Skip to main content
x

ጉሬዛ

ጉሬዛ ዛፍ ላይ የሚኖር ሲሆን ሴቶቹ በአማካይ 9.2 ኪሎግራም፣ ወንዶቹ ደግሞ 13.5 ኪሎግራም ይመዝናሉ፡፡ ዋነኛ ምግቡ ቅጠላ ቅጠሎችና፣ በተጨማሪም ፍራፍሬዎች ነው፡፡ በግንባሩ፣ በጉንጮቹና በአገጩ ላይ ነጭ ፀጉር አለው፡፡

ድብ

ድብ ከአጥቢ እንስሳት ይመደባል፡፡ ድቦች በዋነኛነት የሚመገቡት ፍራፍሬና አትክልቶችን ነው፡፡ አንዳንዴ በጐችን እንደሚበሉም መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ መኖሪያቸው በዋሻዎች ወይም በተቆፈረ ጉድጓድ ውስጥ ነው፡፡

አምባራይሌ

አምባራይሌ አጠቃላይ ቁመናው ከቀንዱ ጥምዝ ጋር የአጋዘን ይመስላል፡፡ በመጠኑ ግን አነሰ ያለ ነው፡፡ የወንዱ ክብደት ከ92 እስከ 108 ኪሎ ግራም፣ የሴቶቹ ደግሞ ከ56 እስከ 70 ኪሎ ግራም ይሆናል፡፡

የጥርኝ ቡና የዓለማችን ውዱ ቡና

የጥርኝ ቡና ባህል በመቶዎች በሚቆጠሩ ዓመታት ወደ ኋላ መለስ ብለን ሆላንዶች ኢንዶኔዥያን ቅኝ ግዛት ወደ ያዙበትን ዘመን ይወስደናል፡፡ በደቡብ ምሥራቅ የምትገኘው ኢንዶኔዥያ 240 ሚሊየን ሕዝብ የሚኖርባት አገር ስትሆን በዓለማችን የጥርኝ ቡና አምራች ከሆኑ አገሮች መካከል ዋነኛዋ አገር ነች፡፡

ተራ የሜዳ አህያ

ተራ የሜዳ አህያ ሰፋፊ ጥቁርና ነጭ መስመሮች፣ በተለይ ከወደ ታፋው የሚነሱት የበለጠ ሰፋፊ የሆኑ መስመሮች አሉት፡፡ ወንዱ በአማካይ 250 ኪሎግራም፣ ሴቷ 220 ኪሎግራም ይመዝናሉ፡፡

ወንድና ሴት ጎሾች

ጎሽ የከብት ዘመድ የሆነ፣ ግዙፍና ሣር በል አጥቢ ነው፡፡ ጎሾች ከፍታቸው በአማካይ ከ130 እስከ 170 ሴንቲሜትር ሲሆን፣ የወንዶቹ አማካይ ክብደት 686 ኪሎግራም፣ የሴቶቹ ደግሞ 576 ኪሎግራም ነው፡፡

የባህር ኧርቺን

የባህር ኧርቺን በውቅያኖስ ይገኛል፡፡ ኑሮውም ቅዝቃዜ በሚበዛበት የውቅያኖስ ክፍል ሳይሆን አለታማ በሆነው የውቅያኖስ ክፍል ነው፡፡ ለመኖር የሚመርጠውም ዝቅተኛውንና ሸለቋማውን የውኃ ክፍል ነው፡፡

ናይል አዞ

በሳይንሳዊ ስሙ ኮሮኮዳይለስ ኒሎቲከስ በመባል የሚታወቀው ናይል አዞ፣ የሰው ልጆች ጠር ከሆኑ ተሳቢ እንስሳት ከቀዳሚዎቹ የሚመደብ ነው፡፡ ይህ አዞ በየወንዝ ዳር ልብስ የሚያጥቡ ሰዎችን ጨምሮ በወንዝ አካባቢ የሚደርሱትን ጨልፎ በመመገብ ይታወቃል፡፡

የሱማሌና የኑቢያ የዱር አህያ

የዱር አህያ ከአንገቱ በላይ ትልቅ የሆነ፣ ረጃጅም ጆሮዎች ያሉት፣ ግራጫ ወይም አመድማ ቀለም ያለው፣ ደረቱ፣ ሆዱ፣ እግሮቹና ቂጡ፣ አፉ አካባቢና በዓይኖቹ ዙሪያ ነጭ የሆነ እንስሳ ነው፡፡ አጭር፣ ቡናማ ጋማ፣ አንዳንዴም ከትከሻው በኩል የሚወርዱ መስመሮች ያሉት፣መኻከለኛ ርዝመትና ጫፉ ባለጥቁር ጎፈር የሆነ ጅራት ያለው፣ ከፍታው ወደ አንድ ሜትር ከሩብ፣ ርዝመቱ ወደ ሁለት ሜትር፣ ክብደቱ በአማካይ 275 ኪ.ግ የሚሆን የአህያ አስተኔ ዘመድ አባል ነው፡፡ ሁለት ንዑስ ብቸኛ ዝርያዎች አሉት፡፡

አራት ዓይና አሳ

ባለአራት ዓይን የሚባል የአሳ ዝርያ አለ፡፡ ይህ አሳ ከሌሎቹ የተለየ ዓይን ያለው ነው፡፡ ይኸውም አራት ዓይን ሳይሆን እያንዳንዱ ዓይን ሁለት ዓይነት ዓይን ያለው በመሆኑ ነው፡፡ ማንይንገረው ሸንቁጥ ‹‹ባለአከርካሪዎች›› በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ እንደገለጹት፣ አሳዎቹም ጥንድ ዓይና ይባላሉ፡፡