ለሰው ልጅ ደግሞ ዘር ሰጥተህ፣ ፍሬ አሰጥተህ ስላደረስከን ለአንተ ኢሬቻ እናቀርባለን፡፡ በክረምቱ መልካው ወንዙ ሞለቶ ዘመድ ከዘመድ ተለያይቶ አሁን ስለተገናኘ እግዚአብሔር ሆየ አንደርስብህምና ለአንተ ኢሬቻ እናቀርባለን፡፡››

እንደ አባ ገዳ በየነ አገላለጽ፣ የመመረቂያው ቦታ አድባር ‹‹ድሬ›› ይባላል፤ የተስተካከለ ቦታ ማለት ነው፡፡ ከዚህ ካልተመረቀ ወደታች ወደ ሐይቁ አይኬድም፡፡ ዱለቻ በሬ ይታረዳል፡፡ ከመልካውም ሲኬድ ኮርማ ይታረዳል፡፡ ምርቃቱም ‹‹እንኳን በሰላም ከክረምቱ ወደ ብርሃኑ አወጣኸን፡፡ ዘመኑን በሰላም ያድርግልን፡፡ የእኛን ሕዝብና አገሪቷን ይባርክልን›› የሚል ነበር፡፡

ሆራ አርሴዲ የክብረ በዓሉ ዋነኛ ስፍራ ነው፡፡ ሰፊና ክብ ነው፡፡ አካባቢው ዙርያው በዛፎች ተሸፍኗል፡፡ ለበዓሉ አክባሪዎችና ሥነ ሥርዓቱ ተከታዮች ምቹ ስፍራ ነው፡፡ ታዳሚዎቹ ለምለም ቅጠል ቀጤማ ርጥብ ሣር አደይ አበባ ይዘው ሐይቁ ውስጥ እየነከሩ ይረጫሉ፤ ወደራሳቸውም ያስነካሉ፡፡ ከሐይቁ ዳርቻም ያስቀምጣሉ፡፡ ክርስቲያኖችም፣ ሙስሊሞችም፣ የዋቄ ፈታ ተከታዮችም አሉበት፡፡ ዝማሬና ምርቃት ልዩ ልዩ ሥነ ሥርዓት በሐይቁ ዳርቻ በሚገኘው ዋርካ ሥር ያደርጉታል፡፡ ዋርካውን ‹‹ኦዳ›› ይሉታል፡፡

በኦዳው ዙሪያ ወንዱና ሴቱ አዋቂውና ሕፃኑ በቡድን በቡድን ተቀምጠዋል፤ እጣኑን ያጨሳሉ፣ ሰንደሉን ይለኩሳሉ፡፡ ለሰንደሎች ማስቀመጫ በተሠራው ክብ ብረት ላይ ያስቀምጡታል፡፡ ቡናውን ያፈላሉ፣ ይቀማምሳሉ፡፡ ኅብረ ዝማሬ ያሰማሉ፡፡ ከተቀመጡት ሌላ በርካታ ቁጥር ያለው ሰው ዙሪያውን ቆሞ በጽሞና ሥነ ሥርዓቱን ይከታተላል፡፡ ጸሎቱን ያደርሳል፡፡ በቅርብ ርቀትም ባህላዊውን ጨዋታ የሚያደርጉ ወንዶችም ሴቶችም ይታያሉ፡፡ እንደ ቢሾፍቱ ነዋሪዋ ወ/ሮ ዓለምነሽ ተፈራ አገላለጽ፣ ‹‹ኢሬቻ እንኳን ከድፍርሱ ውኃ ወደጠራው ውኃ አሸጋገርከን የምንልበት መልካውን የምናከብርበት፣ ሴራውን የምንፈጽምበት ነው፤ መሬሆ የተባለ የምስጋና መዝሙር እናሰማበታለን፤›› ብለዋል፡፡

እድምተኞች እጆቻቸው በልዩ ልዩ ቅርፅ የተዘጋጁ በትሮች ይዘው አንፋሮ ራሳቸው ላይ አጥልቀው የሚጨፍሩ ጎረምሶች፣ የተለያዩ ባህላዊ ልብሶች ቀይ ነጭና ጥቁር ኅብረ ቀለማት ያለውን ለብሰው ይታዩበታል፡፡ አንፋሮ የአንበሳ ምልክት፣ የያዙት ጋሻ (ዋንታ) ውኃ ውስጥ ከሚኖረው የጉማሬ ቆዳ የተለበደበት ነው፡፡ ‹‹ወደ ሆራ አርሴዲ ሲወረድ ሴራ (ሥርዓት) አለው፡፡ በዋንታው ውኃ ይቀዳና ይረጭበታል፡፡

ከዚህ ቀደም በበዓሉ ላይ ከአባ ገዳዎች ጋር ሲመርቁ ያገኘናቸው ሊቀ አዕላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን ስለ ኢሬቻ እንዲህ ያብራራሉ፡፡ ‹‹ኢሬቻ ትርጉሙ እርቅ ማለት ነው፡፡ ሰዎችና ሰዎች የሚታረቁበት እግዜርና ሰው የሚታረቁበት ሰላም፣ ስምምነት አንድነት ምቾት ማለት ነው፡፡ በክረምት ወንዞች ሄደው ሳያልቁ ሳይደርቁ እዚህ ያለውና እዚያ ሳይገናኝ ይቆያል፡፡ ስለዚህ ወደ ወንዙ ይሄድና ከወዲህና ማዶ ያለው ‹አላችሁ ደርሳችኋል እኛ ደርሰናል› እያለ እርስ በርስ ሰላምታ ይለዋወጣል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ኢሬቻውን ፈጽሞ ይሄዳል፡፡››

ኢሬቻ የሚከበርበት መስከረም መገባደጃ የክረምት ማብቂያ መስከረም 26 ቀን የመፀው ወቅት የአበባ መግቢያ ነው፡፡  የአበባ በዓል መስከረም 25 ቀን (በኋላ መስከረም 10) ተቀፀል ጽጌ (አበባን ተቀዳጅ) እየተባለ በስድስተኛው ክፍለ ዘመን ከነበሩት አፄ ገብረ መስቀል ዘመን ጀምሮ እስከ አፄ ኃይለ ሥላሴ ድረስ በቤተ መንግሥት ይከበር ነበር፡፡