Skip to main content
x

የምን መድበለ ፓርቲ? የምን ፌዴራሊዝም?

በኃይለ ማሪያም ደንቡ

ሁሉም ነገር ፈሳሽ ነው ከላይ ወደ ታች፣ ከታች ወደ ላይ ሁሉም ነገር ተቀያሪ ነው በቦታና በጊዜ፡፡ ኅብረተሰባችን ኢትዮጵያም እንደዚያው ነች፡፡ ከዝቅተኛው ከባሪያ ብረተሰብ ዛሬ ወደ ደረሰችበትና ወለችበት አዲሱ ሞክራያዊ መንግት ወደ ምትሉት፡፡ አዎ ከዚያ ደርሳለች ከነበረችበት አሁን ወለችበት፡፡ የመሆን ደቱ ይቀጥላል ግን ይ ፍሰት በኮቻው ብዙ የፖለቲካ ችግሮችን አብሮ ይዞ መጥቷል፡፡ ዛሬ ከሚያደናግሩትና ግራ ከሚያጋቡ የፖለቲካ ችግሮች መድበለ ፓርቲ (ፕሉራሊዝም) እና ፌዴራሊዝም ሳይጠቀሱ የማይታለፉ ጥያቄዎች ናቸው፡፡

ዛሬ ልጆ የፖለቲካ አዋቂዎ በሚያሰሙት መድበለ ፓርቲና ፌዴራሊዝም መፈክሮች ላይ አስተያየት መስጠት ግድ ይላል፡፡ ግን መጀመያ መድበለ ፓርቲ ምንድነው? የፍልስፍና ጥናት ፕሉራሊዝምን በአንድ በኩል፣ የእሱ ተቃራኒ የሆነው ሞንዚምን በሌላ በኩል እየወሰደ ሰዎች የተፈጥሮና የኅብረተሰብን አካሄድ እንዴት እንደሚያዩትና እንደሚረዱት፣ በአንድ ወይስ በብዙ መጽሮች እንደሆነ ይተነትናል፡፡ የሁቱም ፍልስፍና ተከታዮች የነገሮችን ሒደት በተለያየ መንገድ ስለሚረዱት፣ የፈላስዎችን ክርክር እዚሁ ትተን ስለኅብረተሰቡ የሚያጠኑትን (ሶስት) ሊቃውንት ስለፕሉራሊዝም ምን እንደሚሉ እንመልከት፡፡

ፍልስፍና አጠቃላይ ሳይንስ ነው፡፡ ሶሾሎጂ ግን ተጨባጩ ነው፡፡ ስለሆነም ወደ ተጨባጩ ሳይንስ እንሂድ፡፡ ግን እኮ ያ ትልቅ ፈላስፋ ማኅበራዊ ሳይንስን እንደ ተፈጥሯዊ ሳይንስ በፎርሙላ ማስቀመጡ ያስቸግራል እንዳለው ወደ ሶሾሎጂ ብንሄድም መቸገራችን አይቀርም፡፡ ይህ ፎርላ የሌው ሳይንስ በተለይ በኢትዮጵያ ፖለቲከኞች እጅ ከገባ ወዲህ በጣም አደናጋሪ ሆኗል፡፡ ይሁንና ወደ ተነሳንበት ፕሉራሊዝም ከመግባታችን በፊት አንድ ነገር ልበል፡፡ ዓለም በሦስት የፖለቲካ ሥርዓቶች የተከፈለች ነች፡፡ እነሱም የሦስተኛ ዓለም ሥርዓት የከበርቴ ሥርዓትና የሶሻሊስት ሥርዓት ናቸው፡፡ በማኅበራዊ ሳይንስ ከሁሉም በላይ የሚከብደው ስለመንግሥት ምንነት መረዳትና ማስረዳት ነው፡፡ የከበርቴ ሥርዓተ መንግሥት ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች እኩል የቆመና የሁሉንም ጥቅም አስከባሪ ነው ሲል፣ የሶሻሊስት ኅብረተሰብ ደግሞ በመደብ በተከፋፈለ ኅብረተሰብ ውስጥ መንግሥት የፖለቲካ ሥልጣን የያዘው መደብ ጥቅም አስከባሪ እንጂ የሁሉም መደቦች አስጠባቂ ነው የሚባል ነገር የለም ይላል፡፡

  ኢትዮጵያ የሦስተኛው ዓለም አባል ነች፡፡ የመንግሥት መዋቅሯ ምን ይሁን? ፕሉራሊዝም ኢትዮጵያ ውስጥ ይሠራል ወይስ አይሠራም ከማለቴ በፊት፣ የከበርቴና የሶሻሊስት ኅብረተሰቦች ምን እንደሚመስሉ በአጭሩ ማሳየቱ ይበጃል፡፡ ፕሉራሊዝም ያደገው የከበርቴ ሥርዓት የፖለቲካ መዋቅር ነው፡፡ የተጀመረው እ.ኤ.አ. በ1915 በእንግሊዝ ሊቃውንት ነው፡፡ ጀማሪው ሮልድ ላስኪ ነው፡፡ ከዚያም የጀርመኑ ሊቃውንት ሀንስ ጉንተር አሴልና ሌሎችም ተጨምረው ሐሳቡን አስፍተውና አዳብረው የከበርቴ ኅብረተሰብ የፖለቲካ መመርያ አደረጉት፡፡ እንደ ነሱ አባባል መንግሥት እንደ ኳስ አዋች ዳኛ ነው፡፡ ኅብረተሰቡ ውስጥ ያሉትን የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ፍላጎትን በትክክል መፈጸሙንና አለመፈጸሙን ይከታተላል፡፡ ሕግና ደንብ ያስከብራል፡፡ ባለው ዴሞክራሲያዊ የምርጫ ተቋማት አማካይነት የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ተወዳድረው የፖለቲካ ሥልጣን ይረካከባሉ፡፡ የዛሬ አሸናፊ ነገ ተሸናፊ፣ የዛሬ ተሸናፊ ነገ አሸናፊ መሆኑን ስለሚረዳ ጫጫታ አይኖርም፡፡ ሁሉም ሕግ አክባሪና ለሕግ ተገዥ ነው እያለ ይቀጥላል የመድበለ ፓርቲ ንድፈ ሐሳብ የሶሻሊስት ኅብረተሰብ ከዚህ ይለያል፡፡     የመድበለ ፓርቲ ተቃራኒ ነው፡፡ አንድ ፓርቲ እንጂ ብዙ ፓርቲዎች አይፈቀዱም፡፡ የመንግሥት መዋቅሩ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ነው፡፡ የዚህ ንድፈ ሐሳብ መሥራቾችና አዳባሪዎች ማርክስ፣ ኤንግልስና ሌኒን ናቸው፡፡ በእነሱ አባባል የዕድገት ምንጭ ሥራ ነው፡፡ ሰው ካልሠራ ሊኖር አይችልም፡፡ ማንኛውም ኅብረተሰብ ለኑሮ የሚያስፈልጉትን ቁሳቁሶችን ማምረት አለበት፡፡ የቁሳቁስ አምራቾች ወዛደርና ገበሬዎች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ተበዳዮች ናቸው፡፡ በመሆኑም እነዚህ ወዳጃዊ መደቦች በታሪክ አጋጣሚ የፖለቲካ ሥልጣንን መጨበጥ ከቻሉ ሥልጣንን በማዕከል ጥብቅ አድርጎ መያዝ እንጂ ካሸነቸው ጠላቶች ጋራ የምን ሥልጣን መጋራት? የምን እሽሩሩ? ፖለቲካውን የያዘ መንግሥት ኢኮኖሚውን የያዘ መንግሥት ፖለቲካውን ይይዛል፡፡ ታዲያ እነዚህን ሁለቱን አጣምሮ ይዞ ኅብረተሰቡን መምራት እንጂ የምን መድበለ ፓርቲ? ይህ ብቻ አይደለም፡፡ የሠራተኛው መደብ በተፈጥሮው ሩዴሞክራሲያዊ ነው፡፡ እሱ ራሱ ነፃ ወጥቶ ሌሎችንም መደቦች ነፃ አውጪ ነው በመሆኑም እያለ ይቀጥላል፡፡ የሶሻሊዝም ንድፈ ሐሳብ ከሁለቱ የፖለቲካ ሥርዓቶች የትኛው ይሻላል? ለኢትዮጵያችን የትኛው ነው ተስማሚ? አንድ ወፍ በሰዓት አንድ ኪሎ ግራም ጥራ ጥሬ ቢለቅም ሦስት ወፎች ስንት ኪሎ ይለቅማሉ ተብሎ አንዱ ቢጠየቅ እንደ አለቃቀማቸው ነው ብሎ መለሰ ይባላል፡፡ የመምረጡን መብት ለእናንተ ልተውና የእስካሁኑን እንቋጭ፡፡

በአደገ ኢኮኖሚ በአደገ መዋቅርን ይወልዳል፡፡ መንግሥት የምንለው ትልቁ የላይ መዋቅር በአደገ ኢኮኖሚ የተዋቀረ ነው፡፡ መንግሥትን የሚያስተዳድሩና አገሩን የሚመሩ የፖለቲካ ድርጅቶችም ቁሳዊና መንፈሳዊ ባህላቸው እንደዚያው የዳበረ ነው፡፡ ሁለቱም የፖለቲካ ሥርዓቶች ሕግ አክባሪና ለሕግ ተገዥ ናቸው፡፡ ይህም በመሆኑ ሁለቱም ሥርዓቶች እርስ በርስ የሚበላለጡበት ጥሩና መጥፎ ጎን ይኑራቸው እንጂ፣ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቶች ናቸው፡፡ ዴሞክራሲ ቃሉ ሳይሆን ይዘቱ እያስማማን እንደሆነ ነው እንጂ፣ መድበለ ፖርቲም ለከበርቴ ኅብረተሰብ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትም ለሶሻሊዝም ይሠራል፡፡

  ለኢትዮጵያችን የሚለውን ሁለተኛውን ጥያቄ ለመመለስ ቸኩያለሁ፡፡ መድበለ ፓርቲ ኢትዮጵያ ውስጥ አይሠራም ይሠራልም በአንድ ራስ ምላስ ዋሾ! ዋሾ! ተረጋጉ አደብ ግዙ ስታክ ነው እንዳለው አዳኙ ሰውዬ ቢሆንስ? ሚዳቆዋን በአንድ ጥይት  ጆሮዋንና እግሯን ሰፋሁት አለ፡፡ እንዴት ተደርጎ! ወይ ጆሮዋን ወይ እግሯን መታሁ በል እንጂ ትዋሻለህ አሉት፡፡ አልዋሸሁም ሚዳቆዋ ስታክ ነው ያገኘኋት ብሎ መለሰ ይባላል፡፡ ወደ ጀመርነው መድበለ ፓርቲ ልመልሳችሁና መድበለ ፓርቲ አይሠራም የሚለውን ላብራራ፡፡ የፖለቲካ ድርጅቶች የፖለቲካ ሥልጣንን ለመያዝ ከያሉበት ወደ ኢትዮጵያ በሚጎርፉበት ጊዜ መድበለ ፓርቲ አይሠራም ስል አስደነገጥኩ መሰለኝ አይዟችሁ! መድበለ ፓርቲ ይሠራል በምልበት ጊዜ እክሳለሁ፡፡ አይሠራም ላስረዳ፣ ኅብረተሰብ ተጨባጭ ነው፡፡

በአጠቃላይ ኅብረተሰብ የሚባል ነገር የለም፡፡ የምናወራው ስለአሜሪካ ኅብረተሰብ አይደለም፡፡ የምናወራው ስለአውሮፓ ኅብረተሰብ አይደለም፡፡ የምናወራው ከዝቅተኛ ሥልተ ምርት ወደ ከፍተኛ ሥልተ ምርት በመሸጋገር ላይ ስለምትገኝ ኢትዮጵያ ኅብረተሰብ  ነው፡፡ የምናወራው ከፊውዳሊዝም ድሮ ወደ ሶሻሊዝም ዛሬ ወደ ካፒታሊዝም በመሸጋገር ላይ ስለነበረችውና ስላለችው ኢትዮጵያ ነው፡፡ የምናወራው መደቦች ቅርፅ ያልያዙበት አንዱ አንዱን አሸንፎ ያልወጣበት፣ ወላዋይ ንዑስ ከበርቴው ምሁር እንደ ልማዱ ከማን ጋር ብሆን የበለጠ ተጠቃሚ እሆናለሁ ብሎ ስለሚያሰላስልበት ኢትዮጵያ ነው የምናወራው፡፡ ሕዝባችን በድንቁርና ተሸብቦ የዚህ ጨዋ ሕዝብ ዕጣ ፈንታው ተማርኩ በሚሉ ጥቂት ወልጋዳ ምሁራን ስለሚወሰንበት ኢትዮጵያ ነው ምናወራው፡፡ ይኼንን ካልተገነዘብን ያው እንደለመድነው ላላላ! ታታታImage removed. Image removed. እንጂ ፖለቲካ ስለማይሆን መግባባት አንችልም፡፡

አገሬ ‹ኢትዮጵያ አገሬ ተራራሽ አየሩ. . .› አዎ አገራችን ኢትዮጵያ ግን ምን ዓይነት አገር ነች? የፍልስፍና መጀመሪያ አገርን ማወቅ ነው፡፡ ፈረንጆች ሦስተኛ ዓለም፣ ተሻጋሪ ኅብረተሰብ፣ ታዳጊ አገር፣ በኢኮኖሚ ወደ ኋላ የቀረች አገር ብለው ይጠሯታል፡፡ ወደ ኋላ የቀረች አገር የሚባለው አባባል ይስማማኛል፣ ግን በጣም እያዘንኩ፡፡ ኢትዮጵያ በጣም ወደ ኋላ ከቀሩት የዓለም አገሮች አንዷ ናት፡፡ ግን ይህም ሆኖ ኋላ ቀርነታችንን በፉከራ የምናስቀር ይመስል አሁን ስላለንበት አስከፊ ሁኔታ ከማውራት ይልቅ፣ ስለአክሱም ሥልጣኔ ትልቅነት ማውራት እንወዳለን፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን እንደዚህ ነበርን ብለን ማውራት እንወዳለን ልበል! ይሁንና ምሥለ ኋላ ቀርነታችንን ስናወራ ኢትዮጵያ የብዙ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚ አገር መሆኗን መረዳቱ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ የኋላ ቀርነት ዋነኛው ምልክት ነው፡፡ ይህ ኋላ ቀርነት በአኗኗራችን፣ በአበላላችን፣ በአለባበሳችን፣ በፖለቲካ አደረጃጀታችን ወዘተ. መግለጽ ይቻላል፡፡ የፖለቲካ ባህላችን ኋላ ቀር መሆኑና በብሔር መደራጀታችን ብቻ ማንሳቱ በቂ ማስረጃ ነው፡፡ ኋላ ቀር የኢኮኖሚ በዘርፎች ኋላ ቀር መንግሥትን ኋላ ቀር የፖለቲካ ድርጅቶችንና ደቃቃ ምሁሮችን ይወልዳል፡፡

ያደገ ኢኮኖሚ፣ ያደገ መንግሥትን፣ ያደገ መዋቅርን፣ ያደገ የፖለቲካ ድርጅቶችንና የበሰሉ ምሁሮችን ይወልዳል፡፡ መድበለ ፓርቲ ያደጉ የኢንዱስትሪ አገሮች የፖለቲካ መዋቅር ነው ብለናል፡፡ ታዲያ ሲሉ ሰማሁ ወይም ግልበጣ ካልሆነ በስተቀር፣ ምንም ሳይመረመር መድበለ ፓርቲ በኢትዮጵያ ላይ መጫን ይቻላል? ፎቶ ኮፒ ኦርጅናል አይሆንም፡፡ በእርግጥ ሥልጣኔን ከሥልጣኔ ከአንዱ አገር ወደ ሌላ አገር ማጠጋጋትና መማር ይቻላል፡፡ ግን በቅድሚያ ኢትዮጵያን ማወቅ ግድ ይላል፡፡

ከብሔር ቀፎና ከጎጠኝነት ሳይወጡ ድንቄም መድበለ ፓርቲ፣ ድንቄም ተፎካካሪ ድርጅት፣ ድንቄም ኢትዮጵያን መውደድ፡፡ ይሁንና የዛሬ የፖለቲካ ድርጅቶች ኢትዮጵያ ውስጥ መብዛት ነባራዊ ነው፡፡ ከእኛ አስተሳሰብና ፍላጎት የወጣ ዕድገት የፈጠረው ችግር ነው፡፡ ለምን ድርጅቶች በዙ ብላችሁ ፀጉራችሁን ደጋግማችሁ እከኩ መብዛታቸው አይቀርም፡፡ ልጓም ያስፈልግ ይሆን? የድርጅቶችን መብትና ነፃነት ሳናከብር ስለግለሰብ ነፃነትና ዴሞክራሲ ማውራት አንችልም፡፡ ታዲያ ምን ይሆን መውጫው? ምን ይሆን መፍትሔው? ዶክተሮች አድኑን እንጂ! ሊቆች ስንት አሉን? በሚቀጥለው ጽሑፍ ጠብቁኝ አመሠግናለሁ፡፡

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለጽን፣ በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡