Skip to main content
x

የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ድርጅት ኃላፊዎች ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት ማድረስ ክስ ቀረበባቸው፡፡

ከባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ድርጅት በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ ኃላፊዎች ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት ማድረስ ክስ ቀረበባቸው፡፡ ክሱ የቀረባባቸው ከመርከብ፣ የጭነት መኪናዎችና ከኮንቴይነሮች ግዥዎች ጋር በተያያዘ ነው፡፡

ተከሳሾቹ አቶ መስፍን ተፈራ፣ አቶ ሲሳይ አባፈርዳ፣ አቶ ሲራጅ አብዱላሂ፣ አቶ ደሳለኝ ገብረ ሕይወት፣ አቶ ተናገር ይስማው፣ ቺፍ ኢንጂነር አለሙ አምባዬና አቶ ሳሙኤል መላኩ ናቸው፡፡

አቶ መስፍንና አቶ ሲሳይ ከተሸከርካሪዎች ግዥ ጋር በተገናኘ ከ7.5 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ፣ አቶ ሲራጅ  ደግሞ ከመርከቦች ግዢ ጋር በተገናኘ ከ12 ሚሊዮን የጅቡቲ ፍራንክ በላይ ጉዳት በማድረስ የተከሰሱ ሲሆን፣ ቺፍ ኢንጂነር አለሙ ከኮንቴይነር ግዥ ጋር በተገናኘ ከ65 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡

እስካሁን ያልተያዙ ነገር ግን ክስ የቀረበባቸውን አቶ ሰሎሞን ለገሠንና አቶ ተስፋዬ አማረን የፌዴራል ፖሊስ ይዞ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብት ስለማያሰጣቸው እስር ቤት እንዲቆዩ በመወሰን ለኅዳር 15 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡