Skip to main content
x

ቅርባችን ያለውን ሰላም ከሩቅ አንፈልግ!

ሰላም! ሰላም! በቀደም ዕለት እንዲያው ግራ ግብት ብሎኝ የሆድ የሆዴን የማጫውተው ሰው ብፈልግ አጣሁ። ምሁሩ የባሻዬ ልጅ ሥራ ሥራ እያለ ቀልቡ ከእሱ ጋር የለም። ባሻዬ የተጣላ ሲያስታርቁ፣ ቀብር ሲደርሱና ዕድሩን ሲመሩ ጊዜ አጡ።

ከአንጀት ወይስ ከአንገት?

ሰላም! ሰላም! ወከባና ሩጫው እንዴት ይዟችኋል? አንዳንዴ ሀሞት ያፈሳል አይደል? ይህች ዓለም ያለድካም አትሞከርም፡፡ ማለቴ ካልደከመው የሚበረታ፣ ካልታከተው የሚጠነክር ያለ አይመስልም።

አንድ ላይ እንድመቅ!

ሰላም! ሰላም! የተወደዳችሁ ኢትዮጵያዊያን! በያላችሁበት የፍቅር ሰላምታዬ ያለምንም የኔትወርክ መቆራረጥ ይድረሳችሁ፡፡ ቪትዝ 320 ሺሕ ብር ገባ እያላችሁ የተሳሳተ መረጃ የምትለቁ፣ ትዝብት ነው ትርፉ፡፡

አገሬ ኢትዮጵያ ሐዘንሽን ያቅልለው!

ሰላም! ሰላም! እንዴት ናችሁልኝ? ‹‹እንደርሳለን ብለን ከመሸ ተነስተን፣ ስንገሰግስ ነጋ ምንድነው የሚሻለን?›› አለችላችሁ አንዷ አዝማሪ። እውነቷን ነው እኮ! በዚህ አካሄዳችን እንኳን ልንደርስ የት እንደምንሄድም የምናውቅ አንመስልም፡፡

ከሚለያየን የሚያመሳስለን አይበልጥም?

ሰላም! ሰላም! እንደምን ከርማችኋል? እነሆ በናፍቆት ስንጠባበቃት የነበረችው ቀን ደርሳልን ጉዟችን በይፋ ተጀምሮልናል፡፡ ዛሬም ሆነ ወደፊትም እኔና መላው ቤተሰቤ ለሰላም፣ ለፍቅርና ለእርቅ የማንደራደርና ከምንም ነገር በላይ ቅድሚያ የምንሰጥ መሆኑን አክብሮት መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡

መካሪ አያሳጣን!

ሰላም! ሰላም! እንደምን ሰነበታችሁ የተወደዳችሁ ኢትዮጵያዊያን! እኔ ደላላው አንበርብር ምንተስኖት እናቷ ማንጠግቦሽ ብለው ከሰየሟት እኔም ዘወትር ከማልጠግባት ውዷ ባለቤቴ ጋር 100 ቁጥር ያለበት ሻማ ለኩሰን በማብራት፣ ቡናችንን ፉት እያልን እያከበርን ነው፡፡

እንመራረቅ እንጂ!

ሰላም! ሰላም! እንደምን ከርማችኋል የተወደዳችሁ የዚህ ዘመን ዕንቁዎች! ቤት ሠፈር ቀዬው ሰላም እንደሆነ ሳላበስራችሁ አላልፍም፡፡ ሰሞኑን ባሻዬ፣ ‹‹እንግዲህ ለአገር የሚበጅ፣ ለትውልድ የሚጠቅም ሲከናወን እኛም ዕገዛ ማድረግ አለብን፤›› ያሉትን አድንቄያለሁ፡፡

ዓረሙ ይነቀል!

ሰላም! ሰላም! የተወደዳችሁ ወገኖች! በያላችሁበት አንዳንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ይድረስልኝ፡፡ ባሻዬ ልጃቸውን፣ ‹‹አሁንስ ህልም እያየሁ እየመሰለኝ ነው፡፡ ህልምም ከሆነ እባክህ እንዳትቀሰቅሰኝ፤›› በማለት ደስታቸውን ሲገልጹ ነበር፡፡

የቁልፉን ነገር አደራ!

ሰላም! ሰላም! የተወደዳችሁና የተመረጣችሁ ወዳጆቼ እንደምን ከርማችኋል? እኔ ደህናም ነኝ! ደህናም አይደለሁም፡፡ ደህናውን በመናገር ጀምር ካላችሁኝ መቼም የደስታዬ ምንጭ ይጠፋችኋል ብዬ አልጠረጥርም፡፡

ለሁሉም ጊዜ አለው!

ሰላም! ሰላም! እንደምን ቆያችሁልኝ የተወደዳችሁ? እኔማ ናፍቆት እያብሰከሰከኝ ከረምኩ፡፡ መቼም ደላላ ፍቅር አያውቅም የሚል ስንት አለ መሰላችሁ? ፍቅር ለመስጠት ምን ያንሰንና ነው? ወዳጆቼ ዘመን ተቀይሯል፡፡ ፍቅራችንንም ለመግለጽ መሬትና መኪና ካጋዛችኋቸው ሰዎች ጋር ‘ሰልፊ’ ተነስቶ መልቀቅ የተለመደ ነገር ሆኗል፡፡