Skip to main content
x

የኦሮሚያ ክልል በአሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫ ረቂቅ አዋጅ ላይ ለፓርላማ ያቀረበው የሕጋዊነት ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ

የኦሮሚያ ክልል በፌዴራል መንግሥት ተረቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የአሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫ ረቂቅ አዋጅ ሕገ መንግሥታዊ  አለመሆኑን በመጥቀስ እንዳይፀድቅ በተደጋጋሚ ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት አግኝቶ፣ በረቂቅ አዋጁ ላይ ከፍተኛ ማሻሻያ ተደርጎ በፓርላማው ፀደቀ። የኦሮሚያ ክልል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ረቂቅ አዋጁ በሕገ መንግሥቱ ለክልሎች የተሰጠውን ሥልጣን ከግምት ያላስገባና ለመተግበር አስቸጋሪ ሆኖ በመዘጋጀቱ ሊፀድቅ እንደማይገባው በመጥቀስ የሕግ ሰነዱን ላመነጨው የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ባለሥልጣን፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ እንዲሁም ረቂቅ አዋጁን በዝርዝር እየተመለከተ ለነበረው የፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ አቤቱታውን በደብዳቤ በተደጋጋሚ መግለጹን መዘገባችን ይታወሳል።

የዘርፍ ምክር ቤቶች ውጭ ሄደው በቀሩ አመራሮች ምትክ አዲስ ኃላፊዎችን ሰየሙ

የኢትዮጵያ የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከአገር ወጥተው በዚያው በቀሩት ፕሬዚዳንቱ ምትክ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሰየመ፡፡ የኦሮሚያና የአማራ የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶችም እንደወጡ በቀሩት ኃላፊዎች ምትክ ነባሮቹን ምክትል ፕሬዚዳንቶች በተጠባባቂ ፕሬዚዳንትነት እንዲሠሩ መመደባቸው ታውቋል፡ ከዘርፍ ምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው፣ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሆነው በምክር ቤቱ ቦርድ አባላት የተሰየሙት የሶማሌ ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንትና የኢትዮጵያ ዘርፍ ምክር ቤት ቦርድ አባል ሐሰን አብዱላሂ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት 14 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አፀደቀ

ረቡዕ ጥር 9 ቀን 2010 ዓ.ም. የተሰበሰበው የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ተግባራዊ የሚደረግ 14 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አፀደቀ፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ግንቦት 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ተሰብስቦ የ2010 በጀት 320 ቢሊዮን ብር እንዲሆን ማፅደቁ ይታወሳል፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዚህ ግዙፍ በጀት ላይ 14 ቢሊዮን ብር እንዲጨመር በመወሰኑ፣ የበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ በ334 ቢሊዮን ብር የሚከናወኑ ሥራዎች ይኖሩታል፡፡

ከሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉ 86 ሺሕ ዜጎች የመኖሪያ ቤቶች ሊሠሩ ነው

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም እየተደረገ ባለው ጥረት፣ የኦሮሚያ ክልል 86 ሺሕ ለሚሆኑ ዜጎች መኖሪያ ቤቶች ሊሠራ መሆኑን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

‹‹በታሪካችን በየትኛውም ጊዜ ዓይተነው የማናውቀው ተማሪ ሌላ ተማሪን የሚገድልበት ሁኔታ ተፈጥሯል››

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር (ኢሕአዴግ) ኢትዮጵያን መምራት ከጀመረ ከሃያ ስድስት ዓመታት በላይ ተቆጥሯል፡፡ ፓርቲው አገሪቱን በመምራት ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ ባስቆጠረበት ጊዜ ውስጥ አንፃራዊ ሰላምና መረጋጋት ሰፍኖ ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ እየተከሰቱ ባሉ ሕዝባዊ ተቃውሞዎችና ግጭቶች፣ የአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ከመታወኩም በላይ የዜጎች ሕይወት ጠፍቷል፣ ከመኖሪያ ቀዬአቸው ተፈናቅለዋል፡፡

የኦሮሚያ ዕጩ ተወዳዳሪዎችና ዕቅዶቻቸው

ከአጨቃጫቂው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፕሬዚዳንታዊና የሥራ አስፈጻሚ ምርጫ በተጓዳኝ ከኦሮሚያ ክልል ተወክለው በዕጩነት የቀረቡት ተወዳዳሪዎች፣ ቢመረጡ በቀጣይ የሚሠሩዋቸውን ሥራዎችና ዕቅዶቻቸውን በባለድርሻ አካላት አስገመገሙ፡፡ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለስምንት ዓመት የሚያገለግል ስትራቴጂካዊ ዕቅድ አቅርበዋል፡፡

የስ ውኃ በደመወዝ ጭማሪ ምክንያት በተደረገ የሥራ ማቆም አድማ 89 ሠራተኞቹን አሰናበተ

የደመወዝ ጭማሪን ምክንያት በማድረግ በተፈጠረ አለመግባባት የስ ፉድና ቤቨሬጅ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ 89 የሚሆኑ ሠራተኞቹን ከሥራ መሰናበቱን አስታወቀ፡፡ በዚህም ሳቢያ ኩባንያው በከፊል ማምረት ማቆሙን ማወቅ ተችሏል፡፡

ፍርድ ቤት የእነ አቶ በቀለ ገርባ መከላከያ ምስክሮች እንዳይቀርቡ የሰጠው ትዕዛዝ ተቃውሞ ገጠመው

በአቶ አያና ጉርሜሳ የክስ መዝገብ የተካተቱት እነ አቶ በቀለ ገርባ በመከላከያ ምስክርነት የቆጠሯቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ አቶ ለማ መገርሳ፣ ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) እና ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ቀርበው እንዲመሰክሩ ያቀረቡትን ጥያቄ፣ ፍርድ ቤቱ ውድቅ በማድረጉ በተከሳሾቹ ተቃውሞ ቀረበ፡፡

ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በምስክርነት እንዳይቀርቡ የተሰጠው ውሳኔ ተቃውሞ አስነሳ

በእነ ጉርሜሳ አያኖ የክስ መዝገብ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ለተከሰሱ አራት ተጠርጣሪዎች ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ የተጠየቀውን፣ ፍርድ ቤት ሐሙስ ጥር 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ሙሉ በሙሉ ውድቅ በማድረጉ ተከሳሾች ተቃውሞ አሰሙ፡፡

የተጠረጠሩ ዜጎችን ወደ ሕግ ለማቅረብ የኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች አመራሮች ዳተኝነት እንዳለባቸው ተገለጸ

ከወራት በፊት በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ተቀስቅሶ የበርካቶችን ሕይወት ለቀጠፈውና በመቶ ሺሕ ለሚቆጠሩት መፈናቀል ምክንያት በሆነው ግጭት እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች ወደ ሕግ ከማቅረብ አኳያ፣ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አመራሮች ዘንድ ዳተኝነት እንዳለ ተነገረ፡፡