Skip to main content
x

አዲስ አበቤዎች ለምን ደመ መራር ሆኑ?

እንደሚመስለኝ አዲስ አበባን የመሠረቷት ሁሉም ኢትዮጵያን ናቸው፡፡ እንደ ዕድል ሆኖ አዲስ አበባ የታላቋ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ ሆነች፡፡ ይኼን ዕድል ባታገኝ ኖሮ አካባቢው ወይም ለእርሻ ተስማሚ ነው እንደሚባለው ትልቅ ማሳ ይወጣት ነበር፡፡

ማጠንጠኛ

መኖርን የመሰለ ነገር የለም ሲባል እንዲያው ዘበት ይመስላል፡፡ መኖር ደግ ነው፡፡ ደጉንም ክፉውንም፣ ወጪውንም ወራጁንም በየፈርቁ ያሳያል፡፡ መኖር የእውነትም የቀጠሮና ጊዜ መጠበቂያ ነው፡፡ ‹እውነትና ንጋት እያደር ይገለጣል› እንዲሉ፡፡

በለውጥ ምዕራፍ ለአሳሳቢ ግጭቶች ተገቢው ትኩረት ይሰጥ!

ኢትዮጵያ ከተያያዘችው የመደመርና ይቅርታ ለውጥ ጎን ለጎን አሳሳቢ የሆኑ አካባቢያዊ ግጭቶች እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ እነዚህ ግጭቶች የብዙ ዜጎች ሕይወት አካልና ሥነ ልቦና ላይ አስከፊ ጉዳቶችን ከማድረሳቸው በተጨማሪ፣ ዜጎች ያፈሩትን ንብረት ለዘረፋና ውድመት በማጋለጥና ረጅም ጊዜ ከሚኖሩበት አካባቢ በማፈናቀል ከፍተኛ ማኅበራዊ ቀውስ አስከትለዋል፡፡ የዚህ ጽሑፍ ዋና ዓላማ ከጥልቅ ሐሳብ የመነጩና ግጭትን በመከላከል ረገድ ትኩረት የሚሹ የመፍትሔ ዕርምጃዎችን በመሰንዘር አስተዋጽኦ ለማበርከት ያለመ ነው፡፡

ኢሕአዴግ በመንታ መንገድ ላይ

የሰው ልጅ ለአቅመ አዳም ደረሰ የሚባለው ዕድሜው ሰላሳ ዓመት ሲሞላው እንደሆነ ብዙዎች ያምናሉ፡፡ ይኼ ጊዜ አፍላ የጉርምስና ወቅት ተጠናቆ ሰው በአስተሳሰቡ መብሰልና መጎልመስ የሚጀምርበት ዕድሜም  ነው፡፡ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት አዳም ሲፈጠር የሰላሳ ዓመት ጎልማሳ ሆኖ ነበር፡፡

‘አያ ጅቦ ሳታማሃኝ ብላኝ’

አገርና የፖለቲካ ድርጅት አንድ እንዳልሆኑና በአንድ ዓይነት መስፈሪያ እንደማይመዘኑ መናገር፣ መአልትና ሌሊት እየቅል መሆናቸውን የማስረዳት ያህል ነው፡፡ ታዲያ ይህ ሚስጥረ ሥላሴ እንዳልሆነ እየታወቀ ከሰፊው አገራዊ ጥቅም ይልቅ፣ ለአንድ የተወሰነ ቡድን ፖለቲካዊ ትርፍ ወይም ለግለሰብ መሪዎቹ ስምና ዝና የበለጠውን ትኩረት በመስጠት ሁለቱን ሆን ብሎ ለምን ማምታታት ይኖርብናል?

ውለታን አለመክፈል ከክህደት አይተናነስም

ሊቁ አንድን ሰነፍ ተማሪ ሁል ጊዜ ሲያነብ ንባብ ያርሙታል፡፡ በዚህም የተነሳ ጓደኞቹ እየናቁት ሄዱ፡፡ እርሱም ንባቡን ከማሻሻል ይልቅ መምህሩን ዝም የሚያሰኝበት ሌላ መንገድ አሰበ፡፡ አንድ ቀን በጋቢው ውስጥ አናት ውኃ የሚያደርግ የወይራ ዱላ ይዞ ወደ ንባቡ ቀረበ፡፡

የኢትዮጵያ የትምህርት ፖሊሲ ለውጥ ከጃፓን አንፃር

አሁን ባለው የዓለም ነባራዊ ሁኔታ ሉላዊነት (ግሎባላይዜሽን) ዓለምን አገሮች ጠንካራ ወደ ሆነ ውድድር በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊና በባህል ዘርፎች እየገፋ ይገኛል፡፡ የሰዎችና የመረጃ በቀላሉ ድንበሮችን ከአገር ወደ አገር፣ እንዲሁም ከአኅጉር ወደ አኅጉር ማንቀሳቀስ መቻሉ የግለሰቦችን፣ የተቋማትን፣ የአገሮችንና የአኅጉራትን በዓለም ላይ ያላቸውን ተወዳዳሪነት የሚወስነው መረጃዎችን በአግባቡ የመተንተንና የመጠቀም አቅም ያላቸው ዜጎች ላይ ይወሰናል፡፡

ዕውቀት ወደ ሥልጣን ወይስ ሥልጣን ወደ ዕውቀት?

አባ ጨጓሬ ሃምሳ እግር አለው፡፡ አንዱ መጥቶ “አባ ጨጓሬ  በጣም ታድለሃል፡፡ ሃምሳ እግር አለህ” አለው፡፡ “ይመሥገነው፣ አዎን የሃምሳ እግር ጌታ ነኝ” ብሎ መለሰ፡፡ “በጣም ጎታታ ስለሆንክ አካሄድ ላስተምርህ” አለውና ሥልጠና ጀመረ፡፡ ሥልጠናው አለቀና በሥልጠናው መሠረት ሂድ ሲለው አባ ጨጓሬ ተደነቃቅፎ ወደቀ፡፡

የሽግግሩን ሒደት የሚያመሰቃቅሉት ፖለቲከኞች ናቸው

በለውጥ ሒደት ውስጥ አስቸጋሪ ወቅት የሽግግር ጊዜ ነው፡፡ የሽግግር ጊዜ ለዘመናት የተሰባሰቡ ብሶቶች ፈጠው የሚወጡበትና ሁሉም ደርሶብኛል ብሎ የሚገምተውን በደል በስሜት የሚያቀርብበት ሁኔታ በመኖሩ በርካታ ችግሮች ይፈጠራሉ፡፡ ሕግ ይጣሳል፡፡ ንብረት ይወድማል፡፡  ሰው ይሞታል፡፡

ያዲያቆነ ቀኖናዊነት ሳያቀስ አይለቅም

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) 11ኛ ድርጅታዊ ጉባዔውን ከመስከረም 23 ቀን ጀምሮ እስከ 25 ቀን 2011 ዓ.ም. በሐዋሳ ከተማ ያካሂዳል፡፡ የዚህን ጉባዔ ዝግጅት፣ የመወያያ አጀንዳዎችና የሚጠበቁትን ውጤቶች አስመልክቶ የግንባሩ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ መስከረም 10 ቀን 2011 ዓ.ም.