Skip to main content
x

ለኢትዮጵያ ታዳጊዎች ተስፋን የሰነቀው የሦስት ዓመቱ የባየር ሙኒክ ፕሮጀክት

የጀርመን አንጋፋ የእግር ኳስ ክለብ ባየር ሙኒክ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ ተስፋ የፈነጠቀ የምሥራች ይዞ ብቅ ብሏል፡፡ ክለቡ በኢትዮጵያ ተሰጥኦ ያላቸውን ዕድሜያቸው ከ17 ዓመት በታች ታዳጊ ወጣቶች ለአገርና ለዓለም አቀፍ ውድድሮች ብቻ ሳይሆን አግር ኳሱን ከዓለም አቀፍ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ሊያመነጭ የሚችለውን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የሚያስተዋውቅ ሥርዓት እንዲዘረጋ ትልቅ ጅምር ስለመሆኑ ጭምር እየተነገረለት ይገኛል፡፡

ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከእግር ኳሳዊ ውበቱና ትዕይንቱ ይልቅ በአሉታዊ ጎኑ በአነጋጋሪነቱ እንደቀጠለ ይገኛል፡፡ 16 ቡድኖችን የሚያሳትፈው ፕሪሚየር ሊጉ ላለፉት አምስት ዓመታት በእንስት ዳኞች እንዳይዳኝ ተደርጎ ከቆየ በኋላ፣ ፀንቶ የቆየው ክልከላ ከሰሞኑ እንዲነሳ ተደርጎ፣ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ ሊጉን በብቸኝነት እንድታጫወት ተደርጓል፡፡ የሊጉ ደረጃና እንስት የእግር ኳስ ዳኞች የሙያ ብቃት እንደገና ማነጋገር ጀምሯል፡፡ 

በጥናት ሳይሆን በስሜታዊነት ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ሌላው የእግር ኳሱ ተግዳሮት

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በሥሩ ከሚያዘጋጃቸው ሻምፒዮናዎች፣ የአፍሪካ አገሮች በውስጥ ሊግ የሚያወዳድሯቸውን ተጨዋቾች ለማበረታታት በሚል የሚያዘጋጀው የአፍሪካ አገሮች ዋንጫ (ቻን) ይጠቀሳል፡፡ ሻምፒዮናው በየሁለት ዓመቱ አንድ ጊዜ በተመረጡ የአፍሪካ አገሮች ሲዘጋጅ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡

ኢትዮጵያውያኑ በፓሪስና በቦስተን ማራቶን ድል ቀንቷቸዋል

የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤኤፍ) በወርቅ ደረጃ ዕውቅና ከሚሰጣቸው የጎዳና ላይ ውድድሮች የፓሪስና ቦስተን ማራቶኖች ይጠቀሳሉ፡፡ በውድድሩ የተሳተፉት ኢትዮጵያውያን በሁለቱም ፆታ አሸናፊ የሆኑበትን ውጤት አስመዝግበዋል፡፡

ካፍ እና ኢትዮጵያ በቻን ሻምፒዮና ዝግጅት መንታ መንገድ ላይ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት መርሐ ግብር በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ይሁንና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይፋ ባደረገው መመሪያ አንዳንድ ክልሎች ያለ ፌዴሬሽኑ ይሁንታ ለሊጉ የሚሰጡትን የቀጥታ ሚዲያ ሽፋን እንዲያቆሙ ክልከላ ማድረጉ ሰሞነኛ መነጋገሪያ መሆኑ አልቀረም፡፡

በምሥራቅ አፍሪካ የወጣቶች ኦሊምፒክ ውጤታማው የኢትዮጵያ ቡድን ከ200 ሺሕ ብር በላይ ተሸለመ

በሩዋንዳ የተፈጸመውን የዘር ጭፍጨፋ 25ኛ ዓመት ለመዘከር ለሳምንት ያህል በመዲናዋ ኪጋሊ በተካሄደው የወጣቶች ኦሊምፒክ በአትሌቲክስ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን በወርቅ ሜዳሊያዎች የታጀበ ውጤት አስመዝግቦ ተመልሷል፡፡

ሉሲዎቹ ወደ ወሳኙ ምዕራፍ ተሸጋግረዋል

በአፍሪካ የሴቶች እግር ኳስ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በጥንካሬያቸው ከሚጠቀሱ ብሔራዊ ቡድኖች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) አንዱ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ከጊዜ ወደ ጊዜ ውጤት እየራቀው በመምጣቱ በጥንካሬው ሲጠቀስ የቆየውን የሴቶች እግር ኳስ፣ አሁን ላይ ምድቡ ወደ የማጣሪያ ማጣሪያ እንዲካተት ግድ ብሎታል፡፡

ተለዋዋጩን የእግር ኳስ ዳኝነት ሕግ በኢትዮጵያ የማስረፅ ሒደት

አሉታዊ አስተዋፅኦ ጉልህ መሆኑ በዓለም አቀፍም፣ በክለቦች ደረጃም በሚካሄዱ ጨዋታዎች ላይ የውጤት ለውጥ በማሳደር አንዱን ሲያስደስት ሌላውን ሲያስከፋ ታይቷል፡፡ የዓለም አቀፍ እግር ኳስ አስተዳዳሪ ፊፋ የዳኝነት ሕጎችን በየጊዜው የሚያሻሽለው ከዚህ በመነሳት እንደሆነም ይታመናል፡፡

በዴንማርክ የነገሡት የኢትዮጵያ አትሌቶች

አውሮፓዊቷ ዴንማርክ በአርሁስ ያሰናዳችው 43ኛው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና በኢትዮጵያውያን አትሌቶች የበላይነት ተጠናቋል፡፡ ኢትዮጵያም ዳግም በሩጫው መስክ ስሟን ያደሰችበትን ውጤት ብቻ ሳይሆን በደረጃ ስንጠረዡ የዓለም ቁንጮነቷን ያሳየችበት ድል አስመዝግባለች፡፡