Skip to main content
x

የዳያስፖራ ተሳትፎና የድርብ ዜግነት ጥያቄ በኢትዮጵያ

አየናቸው አሰፋ ወልደ ጊዮርጊስ

ጠቅላይ ሚኒስብይ አሜሪካን በጎበኙበት ወቅት መነጋገሪያ ሆነው ከነበሩ አንኳር ጉዳዮች አንዱ የድርብ ዜግነት ጥያቄ ነበር፡፡ በርካቶች የውጭ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያን ዜግነት በተደራቢነት ማግኘት የሚያስችል የግ ማሻሻያ ያስፈልጋል ትውልደ ኢትዮጵያውያኑና ልጆቻቸው ሙሉ የኢትዮጵያ የዜግነት መብቶችና ጥቅሞችን ሊያገኙ ይገባል ሲሉ ይህም አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሁሉን አቀፍና አካታች የሆነ የፖለቲካ ከባቢን ለመፍጠርና ‹‹ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት›› የሚል መሪ ሳብ እያራመዱ እንደ መሆኑ ትክክለኛው ዜ አሁን ነው ሲሉም ተሟግተዋል፡፡ ነገር ግን ይንን ሳብ የተቃወሙትም ነበሩ፡፡ ክርክሩም በማበራዊና ሌሎች መገናኛዎች ላይ ደምቆ ሰንብቷል፡፡

በቅርቡ ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ቃል አቀባይ ሆነው የተሾሙት ግለሰብ የካናዳ ዜግነት ያላቸው መሆኑ በተሰማ ጊዜ ይኸው የድርብ ዜግነት ጉዳይ በድጋሚ መነጋገሪያ ሊሆን ችሏል። የቃል አቀባይዋ የዜግነት ጉዳይ ከተገቢ ነው አይደለም ጥያቄ አልፎ ግ ክርክርም አስነስቷል፡፡ የክርክሩ መነሻ በ1994 ዓ.. የወጣው የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎችን የተመለከተው አዋጅ ቁጥር 270 ሲሆን አዋጁ በአንቀጽ ስድስት ላይ እንዳስቀመጠው የውጭ ገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሁለት ይነት ገደቦች አሉባቸው፡፡ እነዚህም

1ኛ) በማንኛውም የመንግት ደረጃ የሚካሄድ ምርጫ ላይ መምረጥና መመረጥ ያለመቻላቸው

2ኛ) በማንኛውም የገር መከላከያ፣ የገር ደንነት ወይም በውጭ ጉዳይ መሰል የፖለቲካ የመንግት መሪያ ቤቶች በመደበኛነት ተቀጥረው መራት የማይችሉ መሆኑ ነው።

እንግዲህ አንዳንዶች እንደሚሉት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽፈት ቤት ቃል አቀባይነት በፌራል መንግቱ መዋቅር ላይ ከወደ አናቱ የተጠጋ በመሆኑና የራ ድርሻውም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ለራሳቸውም ሆነ ለታዊ ራዎቻቸው እጅግ ቅርብ በመሆኑ የፖለቲካ የመንግት መሪያ ቤቶች በሚለው የአዋጁ ፍረጃ ውስጥ የሚያርፍ ነው። ስለሆነም ሹመቱ ገወጥ ብቻ ሳይሆንለወደፊቱም አደገኛ ምሳሌያዊነት ያለው ነው፡፡ ሌሎች ግን ግለሰቧ ለቦታው የሚመጥን ብቃትና የራ ፍላጎት እስካላቸው ድረስ የሌላ ገር ፓስፖርት መያዛቸው ዋናው ጉዳይ አይደለምየድርብ ዜግነት መፈቀድም ለወደፊት ንን መሰሉን ችግር ይፈታል በማለት ይከራከራሉ።

የክርክሩ አንኳር ጉዳይ  

ርግጥ የድርብ ዜግነት ጉይ የሚያከራክረው በኢትዮጵያ ብቻ አይደለም። ለብዙ አርት መታት የበርካታ አገሮች ያስፖራ ማበረሰቦች በትውልድ ገራቸው የድርብ ዜግነትና የመምረጥ መመረጥ መብትን ለማግኘት ሲሟገቱ ኖረዋል የተሳካላቸው ጥቂቶች ብቻ ቢሆኑም። አንዳንድ አገሮች ድርብ ዜግነትን ይፈቅዳሉ፡፡ ነገር ግን ብዙዎቹ ከደንነት ከወታደራዊና ከፍተኛ ፖለቲካዊ ራዎች ጋር የተያያዙ ገደቦች ያስቀምጣሉ። ሌሎ ተወሰኑ አገሮች ብቻ ይፈቅዳሉ (ለምሳሌ ስፔን የቀድሞ ቅኝ ግዛቶቿ ከነበሩ የደቡብ አሜሪካ አገሮች ጋር ድርብ ዜግነትን ትፈቅዳለች) ሌሎች በርካታ አገሮች ግን ድርብ ዜግነትን ከናካቴውም አይፈቅዱም፡፡

ድርብ ዜግነትን በሚደግፉ የኢትዮጵያ ያስፖራ አባላት ተዘውትሮ የሚቀርበው መከራከሪያ ያስፖራው በገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን ወሳኝ ሚና ታሳቢ ያደረገና ባለ ሁለት ፈርጅ ነው። በአንድ በኩል የድርብ ዜግነት መፈቀድ በበለጠ የባለቤትነት ስሜት የኢኮኖሚ ተሳትፎአችንን እንድናጠናክር ያስችለናል የሚል ነው። ይሁን እንጂ ቀደም ሲል የተጠቀሰው አዋጅ ቁጥር 270|1994 እንደሚያስቀምጠው ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ለገር ውስጥ ባለብቶች የተፈቀዱ የራ መስኮች ላይ መሳተፍ ይችላሉ። እንዲያውም ለትውልደ ኢትዮጵያውያን የተሰጡ የንግድና የኢኮኖሚ ተሳትፎን የተመለከቱ መብቶችና ማበረታቻዎች ለገሬው ነዋሪ ባለብት የሚያስጎመጁ ጭምር ናቸው። በርግጥ ባለፉት መታት እነዚህ መብቶችና የማረታቻ ጥቅማ ጥቅሞች በተለያዩ መመያዎች፣ በፖለቲካ ውሳኔዎችና ብልሹ አራሮች የተነሳ ሲሸረሸሩ ኖረዋል። ይሁን እንጂ ጉ በአግባቡ ከተተገበረ (ምልባትም ከአስፈላጊ ማሻሻያዎች ጋር) ድርብ ዜግነት የያስፖራውን የተሻለ ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ያረጋግጣል የሚለውን መከራከሪያ ያመክነዋል።

ሌላኛው መከራከሪያ ያስፖራው ከኢኮኖሚያዊ አስተዋፅኦው ተመጣጣኝ የሆነ የፖለቲካ ተሳትፎ እንዲኖረው ድርብ ዜግነት ይነተኛው መንገድ ነው የሚለው ነው። ይሁን እንጂ ባለፉት አርት መታት የኢትዮጵያ ያስፖራ በጥሩም ሆነ በመጥፎ ገሪቱ ፖለቲካ ላይ ያለው አስተዋፅኦ እጅግ የጎላ ነው። ከማበራዊ መገናኛ ዘመቻ እስከ ትጥቅ ትግል፣ ከላማዊ ልፍ እስከ ኢኮኖሚያዊ ተአቅቦ፣ ከዲፕሎማሲያዊ ተፅዕዝባዊ እምቢተኝነትን እስከ መምራት ወዘተ ያስፖራው በተለያዩ የፖለቲካ ጎራዎች በመሳተፍ ገሪቱ ዛሬ ላለችበት ሁኔታ የራሱን ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ይህ የሚያሳየው የድርብ ዜግነት መፈቀድ ወይም መከልከል ፖራውን ከፖለቲካ ተሳትፎ ያላገደው መሆኑን ነው። እርግጥ ነው አሁን ካለንት አገራዊ ሁኔታ አንፃርና ወደፊት ግልጽና አሳታፊ የፖለቲካና ማበራዊ ት ለመገንባት ካለን ተስፋ አኳያያስፖራውን ተሳትፎ መደበኛና ጋዊ መረት የያዘ ለማድረግ የሰከነ ውይይት ማድረግ ይግባል። በዚህ ውይይት ውስጥ ታዲያ እንደ ጥቅሞቹ ሁሉ ድርብ ዜግነት ሊያስከትል የሚያስችላቸውን ጋቶች ማንሳቱ ተገቢ ነው።

የመጀመያው የታማኝነት ጥያቄ ሲሆን አንድ ሰው የሁለት አገሮች ዜግነት ሲኖረው ወገንተኝነቱ ለሁለት አገሮች ይሆናል። ሁለት አገሮችን ሊያገለግል፣ ሊጠብቅ፣ ጥቅም ሊያስከብር፣ ወዘተ ቃል ይገባል። ምልባት ይህ ‹‹ለሁለት ጌታ መገዛት›› ጉዳይ በለት ተዕለት ኑሮ ውስጥ አንገብጋቢ ላይሆን ይችላል በመርህ ደረጃ ግን የራሱ አደጋዎች አሉት፡፡

ሁለተኛ ድርብ ዜግነት በብዙ ሺ ማይሎች ርቅው ለሚኖሩ ዜጎች በገሪቱ የፖለቲካ ደት ውስጥ በቀጥታ እንዲሳተፉ ድል ይሰጣል፡፡ ነገር ግን በዚህ መንገድ የሚሳተፉበትን የፖለቲካ ከባቢ እንዲኖሩበት አይጠበቅባቸውም አይገደዱምም። ይህም ባለፉት በርካታ መታት በያስፖራው የፖለቲካ ተሳትፎ ላይ አዘውትሮ  የሚሰነዘረውን ትችት የሚመስል ነው። የያስፖራ ፖለቲከኞች ካሉበት ሆነው ገሪቱ ላይ ተቃውሞ ሲያስተባብሩ ተቃውሞውን ለማክሸፍ የመንግይሎች የሚወስዱት ርምጃ ግን እነሱን የሚነካ አልነበረም። ይህም የበዛ ትችትና የሞራል ጥያቄን ሲያስነሳ ቆይቷል።

ስተኛ የድርብ ዜግነት ባለቤቶችን በቁልፍ የፖለቲካና መንግታዊ አስተዳደር ቦታዎች እንዲሩ መፍራዊ ደንነትን ጋት ላይ ሊጥል የሚችል መሆኑ ነው። በአንድ በኩል እነዚህ ግለሰቦች ለውፅዕኖ ያላቸውን ተጋላጭነት ብንተወው እንኳን እንዲህ ያለው ግ ክፉ ሳብ ያላቸው ግለሰቦች በአገሪቱ የደንነትና ወታደራዊ ተቋማት ሰርገው በመግባት ለሁለተኛው ገራቸው ጥቅም መራት እንዲችሉ ድል ይፈጥራል፡፡ በተለይም ይ ኢትዮጵያ ካለችት አካባቢያዊ ሁኔታና ከገሪቷ ጋር ተፃራሪ የሆነ ፍላጎት ሊኖራችው ከሚችል ጎረቤት አገሮች ወይም ቡድኖች ረገድ ከታየ የበለጠ አሳሳቢ ሊሆን ይችላል። በሌላ በኩል ድርብ ዜግነት በቸገረ ጊዜ እንደ ‹‹መውጫ መንገድ›› ተደጎ ሊታይም ይችላል። ሁለት ገር ያለው ባለልጣን የወሰነው ውሳኔ የተከተለው ፖሊሲ ውጤት እንደተጠበቀው ባይሆን ከኪሳራው ተጋሪ የመሆን ግዴታ አይኖርበትም። እናም ቢያዋጣ ያዋጣ ባይሆን ይቀራል ከሚል ይነት ግዴለሽነት ነፃ መሆኑን እንዴት ማወቅ ይቻላል? በዚህ ሁኔታ እውነተኛ ተጠያቂነት ሊኖርስ ይችላል ወይ?

አራተ እንዲህ ያለው ሹመት በራ አካባቢ ላይ የሚፈጥው ሽኩቻና ፉክክር እንዳለ ሆኖ እነዚህ ግለሰቦች በሌላኛው ገራቸው ያላቸውን ንብረት፣ የባንክ አካውንት፣ ኢንቨስትመንት፣ ወዘተ አጥርቶ ለማወቅ አዳጋች ከመሆኑ አኳያ ሙስናንና የገርን ብት ድብቅ ፍሰት ለመቆጣጠር እጅግ አዳጋች ይሆናል።

በመጨረሻም እነዚህ ነጥቦች ከገሪቱ የፖለቲካ ነባራዊ ሁኔታ አኳያ በቋፍ ካለው የፖለቲካና ቢሮክራሲ ነፃነት አንፃር መታየት አለበት። እንዲሁም እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ሁሉ በንድፈ ሳብ ደረጃ የቀረቡ እንጂ ሁሉም ትውልደ ኢትዮጵያውያን የነዚህ ችግሮች ምንጭ ይሆናሉ ማለት አይደለም። እንዲሁም ማንም አንድ ግለሰብ ወይም ቡድን ላይ ያነጣጠረም አይደለም።

አማራጭ መንገድ

በኢኮኖሚ አስተዋድኦዋችን መጠን ድም ሊኖረን ይገባል የሚለው የያስፖራው ጥያቄ ተገቢነት ያለው ነው። ብዙዎቹ እንሚሉት ዜግነታቸውን የሚቀይሩት ለራሳቸው ወይም ለቤተሰባቸው ካለው ተግባራዊ ጥቅም አኳያ ወይም ከሚደርስባቸው ፖለቲካዊ አፈና የተነሳ እንጂ ኢትዮጵያዊነታቸውን መተው ምርጫቸው ሆኖ አይደለም። ኢትዮጵያዊ ፓስፖርት እንጂ ልቡን አይቀይርም እንሚሉት ብዙዎቹ። በርግጥም ቤተሰቦቻቸውን፣ ዘመዶቻቸውንኞቻቸውን ቤት ንብረታቸውን የያዘች ገር ፈንታ ቢያሳስባቸው ጥሪታቸውን የሚያፈሱባት የተወለዱባት ያደጉባት ገር የወደፊት ፈንታ ላይ ድርሻ ይኑረኝ ማለታቸው እውነት አለው።

እንዲህ ያለው ተሳትፎ ሊረጋገጥ የሚችልበት አንዱ መንገድ በገሪቱ መንግት ውስጥ ያስፖራው ተወካይ እንዲኖው ማድረግ ነው። ከድርብ ዜግነት ወይም ቀጥተኛ ከሆነ የፖለቲካ ተሳትፎ ይልቅ ያስፖራው በተለያዩ የመንግት አካላት ውስጥ በግ አውጪው ወይም በአስፈሚው ውክልና እንዲኖረው ማድረግ ይቻላል። በርካታ አገሮችያስፖራ ጉዳይን በሚኒስቴር መሪያ ቤት ደረጃ ያደራጃሉ። ይህ ችግሮችን ሁሉ የሚፈታ ባይሆንምራ አስፈሚው ውስጥ የያስፖራው ጉዳይ በከፍተኛ ደረጃ እንዲወከል ያስችላል። ይህም በአወቃቀሩ ሚኒስትር መሪያ ቤቱ ከያስፖራው ተወካዮች ጋር ተጣምሮና ተጣጥሞ እንዲራ ከተደረገ የበለጠ ውጤት ያመጣል። ሌላኛው አማራጭ በከፍተኛ ደረጃ በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ የያስፖራ ጉዳዮችን የሚከታተልና ከያስፖራው የተውጣጡ አባላትን ያካተተ አማካሪ የራ ቡድን ማደራጀት ይሆናል።

የዳያስፖራ አባላት በግ አውጭው ውስጥ ውክልና እንዲኖራቸው ማድረግም ሌላው መንገድ ነው። እ.ኤ.አ. በ2010 በተደረገ ጥናት በለም ዙሪያ አራ አንድ አገሮች በፓርላማዎቻቸው ውስጥ ለያስፖራ ተብሎ የተያዙ መቀመጫዎች ነበሯቸው። እንዲህ ያለው ውክልና ከፌራል መንግቱ በታች ባሉ መዋቅሮችም ጭምር ሊታነ ይችላል። በርግጥ እነዚህ አማራጭ ሳቦች አስፈላጊው የግ ማሻሻያ ካልተካተተባቸው ፍሬያማ መሆናቸው ጥያቄ እንደሆነ መቅረቱ አያጠራጥርም።

ከሁሉም በላይ አንዳንድ አወዛጋቢ የሆኑ የግለሰብ ጉዳዮች እየተነሱ እንደ መሆኑቀጣዩ ምርጫም ከመት ከግማሽ ያልበለጠ ጊዜ የቀረው በመሆኑ ዚህ ጥያቄ ላይ እልባት ማድረጉ ተገቢ ነው። የውጭ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ እንደ ማንኛውም ዜጋ ያለ ገደብ ይሳተፉ የሚለውም ሆነ የለም ከነአካቴው ምንም ይነት ተሳትፎ ሊፈቀድላቸው አይገባም የሚሉት ሁለ ሳቦች እኩል እንከን ያለባቸው ናቸው። ከሁለቱ መካከል የሆነ አማካይ መፍት መሻት ይበጃል ይቻላልም።

ሌላው ሁሉ ቢቀር በገሪቱ ፖለቲካ በቀጥታ ለመሳተፍ የሚመርጡ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአዋጅ 378/1996 መረት የኢትዮጵያዊነት ዜግነታቸውን መልሰው ማግኘት ይችላሉ። ንን ለማድረግ የሚጠየቁት ሁለት ቅድመ ሁኔታዎችን ብቻ ነው። እነሱም የሌላኛውን ገር ዜግነታቸውን መተውና በቋሚነት መደበኛ መኖሪያቸውን በኢትዮጵያ መመረት፡፡

  ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለጽን፣ በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡