Skip to main content
x
ጠቃሚዎቹ ወፎች

ጠቃሚዎቹ ወፎች

ከአዕዋፍ ዝርያዎች መካከል አንዳንዶቹ ለምግብነት ያገለግላሉ፡፡ ላባቸውም በዋነኝነት የሴቶችን ባርኔጣ ለማስዋብና ትራስ ለመሥራት ስለሚያገለግል በጣም ተፈላጊነት አለው፡፡ እነዚህም ማስዋቢያዎች የሚገኙት ከእዝዝ ወፎች፣ ሳቢሳዎች፣ ሸመላዎች፣ የገነት ወፎች፣ ተርን፣ ስዋን፣ ኮንዶር እና አልባትሮስ ነው፡፡ ይህም ተፈላጊነታቸው የወፎቹን ቁጥር ሲያመነምን ይታያል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚበሉ የአዕዋፍ ዝርያዎች ረጅም ርቀት መብረር የማይችሉት ናቸው፡፡ እነዚህም ጅግራ፣ ቆቅ፣ ቤት ዶሮዎች ናቸው፡፡ ሰጎን በረሃ ነዋሪ በመሆኗ በኢትዮጵያውያን ከመበላት ተርፋለች፡፡

  • ማንይንገረው ሸንቁጥ ‹‹ባለ አከርካሪዎች›› (2004)