Skip to main content
x

‹‹ቆንጆዎቹ!›› ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ገና አልተወለዱም

 በአገራችን ኢትዮጵያ በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የኅትመት ብርሃን የሚያገኙ መጻሕፍት ቁጥር እያሻቀበ የሚገኝ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎ በይዘታቸው በከፍተኛ ደረጃ የተዋጣላቸው ጥቂት መጻሕፍትም በኅትመት ገበያው ላይ መታየት ጀምረዋል፡፡ ለዚህም እንደ ማሳያ የሚሆነው ዓምና በሆሄ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት በረዥም ልብወለድ ዘርፍ ከታጩት አምስት መጻሕፍት አንዱ የሆነውና ብዙም ያልተወራለት ወሰብሳቤ አንዱ የነበረ ሲሆን፣ የመጽሐፉም ደራሲ ያለው አክሊሉ ነው፡፡

ብሔራዊ የትምባሆ ድርጅት ከመንግሥት እጅ መውጣቱ የሚያስከትለው ሥጋት

መንግሥት በቅርቡ በብሔራዊ የትምባሆ ድርጅት ውስጥ ያለውን ወደ 31 በመቶ የሚጠጋ የባለቤትነት ድርሻን ለጃፓን ዓለም አቀፍ የትምባሆ ድርጅት (ጄቲአይ) በመሸጥ ከትምባሆ ንግድ ውስጥ ለመውጣት የወሰደው ውሳኔ በመልካም ጎን የሚታይ ነው፡፡ በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሰዎች ሕይወትን እየቀጠፈ ያለውን የትምባሆ ምርት መንግሥት ለራሱ ዜጎች እንዳያመርትና እንዳይሸጥ የሞራል ኃላፊነት አለበት፡፡ ይህ ውሳኔ አገሪቱ እ.ኤ.አ. በ2014 በአዋጅ ያፀደቀችውን የዓለም የጤና ድርጅት የትምባሆ ቁጥጥር ማዕቀፍ ስምምነት ሙሉ ለሙሉ ለማስፈጸምም ይረዳል፡፡

ወደ ሞት እየተገፋ ያለው ዝዋይ ሐይቅ

 የምሥራቅ ኢትዮጵያ ሲሳይ መሆን ይችል የነበረው ሐረማያ ሐይቅ አብዛኛው ክፍል ደርቆ የከብቶች መሰማርያ መስክ እስከመሆን ደርሶ ነበር፡፡ ተደረገለት በተባለ የአካባቢ ጥበቃ አገገመ ሲባልም ተሰማ ፡፡ይሁንም እንጂ ውኃው በሞተር እየተሳበ ጫት እየለማበት ነው፡፡ በዚህ ድርጊት እየተደጋገመ መሔድም ሐይቁ ጨርሶ  እንዳይደርቅ ያሠጋል፡፡

የ‹‹እናውቅልሃለን›› ፖለቲካዊ ፍልስፍና ከያ ትውልድ እስከ እኛ ትውልድ

‹‹የሕዝባችን ብሶትና የድሆች አሰቃቂ ሁኔታ እስከ አጥንታችን ድረስ ዘልቆ ተሰምቶናል›› ያሉን ‹‹ምርጥ የኢትዮጵያ ልጆች››፣ የ‹‹እናውቅልሃለን›› ፖለቲካዊ ፍልስፍና ማራመድ ከጀመሩ እነሆ 44 ዓመት አስቆጠሩ። ከዚያ ጊዜ ወዲህ የ‹‹እናውቅልሃለን›› ፖለቲካዊ ፍልስፍና በአገራችን ባህል ሆኖ ቆይቷል።

ትውልድን የመታደግ አደራና የገባንበት አጣብቂኝ

ለዛሬ አሁን ያለውን ትውልድ ስኬት በማንሳት ላሰለቻችሁ አልሻም፡፡ ይልቁንም እንደ አገር በማኅበረሰቡ በተለይም በወጣቱ ትውልድ ላይ የተደቀኑ ፈተናዎችን መንቀሴን መርጫለሁ፡፡ ከዚያም አልፎ የወደፊቷ ኢትዮጵያ እንደ መርግ ሊጫናት ያረበበውን አስከፊ ሁኔታ ሁሉ በማንሳት የመነጋገሪያ አጀንዳ ለመሰንዘር እሞክራለሁ፡፡

ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ከኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ጉባዔ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊውን የኢትዮጵያ ሁኔታ አስመልክቶ ታኅሣሥ 12 ቀን 2010 ዓ.ም. በካቶሊካውያን ጳጳሳት ጉባዔ አማካይነት መግለጫ አውጥታለች፡፡ መግለጫውን ብፁዕ እምብፁዓን ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን ከመንበራቸው አቅርበውታል፡፡ ሙሉ ይዘቱ የሚከተለው ነው፡፡  

የኢንዱስትሪ - ዩኒቨርሲቲ ትስስር ለሰው ኃይል ልማት

ያደጉ አገሮች ለማደጋቸው ዋናው ምስጢር ኢንዱስትሪያላይዜሽንን በአገራቸው ተግባራዊ በማድረጋቸው እንደሆነ ምሁራን ይናገራሉ፡፡ ለዘርፉ ማደግ ደግሞ አዳዲስ ቴክኖሎጂና በሙያው ብቁ የሆነ የሰው ኃይል መኖር የአንበሳውን ድርሻ ይይዛሉ፡፡ አገራችንም ወደ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ለመሰለፍ ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ለመሸጋገር በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ ትገኛለች፡፡

ማኅበራዊ ንቅዘትን የተፋለመው ወጣት

በሰለሞን ኃይለማርያም ‹‹ዘ ያንግ ክሩሴደር›› በሚል ርዕስ (ተዛማጅ ትርጉም ማኅበራዊ ንቅዘትን በወኔ የተፋለመው ወጣት) በእንግሊዝኛ ተደርሶ በ2003 ዓ.ም. በኮድ ኢትዮጵያ ለኅትመት የበቃው መጽሐፍ በጀርመንኛ ተተርጉሞ ባለፈው ጥቅምት ወር  ለጀርመንኛ አንባቢዎች ቀርቧል፡፡ ምንም እንኳን መጽሐፉ ከሰባተኛ ክፍል በላይ የሚገኙ እንግሊዝኛ አንብበው ለመረዳት የሚችሉ ታዳጊ ወጣቶችና ወጣቶች ትምህርታዊ ቢሆንም፣ ከአማርኛ በፊት ጠቃሚነቱ ታውቆ ወደ ጀርመንኛ መተርጎሙ የሚያስገርም ነው፡፡

ትምህርት ዓይነ ስውርነቴን ወደ በጎ አጋጣሚ የቀየረልኝ ቁልፍ ነው

የአምስት ዓመት ልጅ ሆኜ ነበር ዓይነ ስውር የሆንኩት፡፡ ለቤተሰቦቼ እጅግ አስደንጋጭ ሁኔታ ነበር፡፡ በተለይም ደግሞ ባደግኩበት ገጠራማ መንደር የነበረው  ድንጋጤ ከባድ ነበር፤ ምክንያቱም በዚያች መንደር ዓይነ ስውር ለመሆኔ ሰበቡ የእግዜር ዕጣ ወይም ደግሞ አንዳች እርግማን እንደነበር ነው የታመነው፡፡