Skip to main content
x

መንግሥት የሽግግር ወቅት ፍትሕ እየተገበረ ይሆን?

‹‹አገር ተዘርፋ፣ ወገንም ተሰቃይቶ ከማለቁ በፊት ለውጥ እንዲመጣ ታግሎ አሁን ለደረስንበት የተስፋ ዘመን አድርሶናል፡፡ ስለዚህም መንግሥት የሕዝብን ጥያቄ መመለስ ውዴታው ብቻ ሳይሆን ግዴታውም ነው፡፡ ፍትሕ የተበደለን ሕዝብ የመካሻ አንዱ መንገድ ነውና፡፡››

ሰማያዊ ፓርቲ ለተቋማት ግንባታ ቅድሚያ እንዲሰጥ አሳሰበ

ላለፉት ሰባት ወራት የተካሄደውን የለውጥ ጅምር እንደሚያደንቅ የገለጸው ሰማያዊ ፓርቲ፣ ይህ መልካም የለውጥ ጅማሮ መሠረት የሚይዘው ግን በተቋም ደረጃ ሲገነባ ነው አለ፡፡ አሁንም የተቋማት ግንባታ ቅድሚያ እንዲሰጠው አሳሰበ፡፡

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክና ብርሃን ኢንሹራንስ ኩባንያ በ10.1 ሚሊዮን ብር ዕዳ ተከሰሱ

የአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ ለሚያስገነባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ ለተቋራጭ የገቡትን ዋስትና አልከፍልም ብለውኛል ያላቸውን ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማኅበርና ብርሃን ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበርን በ10.1 ሚሊዮን ብር ዕዳ ከሰሰ፡፡

በከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩት የአገር ውስጥ ደኅንነት ዋና ኃላፊ አሰቃቂ ድርጊት በፍርድ ቤት ተነገረ  

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የአገር ውስጥ ደኅንነት ኃላፊ የነበሩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን፣ በተጠረጠሩበት ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በዜጎች ላይ ፈጽመውታል የተባለ አሰቃቂ ድርጊት በፍርድ ቤት ተነገረ፡፡

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ የመልቀቂያ ጥያቄ አቀረቡ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ሆነው ሲሾሙ አንገራግረው የነበሩት የቀድሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንትና ከጥቂት ወራት በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ሆነው የተሾሙት አቶ በቃሉ ዘለቀ፣ ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰማ፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሠራተኞች ደመወዛቸው በመዘግየቱ ቅሬታ አቀረቡ

በፀጥታና በደኅንነት ሥራዎች የተመደቡ ሠራተኞች ሰሞኑን በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ላይ በሙስና ምክንያት በሚካሄደው ማጣራት ሳቢያ፣ ወርኃዊ የደመወዝ ክፍያ እንደዘገየባቸው በመግለጽ ቅሬታቸውን አሰሙ፡፡

በቀንጢቻ ታንታለም ማምረቻ ባህላዊ አምራቾች ለዩራኒየም ጨረር ተጋልጠዋል

በኢትዮጵያ የማዕድን፣ ነዳጅና ባዮፊውል ኮርፖሬሽን ሥር በሚተዳደረው የቀንጢንቻ የታንታለም ማዕድን ማውጫ፣ በሕገወጥ መንገድ ገብተው ታንታለም የሚያመርቱ የአካባቢው ባህላዊ የማዕድን አምራቾች ለዩራኒየም ጨረር እየተጋለጡ እንደሆነ ታወቀ፡፡