Skip to main content
x

ፍሬከናፍር

‹‹ወጣቶች የመልካም ተግባር አርአያ መሆን እንጂ በስሜት በመነሳሳት አንድነትን በሚሸረሽሩ ተግባር ላይ መሰማራት <

ፍሬከናፍር

‹‹አሁን ፕሬዚዳንታችን ሆነዋል። ከእንግዲህ የርስዎ ስኬት የአገራችን ስኬት ነው። ለርስዎ ከፍተኛ ድጋፍ አደርጋለሁ!

‹‹የርዕዮተ ዓለም ልዩነት የጋራ ሀብት እንጂ የልዩነት መነሻ መሆን የለበትም!››

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ከአገር አቀፍና ክልላዊ እንዲሁም በቅርቡ ከባህር ማዶ ከመጡ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት የተናገሩት፡፡ ኅዳር 18 ቀን 2011 ዓ.ም.

ፍሬከናፍር

‹‹ሌብነት ገንዘብ መዝረፍ፣ የሕዝብንና የመንግሥት ሀብት መበዝበዝ ብቻ አይደለም። የሕዝብ ሀብት የሆነውን መሬት በመሀል ከተማ አጥረው በፆም ለዘመናት ማቆየትም ሌብነት ነው። አንዳንዱ እንደ ከዚህ በፊቱ መስሎት የአጥር ቆርቆሮዬን አላነሳም ይላል፡፡››

‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ብርታት የሚጠይቀውን ጎዳና መርጠዋል እኛም ከጎናቸው እንቆማለን!››

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ጋር በፓሪስ ኤልሴ ቤተ መንግሥት ጥቅምት 19 ቀን 2011 ዓ.ም. በተገናኙበት ወቅት የተናገሩት፡፡ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚያደርጓቸው ማሻሻያዎች በቀላሉ የማይታዩ መሆናቸውንም አመልክተዋል፡፡

ፍሬከናፍር

‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በኢትዮጵያውያን ወገኖችዋ ስትቃጠል ማየት አሳፋሪና የድፍረት ድፍረት ነው!›› ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዓመታዊ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ ጥቅምት 12 ቀን ሲከፍቱ የተናገሩት፡፡

‹‹እኔ በቻይና ቋንቋ መነጋገር አልችልም፣ የምንነጋገረው በእንግሊዝኛ ነው፣ እንግሊዝኛ ፋብሪካዎችን መገንባት ካልቻለ ምን እናድርግ ታዲያ?››

የኡጋንዳ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ፡፡ ፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ ይህንን የተናገሩት እሑድ ጥቅምት 4 ቀን 2010 ዓ.ም. ለንደን ውስጥ ከእንግሊዝ ኢንቨስተሮች ጋር በነበራቸው ውይይት ነው፡፡

ፍሬከናፍር

‹‹ከወሳኝ ባለድርሻ አካላት ጋር አገራዊ መግባባት ባልፈጠረ የፖለቲካ ምኅዳር ብቻችንን ስንዳክር ቆይተናል!››

ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር)፣ የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባን በከፈቱበት ወቅት ካሰሙት ዲስኩር የተወሰደ፡፡ ፕሬዚዳንቱ የፓርላማውን አራተኛ የሥራ ዘመን አንደኛ የጋራ ስብሰባ ላይ የ2011 በጀት ዓመት የመንግሥት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫንም አስታውቀዋል፡፡