Skip to main content
x

ለአገራዊ መግባባት የፀረ ማሰቃየት (ቶርቸር) ሕግ አስፈላጊነት

ከ1966 ዓ.ም. ጀምሮ በምርመራ ሰበብ እጅግ በርካታ እስረኞች የሚሰቃዩበት ‘ማዕከላዊ’ በመባል የሚታወቀው ማረፊያ ቤት ተዘግቶ ሙዚየም እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ይፋ አድርገዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳያቸው በመታየት ላይ ያሉ ተከሳሾች የተለያዩ ድብደባና ሌሎች ኢሰብዓዊ ድርጊቶች እንደተፈጸሙባቸው ለችሎቱ ጉዳት የደረሰበትን አካላቸውን ጭምር እያሳዩ እንደሆነ በተለያዩ ሚዲያዎች ተዘግቧል፡፡

የምሕረት አደራረግ ሕጉና ዓላማው ሲገለጥ

የኢሕአዴግ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከአባል ድርጅቶቹ ሊቃነ መናብርት ጋር በመሆን የግንባሩ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለ17 ቀናት ያደረገውን ግምገማ መሠረት በማድረግ ማብራሪያና መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫውም፣ የተሻለ አገራዊ መግባባት ለመፍጠርና የዴሞክራሲ ምኅዳሩን ለማስፋት በጥፋታቸው ምክንያት ጉዳያቸው በዓቃቤ ሕግ ተይዞ በእስር የሚገኙም ሆኑ የተፈረደባቸው አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትናና ግለሰቦች ክሳቸው እንደሚቋረጥ ወይም ምሕረት እንደሚደረግላቸው አስታውቀዋል፡፡

የመተማመኛ ድምፅ መስጠትና መንፈግ ሕጋዊነትን ለማስፈን

ገዥው ፓርቲ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከሁለት ሳምንታት በላይ የፈጀ ስብሰባ በማድረግ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ በዚህም መሠረት ፓርቲው ራሱ በተለይም ሥራ አስፈጻሚው የፈጸማቸውን ስህተቶች አምኖ ምን ማድረግ እንዳለበትም በተከታታይ በመግለጽ ላይ ይገኛል፡፡

በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ አጋርነት ረቂቅ አዋጅ ላይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ2009 ዓ.ም. መደበኛ የሥራ ዘመኑን ከማጠናቀቁ በፊት ከሚኒስትሮች ምክር ቤት በመቀበል ወደ ቋሚ ኮሚቴዎች ከመራቸው ረቀቂ አዋጆች አንዱ የመንግሥትና የግሉን ዘርፍ አጋርነትን (Public Private Partnership) የሚመለከተው ነው፡፡

ሕጉን መሙላት ያልቻሉት የማሟያ ምርጫዎች

በተለያዩ እርከን ላይ የሚገኙ የሕዝብ ምክር ቤቶች አባላታቸው በሚጓደሉባቸው ጊዜያት የማሟያ ምርጫ እንዲደረግ ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ አሁን በሥራ ላይ ያለውን የፌዴራሉን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በምሳሌነት ብንወስድ እንኳን ቢያንስ ሁለት አባላቱ እንደሞቱ ይታወቃል፡፡ አንዱ ከአዲስ አበባ፣ ሌላዋ ደግሞ ከአማራ ክልል የተወከሉ፡፡ ይሁን እንጂ በአሠራሩ ላይ የሁለት ድምፅ መጉደል ልዩነት እንደማያመጣበት በመገመትም ይሁን በሌላ ምክንያት የማሟያ ምርጫ አልተደረገም፡፡

ለሕገ መንግሥት ሕልውና የሕገ መንግሥታዊ ማሻሻያ ሚና

የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት የፀደቀበትን 23ኛ ዓመት የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በማክበር በአፋር ክልል ዋና ከተማ በሆነችው በሰመራ ባለፈው ዓርብ ኅዳር 29 ቀን 2010 ዓ.ም. ተከብሯል፡፡ በ1987 በኅዳር ወር ፀድቆ በዚያው ዓመት በነሐሴ ወር ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡

ስለዳኝነት ሥልጣን የሰበር ውሳኔዎችና ፍትሕ የማግኘት መብት

የፍትሕ ተደራሽነት መብት የሚያጠነጥነው ፍትሕ በሚፈልገው ሰው ዙርያ ነው፡፡ የፍትሕ ተደራሽነት ሲባል አንድ ነጠላ የፍትሕ ዘሃ ላይ ብቻ ሙጥኝ ያለም አይደለም፡፡ ይልቁንም ፍትሕ የሚፈልገው ሰው መብቱን በማስከበር ረገድ ተገቢ የሆነ እልባት ለማግኘት የሚከተለውን ሥርዓትና ሒደት በሙሉ ያካልላል፡፡

የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ውሳኔዎች ሕጋዊነታቸውና ሕገ መንግሥታዊነታቸው ሲፈተሹ

መኖሩ ጭምር በአብዛኛው ሕዝብ ዘንድ ሊባል በሚችል መልኩ በቅርቡ የታወቀውና የተለያዩ ውሳኔዎች ያሳለፈው ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት በብዙ ሰዎች ዘንድ ግርታን ፈጥሯል፡፡ ይህንን ግርታ ያስከተለው ምክር ቤት ሕጋዊ መሠረት ምን እንደሆነ መቃኘት እንዲሁም ያስተላለፋቸው ውሳኔዎች ከሕገ መንግሥቱ ጋር የመስማማት ወይም አለመስማማታቸውን መፈተሽ የዚህ ጹሑፍ ትኩረት ነው፡፡

ተለዋዋጩ የፌዴራል ድጎማ በፌዴራል ሥርዓቱ ላይ የሚኖረው አንድምታ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ላለፉት አምስት ዓመታት ሲጠቀምበት የነበረውን የፌዴራል መንግሥት ለክልሎች የሚሰጠውን ድጎማ የትኛው ክልል ምን ያህል ሊያገኝ እንደሚገባ ለመወሰን የሚረዳውን ቀመር እያሻሻለ መሆኑን ከመገናኛ ብዙኃን ሰምተናል፡፡ ቀመሩ በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ኮሚቴዎች እየተጠና ተከልሷል፡፡ የኮሚቴዎቹን የጥናት ውጤትም መሠረት በማድረግ ምክር ቤቱ የተለያዩ ቀመሮችን አጽድቋል፡፡