Skip to main content
x

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሳምንት ክራሞት

ከተመረጡ ሁለት ሳምንታት ያስቆጠሩት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሥልጣናቸውን በተረከቡ በቀናት ውስጥ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሥራ ጉብኝት በማድረግ፣ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር በመገናኘት ውይይት እያደረጉ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

ለበጎ የታሰበው ክፋት እንዳያበላሸው!

በመላ አገሪቷ አንፃራዊ ሰላምና መረጋጋት ሰፍኖ ኢትዮጵያውያን በተስፋ ተሞልተው የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን እያከናወኑ መሆናቸው፣ አገሩን ለሚወድ ማንኛውም ሰው ዕፎይታ ይሰጣል፡፡ ኢትዮጵያውያን ለጋራ ዓላማ አብረው ለመሠለፍ የሚያስችላቸው ጅማሬ እየታየ በመሆኑ፣ ብዙዎች መጪውን ጊዜ በብሩህ ተስፋ ተሞልተው ቢጠብቁ አይገርምም፡፡

የዕርቀ ሰላም ጅማሬ

ቅዳሜ መጋቢት 29 ቀን 2010 ዓ.ም. ወደ ሶማሌ ክልል ያቀኑት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አጋጥሞ የነበረው ግጭት ‹‹ያልተገባ፣ ከኢትዮጵያዊነት ባህል ያፈነገጠና የሁላችንንም አንገት ያስደፋ የሽንፈት ታሪካችን ነው፤›› በማለት ከኅብረተሰቡ ለተወከሉ የኮንፈረንስ ተሳታፊዎች ንግግር አድርገው ነበር፡፡ ከሁለቱም ክልሎች በርካታ ዜጎች ለሕልፈት የተዳረጉበትን፣ በርካቶች ለአካል ጉዳት የተጋለጡበትንና ከ700 ሺሕ በላይ የተፈናቀሉበትን ግጭት በዕርቀ ሰላም እንዲቋጭም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አንገት ከመድፋት መውጣት የሚቻለው ሕዝብ ሲደመጥ ብቻ ነው!

መሰንበቻውን መነጋገሪያ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በሶማሌ ክልል ከሕዝብ ተወካዮች ጋር ያደረጉት ውይይት ነው፡፡ የጉብኝታቸውና የውይይታቸው ዓላማ በመስከረም 2010 ዓ.ም. በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ሥፍራዎች የተቀሰቀሰው ግጭት ያደረሰው ጥፋት ነው፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ የተመራ የልዑካን ቡድን ወደ ጅግጅጋ አመራ

በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የተመራ የልዑካን ቡድን ቅዳሜ መጋቢት 29 ቀን 2010 ዓ.ም. በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች ድንበር አካባቢ ላይ ተከስቶ የነበረውን ግጭት በዘላቂነት ለመፍታት ወደ ጅግጅግ አቅንቷል፡፡

ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር በሁሉም ክልሎች ሕዝባዊ ውይይቶች ሊካሄዱ ነው

በአገሪቱ ላለፉት ሦስት ዓመታት ያህል የተከሰተውን ችግር ለመቅረፍና ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር፣ በሁሉም ክልሎች ሕዝባዊ ውይይቶች ሊካሄዱ እንደሆነ ታወቀ፡፡ የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ከተጠናቀቀ በኋላ በመላ አገሪቱ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠርና በየአካባቢው የሚፈጠሩ ችግሮችን ለማስወገድ፣ በሁሉም ክልሎች ሕዝባዊ ውይይቶች እንዲካሄዱ ውሳኔ መተላለፉን አንድ የኢሕአዴግ የምክር ቤት አባል ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

‹‹የሥልጣን ፍላጎት ለጥቅም ቡድኖች መፈጠርና መሻኮት የተመቸ ሆኗል›› የኢሕአዴግ ምክር ቤት

የኢሕአዴግ ብሔራዊ ምክር ቤት ዓርብ መጋቢት 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ አገሪቱ ወደ ቀውስ እንድትገባና አገራዊ ህልውናን የመፈታተን ጠንቅ ያጋጠመበት አንዱ ምክንያት፣ የሥልጣን ፍላጎት ለጥቅም ቡድኖች መፈጠርና መሻኮት የተመቸ ሁኔታ በመፍጠሩ እንደሆነ አስታወቀ፡፡

ኢትዮጵያ የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ፖሊሲ እንድታወጣ ተጠየቀ

በኢትዮጵያ የሚስተዋለው የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም በችግሮች የተተበተበ ስለሆነ፣ ችግሮቹን ለመፍታት መንግሥት የአጠቃቀም ፖሊሲ እንዲያወጣ ተጠየቀ፡፡ ይህ ጥያቄ የቀረበው ከሁሉም የአገሪቱ ክልሎች ከተውጣጡ ወጣቶች ሐሙስ መጋቢት 20 ቀን 2010 ዓ.ም. በጁፒተር ሆቴል የፓናል ውይይት በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡

ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን በሌላ ሥፍራ ማስፈር እንዲቆም መድረክ ጠየቀ

ለዘመናት ኑሮዋቸውን መሥርተውና ማኅበራዊ ትስስር ፈጥረው ከሚኖሩባቸው አካባቢዎች ተገደው የተፈናቀሉ ዜጎችን መብት በማስከበር መንግሥት ወደ ቀዬአቸው ተመልሰው እንዲቋቋሙ ማድረግ ሲገባው፣ ተፈናቃዮቹ ወደማያውቋቸው ሩቅ አካባቢዎች ወሰዶ የማስፈር ዕቅድ አንድምታው ለአገሪቱ አንድነትና ለሕዝቡም አብሮነት አደጋ እንዳለው፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) አስታወቀ፡፡