Skip to main content
x

‹­‹ሙስናን መታገስ የማይችል አሠራር ነው ያሰፈነው››

በቅርቡ የእናት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ በሰብሳቢነት እንዲመሩት ሁለተኛዋን ሴት የቦርድ ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡ የመጀመርያዋም ሆኑ ሁለተኛዋ የባንክ ቦርድ ሊቀመንበር የተሰየሙት በዚሁ እናት ባንክ ነው፡፡ በአገሪቱ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ በዚህ የኃላፊነት ደረጃ ያገለገለ ሴት አልነበረም፡፡ የመጀመርያዋን የቦርድ ሊቀመንበር ተከትለው ሁለተኛዋ የባንኩ ቦርድ ሊቀመንበር መሆን የቻሉት ደግሞ ወ/ሮ ሐና ጥላሁን ናቸው፡፡

‹‹ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ያስፈለገበት አንዱ ጉዳይ ተተኪ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሰየምበትን የሽግግር ሒደት ለማየት ነው››

አምባሳደር ዶናልድ (ዶን) ያማማቶ፣ በአሜሪካ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ውስጥ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ትልቅ ቦታ ያላቸው ዲፕሎማት ናቸው፡፡ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት፣ ለአፍሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ ረዳት ሚኒስትር ተብለው ከተሾሙ ስድስት ወራት አስቆጥረዋል፡፡ ቀድሞውንም በአፍሪካ የካበተ የዲፕሎማሲ ልምድ ያላቸው ጎምቱ በመሆናቸው ወደ ሥራ ለመግባት ጊዜ አልፈጀባቸውም፡፡ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር በመሆን አራት ለዓመታት ማለትም እ.ኤ.አ. ከ2006 እስከ 2009 ማገልገላቸው አይዘነጋም፡፡

‹‹በኢትዮጵያ የአየር ብክለት ጉዳይ የሰዎችን ትኩረት መሳብ የጀመረው ገና አሁን ነው››

በአሜሪካ መንግሥት የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አማካይነት የአየር ብክለትና የብክለት ደረጃን የሚለካ ጥራቱን የሚከታተል፣ ‹‹ኤር ኳሊቲ ፕላኒንግ ኤንድ ስታንዳርድስ›› በሚል መጠሪያ የሚንቀሳቀስ ጽሕፈት ቤት አለ፡፡ ጽሕፈት ቤቱ በአሜሪካ ያለውን የአየር ብክለት ደረጃ ከመለካት ባሻገር፣ ለብክለት መንስዔ የሆኑ ምንጮችን በመከታተልና በማጥናት ጭምር ይታወቃል፡፡ ሳራ ቴሪም የዚህ ጽሕፈት ቤት ከፍተኛ የፖሊሲ ጉዳዮች አማካሪ በመሆን ያገለግላሉ፡፡

‹‹ፖለቲካዊ ችግሩ በአፋጣኝ መፍትሔ እንደሚያገኝ ተስፋ እናደርጋለን››

ከጥቂት ቀናት በፊት የቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን፣ የተቋሙን ዓመታዊ መጽሔት ይፋ ሲያደርግ ጥንዶቹ የዓለም ቢሊየነሮች በየአጋጣሚው ከሚቀርቡላቸው በርካታ ጥያቄዎች ውስጥ አሥር ከባድ ጥያቄዎች ባሏቸው ላይ የሰጧቸውን ምላሾች በመጽሔቱ አስነብበዋል፡፡ ይህን ተከትሎም በኢትዮጵያ የቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ዋና ዳይሬክተር፣ እንዲሁም የተቋሙ የአፍሪካ ተጠሪ የሆኑት አቶ ሀዲስ ታደሰ ከሪፖርተር ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

‹‹በመጤው ተምች ሳቢያ ፈተና ላይ ወድቀናል››

ኢያን ቼስተርማን የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ (ዩኤስኤኣይዲ) ፋይናንስ በሚያደርገውና የ‹‹ፊድ ዘ ፊውቸር›› ኢትዮጵያ ፕሮጀክት፣ የእሴት ሥራዎች ላይ ለሚካሄደው እንቅስቃሴ ዋና ኃላፊ ወይም ቺፍ ኦፍ ፓርቲ ናቸው፡፡ ፕሮግራሙ በቆሎን ጨምሮ በስድስት ዋና ዋና ሰብሎች ላይ የእሴት ሰንሰለት የማስፋፋት እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በአብዛኛው በደቡብ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራና በትግራይ ክልሎች ውስጥ የሚተገበር ፕሮግራም ነው፡፡ በግብርና መስክ ከ30 ዓመታት በላይ ልምድ ያካበቱት ሚስተር ቼስተርማን፣ በኢትዮጵያ ብቻም ሳይሆን በኬንያ፣ በዛምቢያ፣ እንዲሁም በዚምባብዌ ሠርተዋል።

‹‹አንድነታችን ሊጠናከር የሚችለው ሥልጣን የሚያዝበት ሥርዓት በሕዝብ የሚታመን ሲሆን ነው››

ኢሕአዴግ ሥልጣን ከተቆጣጠረ ጀምሮ በሽግግሩ ጊዜና ከሽግግሩ በኋላም በአጠቃላይ ለሰባት ዓመታት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማጆር ሹም የነበሩት ሌተና ጄኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳዔ፣ በወቅታዊ ጉዳዮችና በቅርቡ ሹመት ስላገኙ ጄኔራሎችና የጠቅላይ ኤታ ማጆር ሹም የሥልጣን ቆይታን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ከዮሐንስ አንበርብር ጋር ያደረጉት ቆይታ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

‹‹በመረጃ የበለፀገ ኅብረተሰብ በመፍጠር ቢያንስ የሰው ሕይወት ሕልፈትን መቀነስ ይቻላል››

የአየር ንብረት ለውጥ የዓለም ሥጋት በመሆኑ የዓለም መሪዎች ጭምር ዋነኛ አጀንዳ አድርገውት መምከር ከጀመሩ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ድንበር የማያግደው ይህ የአየር ንብረት ለውጥ ችግር ነገም ሥጋት ሆኖ መቀጠሉ እየታየ ነው፡፡ ኢትዮጵያም በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ተደጋጋሚ አደጋዎችን አስተናግዳለች፡፡ ወደፊትም የሚያጋጥሙዋት በርካታ አደጋዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ይነገራል፡፡ ይህንን ተለዋዋጭ የሆነ የአየር ንብረት ለውጥ ተከትሎ ሊመጡ የሚችሉ አደጋዎችን ለመቀነስ፣ የአየር ንብረት ለውጡንና ባህሪውን በመከታተል ትንበያ መስጠት ያለባቸው ተቋማት ሥራ ከብዷል፡፡

‹‹የኛ በኢትዮጵያ ወጣቶችን የሚወክል ትልቅ የሐሳብ ብራንድ ነው››

ሚስስ ፋራህ ራምዛን ጎላንት በኢትዮጵያ ‹‹የኛ›› በሚል ስያሜ የሚታወቀውን የልጃገረዶች ፕሮግራም ጨምሮ፣ በበርካታ አገሮች ውስጥ በልጃገረዶች ጉዳይ የሚንቀሳቀሰውን ‹‹ገርል ኢፌክት›› የተሰኘ ማኅበራዊ ተቋም በዋና ሥራ አስፈጻሚነት መምራት ከጀመሩ ሁለት ዓመታት አስቆጥረዋል፡፡ ከ12 ዓመታት በፊት በታዋቂው የስፖርት ትጥቅ አምራች ናይኪ ኩባንያ፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፋውንዴሽንና በሌሎችም አጋሮች አማካይነት ተመሥርቶ የሚንቀሳቀሰው ገርል ኢፌክት፣ በኢትዮጵያ የኛ ፕሮግራምን መምራት ከጀመረም አምስት ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡

‹‹የአዲስ አበባ ጂቡቲ ምድር ባቡርን ለማስተዳደር በዓመት 59 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ ይፈጸማል››

ጥላሁን ሳርካ (ኢንጂነር) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ1980 ዓ.ም. በሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ተመርቀዋል፡፡ ከዩኒቨርሲቲ ከወጡ በኋላ በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ከ29 ዓመታት በላይ አገልግለዋል፡፡ መጀመሪያ ተቀጥረው ሥራ የጀመሩት በገንዘብ ሚኒስቴር ውስጥ ነበር፡፡ አንድ ሜካኒካል ኢንጂነር ገንዘብ ሚኒስቴር ውስጥ ምን ዓይነት ሥራ ቢኖረው ነው? የሚል ጥያቄ ቢያስነሳም፣ እሳቸው በዚህ መሥሪያ ቤት እስከ የሽያጭና የጥገና መምርያ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል፡፡ በ1983 ዓ.ም. የመንግሥት ለውጥ ሳቢያ ባለሙያዎች ክልላችሁን አልሙ የሚለው የመንግሥት ሐሳብ ሲመጣ፣ አንድ እርከን ተጨምሮላቸው ወደ ሐዋሳ በመሄድ የደቡብ ክልል የመንግሥት ዕቃ ግዥ መምሪያን ማደራጀታቸውን ይገልጻሉ፡፡

‹‹ከቱሪስቱ በላይ እኛ ዘንድ ያለው ችግር ነው መሠረታዊ ለውጥ የሚፈልገው››

‹‹ኢትዮጵያን ብዙ ብናስተዋውቅ፣ ገጽታ ብንገነባና በርካታ ቱሪስቶች ብናመጣ የማስተናገድ አቅማችን ዝግጁ ካልሆነ፣ በርካታ መዳረሻዎችን ካልገነባን አሉታዊ ተፅዕኖ ይፈጥራል፤›› የሚሉት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ መዓዛ ገብረ መድኅን፣ በቱሪዝም ዘርፉ በርካታ ያልተነኩ ሀብቶች እንዳሉ ይገልጻሉ፡፡ የዘርፉ ማነቆዎች በግሉ ዘርፍ ተሳትፎም ጭምር መፈታት አለባቸው ብለው ያምናሉ፡፡ መስኅብ ከመለየት፣ መዳረሻ ቦታዎችን ከማልማት ችግሮች ባሻገር፣ የሠለጠነ የሰው ኃይል ችግርም የዘርፉ መገለጫ ነው፡፡