Skip to main content
x

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከተተኪው ጠቅላይ ሚኒስትር ብዙ ይጠብቃል!

ኢትዮጵያ በታሪኳ በውስጥ ችግር ምክንያት አጣብቂኝ ውስጥ ከገባችባቸው ጊዜያት መካከል እንዳሁኑ የከበደ የለም፡፡ ላለፉት ሦስት ዓመታት ያህል ሰላምና መረጋጋት ደፍርሶ የበርካቶች ሕይወት ከማለፉም በላይ፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ በተለያዩ ግጭቶች ሳቢያ ተፈናቅለዋል፡፡ የአካልና የሥነ ልቦና ጉዳት የደረሰባቸውም በርካቶች ናቸው፡፡ መጠኑ የማይታወቅ የአገር ሀብት ወድሟል፡፡ በገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ውስጥ በተፈጠረ አለመግባባት ሳቢያም አገር ቋፍ ላይ ትገኛለች፡፡

በሕዝብ ላይ መቆመር አስነዋሪ ነው!

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሚታወቅባቸው ዋነኛ መለያዎቹ መካከል ለአገሩ ያለው ጥልቅ ፍቅር አንደኛው ነው፡፡ ይህ የአገር ፍቅር ስሜት ራስን በፈቃደኝነት ለመስዋዕትነት ከማቅረብ ጀምሮ፣ በልዩ ልዩ አበርክቶዎች እየተገለጸ ዘመናትን መሻገር ተችሏል፡፡ ይህ ኩሩና ጨዋ ሕዝብ በአገሩ ጉዳይ ከማንም ጋር ተደራድሮ አያውቅም፡፡

የሞያሌው ክስተት መወገዝ አለበት!

​​​​​​​መሰንበቻውን በሞያሌ በንፁኃን ዜጎች ላይ የደረሰው ሞትና የአካል ጉዳት በፍፁም ማጋጠም የሌለበት ከመሆኑም በላይ፣ ድርጊቱ በፅኑ ሊወገዝ ይገባል፡፡ ይህ ዓይነቱ ድርጊት የዜጎችን በሕይወት የመኖርና የአካል ደኅንነት መብትን ከመግፈፍ በተጨማሪ፣ በምንም ዓይነት ሁኔታ ተቀባይነት የሌለው ነው፡፡

የአገር ህልውና ለድርድር አይቀርብም!

እኛ ኢትዮጵያውያን ከገባንበት ቀውስ ውስጥ ለመውጣት ከእኛ በላይ ማንም እንደሌለ ማመን ይገባናል፡፡ ባዕዳን መጡም ሄዱም ከራሳችን በላይ በማንም መተማመን የለብንም፡፡ ኢትዮጵያውያን በታሪካቸው ለማንም ጥገኛ ሆነው አያውቁም፡፡ የጥገኝነት አስተሳሰብና ሥነ ልቦና የሌለው ሕዝባችን በታሪክ ያጋጠሙትን ፈተናዎች ያለፈው፣ በጠንካራ አንድነቱና ኅብረቱ ነው፡፡ በዚህ ዘመንም ይህ ጥሩ ልምድ ሊያገለግለን ሲገባ ባዕዳን ሥር መርመጥመጥ እየበዛ ነው፡፡

ፈተናው ቢከብድም ማለፍ ግን ይቻላል!

አገሪቱ ከሁለት ዓመታት በላይ የገባችበት የቀውስ አዙሪት፣ በተለያዩ ገጽታዎች የተለያዩ ክስተቶችን እያስተናገደ ነው፡፡ የወቅቱን ፈታኝነት በሥጋት የሚመለከቱ ያሉትን ያህል፣ ከሥጋት ባሻገር የተሻለ ጊዜ ይመጣል ብለው ተስፋ የሚያደርጉም አሉ፡፡ ወቅቱ ያረገዘው ሥጋት ፈተናውን እንዳከበደው እርግጥ ቢሆንም ተስፋ መቁረጥ ግን አይገባም፡፡

ታላቁ የዓደዋ ድል ሲዘከር የኢትዮጵያዊነት ስሜትም ያንሰራራ!

የዛሬ 122 ዓመት የአውሮፓ ኮሎኒያሊስቶችን አንገት ያስደፋ፣ የመላው ዓለም ጥቁር ሕዝቦችን አንገት ደግሞ በኩራት ቀና ያደረገ ታሪክ የተሠራው በጀግኖቹ ኢትዮጵያውያን ወደር የሌለው ተጋድሎ ነበር፡፡ ታላቁ የዓደዋ ድል የአይበገሬነት ፅናትንና የእናት አገር ጥልቅ ፍቅርን ተምሳሌታዊነት ያረጋገጠ የመስዕዋትነት ውጤት ነው፡፡

ኢትዮጵያ ዋስትና ያለው ሰላምና ዴሞክራሲ ይገባታል!

ለአገራችን ኢትዮጵያ ሰላምና ዴሞክራሲን ከመመኘት በላይ፣ ለተግባራዊነቱ ርብርብ የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡ ዋስትና ያለው ሰላምና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ቅንነት ያስፈልጋል፡፡ ይህ ቅንነት በመነጋገር፣ በመደራደርና የጋራ ውሳኔ ላይ በመድረስ ሰፊውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ያማከለ መግባባት ለመፍጠር ማገዝ አለበት፡፡ ምንም እንኳ ፖለቲካ በባህሪው ከቅንነት በላይ ውስብስብና መሰናክሎች የበዙበት የሥልጣን ፍትጊያ ቢኖርበትም፣ ለሕዝብ ደኅንነትና ለአገር ህልውና ሲባል በሰጥቶ መቀበል መርህ መመራት አለበት፡፡

ኢትዮጵያን መታደግ ይቅደም!

የአገሪቱን ተተኪ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሰየም በዝግጅት ላይ የሚገኘው ኢሕአዴግ ከፊቱ በርካታ ፈተናዎች ይጠብቁታል፡፡ ከፈተናዎቹ መካከል አንደኛው በጋራ መግባባት ላይ የተመሠረተ ዕጩ መምረጥ ነው፡፡

ለሕዝብ ፍላጎት መታዘዝ ያስከብራል!

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በገዛ ፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን ለመልቀቅ መወሰናቸው ከመሰማቱ በፊት  በእስር ላይ የነበሩ በርካታ ፖለቲከኞች ተፈተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር እንዲደረግ በማሰብ ራሳቸውን ለማግለል መወሰናቸው፣ አገሪቱ ያለችበትን አሳሳቢ ችግር ያመለክታል፡፡ ላለፉት 27 ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆየው ኢሕአዴግ ከፊቱ ሁለት መሠረታዊ ጉዳዮች ተደቅነውበታል፡፡ አንደኛው ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሁሉንም ወገኖች በሚያግባባ ሰው መተካትና የተሻለ ምኅዳር መፍጠር ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ እንደካሁን ቀደሙ በነበረው ሁኔታ የሚያስቀጥል አምጥቶ ቀውሱን ማባባስ ነው፡፡