Skip to main content
x

ካስቴል የዘቢዳርን 40 በመቶ ድርሻ ለመግዛት ያቀረበውን ዋጋ ባለአክሲዮኖች አልተስማሙበትም

የዥማር ኩባንያ ባለአክሲዮኖች በዘቢዳር ቢራ ያላቸውን የ40 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ለካስቴል ግሩፕ (ቢጂአይ ኢትዮጵያ) ለመሸጥ ወሰኑ፡፡ ካስቴል ግሩፕ አክሲዮኖቻቸውን ለመግዛት ያቀረበላቸውን ዋጋ ግን እንደማይቀበሉ አስታወቁ፡፡ የዥማር ሁለገብ አክሲዮን ማኅበር አባላት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ባካሄዱት ስብሰባ ወቅት፣ በዘቢዳር ቢራ ውስጥ ለያዙት የአክሲዮን ድርሻ የቀረበላቸው ዋጋ ከሚጠብቁት በታች በመሆኑ፣ የሽያጭ ዋጋው እንዲሻሻልና ለዚህም ቦርዱ ከካስቴል ግሩፕ ጋር እንዲደራደር ውክልና ሰጥተዋል፡፡

ለንግዱ ኅብረተሰብ በአንዴ የቀረቡት 21 ረቂቅ የታክስ መመርያዎች

የኢትዮጵያ ገቢዎች ጉምሩክ ባለሥልጣንና የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር፣ ባልተለመደ አኳኋን 21 ረቂቅ መመርያዎችን በማሰናዳት ከንግዱ ኅብረተሰብ ጋር ምክክር አድርገዋል፡፡ ሰኔ 5 እና 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ውይይት ከተደረገባቸው ረቂቅ መመርያዎች መከካል 11ዱ በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር በኩል የቀረቡ ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ ረቂቅ መመርያዎችም በባለሥልጣኑ ለውይይት የቀረቡ ነበሩ፡፡

አንበሳ ጫማ በአፍሪካ አድናቆትን ካተረፉ ብራንዶች ተርታ በድጋሚ ሊመደብ ቻለ

ከተመሠረተ ከ80 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው አንበሳ ጫማ ፋብሪካ፣ በተጠቃሚዎች ምርጫ አማካይነት በሚሰጠው የብራንድ ደረጃ፣ ከአፍሪካ አድናቆትን ካተረፉ ትልልቅ ብራዶች ተርታ ዳግመኛ ውጤት ማግኘቱ ታወቀ፡፡

የፈረንሣይ ኩባንያ በ50 ሚሊዮን ዶላር 60 ሺሕ ቶን ብቅል የሚያመርት ፋብሪካ ለመትከል ተስማማ

ሱፍሌ የተባለው ታዋቂ የፈረንሣይ ኩባንያ በኢትዮጵያ 60 ሺሕ ቶን ብቅል የማምረት አቅም ያለው ፋብሪካ በ50 ሚሊዮን ዶላር ፋብሪካ ለመትከል የመሬት ሊዝ ስምምነት ፈረመ፡፡ ፋብሪካው በአንድ ዓመት ውስጥ ተገንብቶ ሥራ እንደሚጀምር ይጠበቃል፡፡ ማልቲየረስ ሱፍሌ ኩባንያ በገብስ፣ በስንዴና በጥራጥሬ እህሎች አምራችነት የሚታወቅ የቤተሰብ ኩባንያ ሲሆን፣ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የብቅል ፋብሪካ ለመገንባት የተስማማ ሁለተኛው የአውሮፓ ኩባንያ ሆኗል፡፡

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የአበል ማሻሻያ ረቂቅ አዘጋጅ

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች አፈጻጸምን የተመለከተውን መመርያ በማሻሻል፣ የትራንስፖርትና ሌሎች አበሎችን ክፍያ የሚያሻሽል ተጨማሪ ተፈጻሚ ድንጋጌዎችን ያካተተ ረቂቅ መመርያ አዘጋጀ፡፡ ሚኒስቴሩ በአዲሱ ረቂቅ መመርያ የትራንስፖርት አበልና የመጓጓዧ ወጪን በተመለከተ እንደጠቀሰው፣ ከግብር ነፃ እንዲሆን በቀድሞ ድንጋጌው ላይ የተጠቀሰውን የቀን ውሎ አበል ጣሪያ ከ225 ወደ 500 ብር ከፍ ተደርጓል፡፡

የብሔራዊ ባንክ ገዥና የፋይናንስ ተቋማት ኃላፊዎች በአዳዲስ አመራሮች ሊተኩ ነው

የኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማትን ሪፎርም ለማድረግ እየተደረጉ ባሉ እንቅስቃሴዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ኃላፊዎች በአዳዲስ አመራሮች ሊተኩ ነው፡፡ በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ ከኃላፊነታቸው እንደሚነሱ የተረጋገጠ ሲሆን፣ አሁን ባለው መረጃ እሳቸውን ለመተካት የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽነር ይናገር ደሴ (ዶ/ር) በዕጩነት ቀርበዋል፡፡

ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ግብር የሚፈለግበት ኪንግናም ንብረቱ ታገደ

በኢትዮጵያ የመንገድ ግንባታ ዘርፍ ለ20 ዓመታት ያህል ሲሳተፍ የቆየው ኪንግናም የተሰኘው የደቡብ ኮሪያ ኩባንያ፣ ለኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን መክፈል የነበረበትን ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ቀረጥና ግብር ባለመክፈሉ፣ የኩባንያው የተለያዩ ንብረቶች ታገዱ፡፡ ኮሪያዊው ሥራ አስኪያጅም ከአገር እንዳይወጡ ታዘዘ፡፡