Skip to main content
x

ፌርማታ

እሑድ ሚያዝያ 7 ቀን 2010 ዓ.ም. አመሻሽ ላይ ሚሊኒየም አዳራሽ ለተሰበሰቡ 25 ሺሕ የሚሆኑ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ንግግር አድርገው ነበር፡፡

የፋሲካው በዓል

የዘንድሮ የእግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል (ፋሲካ) በኢትዮጵያና በምሥራቅ አውሮፓ ኦርቶዶክሳውያን ዘንድ መጋቢት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ተከብሯል፡፡ በአዲስ አበባ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በተገኙበት ተከናውኗል፡፡ የፋሲካ በዓል በድምቀት ከሚከበርባቸው አገሮች መካከል ሩሲያ አንዷ ነች፡፡ በሩሲያ የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉን አስመልክቶ በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ተሳትፈዋል፡፡

የዶግአሊ መታሰቢያ በምፅዋ

በአፄ ዮሐንስ አራተኛ ዘመን፣ በወርኃ ጥር 1879 ዓ.ም. የንጉሠ ነገሥቱ ጦር በራስ አሉላ አዝማችነት በወራሪው የጣሊያን ሠራዊት ላይ በዶግአሊ/ ተድአሊ የተቀዳጀውን ድል ለመዘከር፣ በየካቲት 1960 ዓ.ም. በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አማካይነት በምፅዋ ከተማ ቆሞ የነበረውና አብዮቱ የበላው ሐውልት ይህ ነበር፡፡

  • ሔኖክ መደብር

ዳየር አምባ

ይህ ዳየር አምባ ነው፡፡ ዳየር የሚገኝበት የግሼ ወረዳ ከተማ ራቤል ይባላል፡፡ ከራቤል ዳየር አምባ ለመድረስ በእግር ጉዞ ሦስት ሰአት ያህል ይወስዳል፡፡ በፎቶው እንደምትመለከቱት ወደ አምበው ለመድረስ ቀጥ ያለውን ዳገት መውጣት ግድ ነው፡፡ ዳገቱ ብቻ በእግር ጉዞ ከሠላሳ እስከ አርባ አምስት ደቂቃ ይፈጃል፡፡ ዳገቱን ሲጨርሱ ከገደሉ አናት ላይ ሜዳ አለ፡፡ አምባ የሚባለውም ከላዩ ያለው ሜዳ ነው፡፡ አምባው ላይ የቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ትገኛለች፡፡ ጥንታዊቱዋ የዳየር ማርያም ቤተ ክርስቲያን በአፄ ኢያሱ ዘመነ መንግሥት ዲሜጥሮስ በተባሉ የሸዋ ገዥ እንደተሠራች ይነገራል፡፡

«ሴቶች የወንዶች የበላይ ናቸው»

ዕድሜያቸው በግምት 70 ዓመት እንደሚሆናቸው ይናገራሉ፡፡ ሴቶች የእኩልነት መብት ያገኙት አሁን ሳይሆን በዘመነ ክርስቶስ እንደሆነ ማስረጃ ያቀርባሉ፡፡ «ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከከርሰ መቃብር ሞትን ድል ነስቶ መነሳቱ የተናገራቸው ለሴቶች ነው» ይላሉ፡፡ ይህም ከወንድ እኩልነትን ሳይሆን የበላይነታቸውን ያስረዳል የሚሉት እማሆይ ገላነሽ ሐዲስ የቅኔ መምህርት ናቸው፡፡

ውሻና ስድስቱ ነገሮች

በርዘመሃር የተባለ ፈላስፋ እንዲህ አለ፡- ስድስቱን ነገሮች ገንዘብ ያደረገ ሰው ፍፁም ነውይባላል፡፡  ከነሱ አንዱን ያጐደለ እንደሆነ ግን ሰው ከመባል የራቀና የተለየ ነው፡፡ እነዚህን  ልብ ብሎ ካስተዋለ ግን ፍፁም ሰው ይባላል፡፡ እነሱም፡- ፍቅር፣ የልቡና መስማማት፣ ትሕትና፣ ማመስገን እና ተስፋ ናቸው፡፡

የድቻዎች ጉዞ

በአፍሪካ  የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ አዲስ መጪው ወላይታ ድቻ በተደጋጋሚ  የአህጉሪቱን ዋንጫ በማንሳት የሚታወቀውን   የግብፁን   ዛማሌክ በመርታት  ከውድድር ማሰናበቱ  ጉድ አሰኝቷል።

ደራሲ ማን ነው?

አንተ ባለቅኔ! አንተ ልብ-ወለድ ወላጅ ሥነጽሑፍን ከሕዝብ ገንጥሎ ተራማጅ፡፡        ከመካከል ቁመህ ደረትህን አትንፋ        ወይ እሳቱን አንድድ ወይ እሳቱን አጥፋ…

የፎቶው ገበታ

በ45 ዓመቱ የሞተው የመጨረሻው ወንድ ኖርዘርን ዋይት አውራሪስ፡፡ በኬንያ በሚገኘው አንድ የእንስሳት መጠባበቂያ ይኖር የነበረው አውራሪሱ ከዝርያዎቹ የቀሩት ሁለት ሴቶች ብቻ እንደሆኑ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡