Skip to main content
x

የመስከረሟ አደይና ሆያ ሆዬ

የአዲስ ዘመን ብስራት በአንድ ጎኑ መሬት ከፀሓይ ጋር ካላት ግንኙነት የሚከሰት ነው፡፡ አንድ ዓመት፣ ሁለት ዓመት እየተባለ የሚጠራው መሬት በፀሓይ ዙሪያ ጉዞዋን ለማድረግ የሚፈጅባትን የ365 ከሩብ ቀናት የሚፈጅባት ጊዜ ነው፡፡ በነዚህ የዐውደ ዓመት ቀናት አራቱ ወቅቶች ክረምትና በጋ፣ መፀውና ፀደይ ይፈራረቃሉ፡፡

ታሪካዊቷ መስከረም 1 ቀን ድሮና ዘንድሮ

መስከረም 1 ቀን የአዲስ ዘመን መባቻ፣ ቅዱስ ዮሐንስ ለኢትዮጵያና ለኤርትራ ልዩ ትርጉም አላት፡፡ ኤርትራ በቅኝ ገዥዎቹ ጣሊያንና እንግሊዝ ለ60 ዓመታት ተይዛ ከቆየች በኋላ በፌዴራሲዮን ከኢትዮጵያ ጋር የተቀላቀለችው መስከረም 1 ቀን 1945 ዓ.ም. ነበር፡፡

መልካም አዲስ ዓመት!

ጤና ይስጥልኝ፡፡ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሬይነር እባላለሁ፡፡ መልካም አዲስ ዓመት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ፡፡ በኢትዮጵያም ሆነ በመላው ዓለም  አዲስ ዓመት ለራሳችን፣ ለቤተሰቦቻችን  እንዲሁም ለወዳጆቻችን  ብሩህ ተስፋን የሰነቀ ነው፡፡   ይህ ተስፋ በኢትዮጵያ ከቀደሙት ዓመታት ይልቅ ዘንድሮ ይበልጥ ለምልሞ ይታያል፡፡

የፀሐይና የጨረቃ የዓመት መባቻ የገጠመበት መስከረም 1

ዘመን ከሚሞሸርባት ዓመት ወደሚቀመርባት ወደኛዋ እንቁጣጣሽ ወደ አደይዋ ንስናሽ ተብሎ በመደበኛው ፀሐያዊው የኢትዮጵያ አቆጣጠር መሠረት መስከረም 1 ቀን 2011 ዓ.ም. (የቁጥር ድርደራውም በተመሳሳይ 1111 ሆኗል) አዲሱ ዓመት ገብቶ ሁለተኛው ቀን ላይ እንገኛለን፡፡

መስከረም የወራቱ ጌታ

‹‹ኢዮሃ አበባዬ . . . መስከረም ጠባዬ›› ዘመን በተሞሸረ ዓመት በተቀመረ ቁጥር ሰው መልካም ምኞት የሚለዋወጥበት ሐረግ ነው፡፡ ድምፃውያንም ያቀነቅኑታል፡፡ እንግዲህ ኃያሉ ክረምት ሊያበቃ፣ መሰስ እያለ ወጥቶ ለከርሞ ሊመለስ ከመስቀል በዓል በኋላ አንድ ሳምንት (መስከረም 25 ቀን 2011 ዓ.ም.) ቢቀረው ነው፡፡

የጳጉሜን ነገር

ዛሬ ያመቱ፣ የ2010 ዓ.ም. 360ኛ ቀን ነው፡፡ ዓመቱ ሊያበቃ፣ ዘመኑ ሊካተት አሮጌ ሆኖ ሊያልፍና ዓምና የሚለውን ካባ ለመደረብ አምስት ቀናት ቀርቶታል፡፡ ጳጉሜን ከነሐሴ ወር መጨረሻ አዲስ ዓመት ከጀመረበት መስከረም አስቀድመው የሚገኙ ዕለታትን የያዘች ናት፡፡ ጳጉሜን ቃሉ ‹‹ሄፓጎሜኔ›› ከሚለው የግሪክ ቃል የተገኘና ተጨማሪ የሚል ፍች አለው፡፡ ትርፍ የሚል ትርጉምም የሚሰጠው ጊዜ አለ፡፡

በቋንቋና ባህል ላይ ያተኮሩት አዲሶቹ ጥናቶች

በቋንቋና የጋራ ባህል እሴቶች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ባለሙያዎች ጋር የተካሄዱ ጥናቶች ስብስብን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ለኅትመት አብቅቷል፡፡ የመጻሕፍቱን ማስተዋወቂያና ምረቃ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

የኢትዮጵያ ጥናት በአውሮፓ የተወጠነበት የሐበሻው ደብረ እስጢፋኖስ

ኢትዮጵያውያን ቅዱሳት ሥፍራዎችን ለመሳለም (ለንግደት) እጅግ ከራቀው የጥንት ዘመን ጀምሮ በየዓረፍተ ዘመኑ ወደ ኢየሩሳሌም ይጓዙ እንደነበር ይወሳል፡፡ እንደዚሁም ተሳላሚዎች ወደ ሮም መምጣት የጀመሩት እ.ኤ.አ. በ1351 መሆኑን ስለ ሰብአ ሰገል በሚናገረው መጽሐፍ ተጠቅሶ ይገኛል፡፡

ኅብራዊው ክብረ በዓል

በሮም ፍራስካቲ ሠፈር የሚገኘው ትልቁ ባሰሊካ (ካቴድራል) የማያቋርጥ የደወል ድምፅ ይሰማል፡፡ እየቆየም ማስተጋባቱን ቀጥሏል፡፡ በአዘቦቱ ዘወትር ከሚሰማው የተለየውም በሀገረ ጣሊያን በምሥራቅ ኦርቶዶክስና በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያናት ረቡዕ  ነሐሴ 9 ቀን 2010 ዓ.ም.