Skip to main content
x

የሚታየው ሁሉ ሚራዥ የሚሆንባት አገር. . .!

በቀትር በአስፋልት፣ በምድረ በዳ በመኪና ወይም በእግር ስንጓዝ ከርቀት ውኃ ይታየንና እየቀረብን፣ እየተጠጋን ስንሄድ ግን ውኃውን አናገኘውም፡፡ እንደገና ራቅ ብሎ ግን ያታየናል፡፡ ስንጠጋው አሁንም ውኃውን አናገኘውም፡፡ ጀንበር ጠልቃ ወይም ጉዞአችንን ጨርሰን እስክናቆም ድረስ አዙሪቱና ዑደቱ በዚህ ሁኔታ ይቀጥላል፡፡ ይህን ክስተት ነጮች ሚራዥ (Mirage) ይሉታል፡፡

ወቅታዊው የኢትዮጵያ ምስቅልቅል መንስዔውና መፍትሔው

ኢትዮጵያ አገራችን እንደ አገር በታሪክ ከታወቀችበት ጊዜ ጀምሮ ከውስጥና ከውጭ በሚነሱ ችግሮች ዜጎችዋ ሲታመሱ ኖረዋል። ከውጭ የመጣውን ጠላት ዜጎችዋ ከጥንት ጀምሮ መክተው በመመለሳቸው ኢትዮጵያ በነፃነትዋ የምትታወቅ አገር ሆናለች። እኛም ከጥንት ታሪካችን በተለይ የዓድዋን ድል በንግግራችን ውስጥ ሁሉ ካፋችን ሳይጠፋ፣ ደግመን ደጋግመን በመናገር እርካታ እንደምናገኝ የሚያጠራጥር አይደለም።

ከመጣንበት ይልቅ አብረን የምንጓዝበት መብለጡን ነጋሪ ያስፈልገናል ወይ?

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገራችን ከፍተኛ የሕዝብ የለውጥ ፍላጎት፣ ቀላል የማይባልም ለውጥ ታይተዋል፡፡ በዚህ ሒደትም የፍላጎት ግጭቶችና የፖለቲካ ውዝግቦች በማጋጠማቸው ዜጎች ለሰላም ዕጦት ተጋልጠዋል፡፡ የብሔሮች ግጭትና የሕዝቦች መፈናቀል፣ የባለሀብቶች መጎዳትና የልማት መስተጓጎልም እንደቀጠለ ነው፡፡

የጥላቻ ንግግሮች የወለዱት የወቅቱ ሥጋትና የወደፊቱ ፈተና

ሰሞኑን በአንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ የተደረገ አንድ የኦሮሚኛ ቃለ መጠይቅ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ በፌስቡክ ላይ ሲቀባበል ገጥሞኝ አነበብኩት፡፡ ቃለ መጠይቁን አንብቤ እንደጨረስኩ የተፈጠረብኝ ስሜት በ"ፖስት ሞደር" ዘመን ያውም በከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቀስመዋል ከሚባሉ ሰዎች፣ እጅግ ኋላ ቀርና ክፉ ዘረኛነት የተጣበበው አስተሳሰብ እንደ አዲስ ሊዘራ ቻለ የሚል ሥጋትና ጥርጣሬ ነበር፡፡

ከስህተታችን እንማር

ይህ ጽሑፍ አቶ አንዳርጋቸው አሰግድ በሪፖርተር ጋዜጣ እኔ እምለው ዓምድ ላይ እሑድ የካቲት 20 ቀን 2011 ዓ.ም. ለጻፉት መልስ ነውና በጥሞና አንብቡልኝ፡፡

ጦር መሳልና ጠብመንጃ መወልወልን በአንድ ድምፅ እንቢ ልንል ይገባል

ዛሬ የሕዝቧ ቁጥር አንድ መቶ ሚሊዮን እንደተጠጋ (በማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ግምት) የሚነገርላት አገራችን ኢትዮጵያ፣ በተለያዩ ጊዜያት ብዙ ስቃይና መከራን አስተናግዳለች፡፡ የስቃይና የመከራዋ ማብቂያ እንደ ሰማይ ርቋት በችጋር ተወልደው ማደጋቸው ሳያንሳቸው ዘልለው ያልጠገቡ ሕፃናት ልጆቿ፣ ወጣቱ፣ ጎልማሳው፣ አዛውንቱ በተለያዩ ጊዜያትና ምክንያቶች ለስደት ባስ ሲልም ለሞት መዳረጋቸውን ጆሮዎቻችን ተላምደው በየዕለቱ የምንሰማው መፈናቀል፣ ስደትና ሞት ተራ ነገር እየሆነብን መጥቷል፡፡

‘ብቻውን የበላ ብቻውን ይሞታል’

ዕድል ፈንታው ሆኖ ጨዋታ በቀላሉ የሚደምቅለት አንድ ወዳጄ በዚያ ሰሞን፣ ‹‹ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ዘንድሮ 44ኛውን የልደት በዓሉን መቀሌ ላይ በመታደም ያከበረው ብቻውን እየቆዘመ ነበር፤››

የምርጫ ቦርድን ትኩረት የሚሻው ሌላው ዓብይ ጉዳይ

አገራችን የተያያዘችውን የለውጥ ጉዞ ከልባችን የምንደግፈውና ልናግዝ በፅናት የተነሳሳነው በውስጡ ምንም ዓይነት ችግር ስለሌለው አይደለም። አባጣ ጎርባጣ፣ ውጣ ውረድ፣ መውደቅ መነሳት፣ ሕይወትና ሞት የተቀላቀሉበትና ስንክሳር የበዛበት መሆኑ ምንም አያጠያይቅም። ነገር ግን በማናቸውም መሥፈርት ቢለካ አንድ፣ ሁለት ተብለው የሚቆጠሩ፣ በጆሮ የሚሰሙ ብቻ ሳይሆኑ በዓይን የሚታዩ ተጨባጭ የሆኑ ለውጦች በየቀኑ ህያው እየሆኑ መጥተዋል።