Skip to main content
x

የጣልያኑ ጨርቃ ጨርቅ አምራች ከኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ምርት መላክ ጀመረ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በአውሮፓ ጉብኝታቸው ቀዳሚ ካደረጓት ጣልያን ባለሥልጣናትና ባለሀብቶች ጋር በተወያዩበት ወቅት የተሳተፈውና ካርቪኮ ግሩፕ የተሰኘው የጨርቃ ጨርቅ ኩባንያ ምርቶቹን ለአውሮፓ ገበያ ማቅረብ ጀመረ፡፡

የኢትዮጵያን የውጭ ግንኙነትና ደኅንነት ፖሊሲ ማሻሻል ለምንና እንዴት?

ሁለት አሠርት ዓመታት ለመሙላት ጥቂት ጊዜ የቀረውንና በሥራ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና አገራዊ ደኅንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ ለማሻሻል እየተሠራ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና የአገራዊ ደኅንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር ከገባ 17 ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ይኼንን ፖሊሲና ስትራቴጂ በፊታውራሪነት ያረቀቁት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ነበሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ የኢትዮጵያን የለውጥ ጉዞና መፃኢ ዕድሎች ለዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ታዳሚዎች ያስረዳሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የበርካታ አገሮች መሪዎችና ተፅዕኖ ፈጣሪ ባለሀብቶችና የዓለም አቀፍ ተቋማት አመራሮች በሚታደሙበት የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም (መድረክ) ተገኝተው፣ በእሳቸው አመራር በኢትዮጵያ ስለተጀመረው የለውጥ ጉዞና መፃኢ ዕድሎች ረቡዕ ጥር 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ከቀትር በኃላ ያስረዳሉ።

የገንዘብ ተቋማት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ለታቀደው የ29 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክት ድጋፋቸው ተጠየቀ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ከገንዘብ ተቋማት ኃላፊዎች ጋር መክረዋል፡፡ የውይይቱ አጀንዳ አስቀድሞ ባይገለጽም የሁሉንም ባንኮችና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ሥራ አስፈጻሚዎችና የቦርድ ሰብሳቢዎች በውይይቱ ተሳትፈው ነበር፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይትና ድርድር የሚመራበት ረቂቅ ደንብ ፀደቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያዘጋጀው ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ በቀጣይ የሚያደርጉት ውይይትና ድርድር የሚመራበት 16 አንቀጽ ያለው ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይተው ማፅደቃቸውን፣ በውይይቱ ከተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለማወቅ ተችሏል፡፡

ኃላፊነት በጎደላቸው ድርጊቶች ምክንያት አገር አይታመስ!

ሕዝብና አገርን ችግር ውስጥ የሚከቱ ኃላፊነት የጎደላቸው ድርጊቶች እየተበራከቱ ነው፡፡ እነዚህ ድርጊቶች በአመዛኙ እየተፈጠሩ ያሉት ለሕዝብም ሆነ ለአገር ኃላፊነት በማይሰማቸው ወገኖች ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በይፋ መንበረ ሥልጣኑን ከተቆጣጠሩ ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም

የኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ተሻጋሪ ግንኙነት ሕግ እየተበጀለት ነው

ኢትዮጵያና ኤርትራ የሚጋሯቸውን ድንበሮች ለማቋረጥ ሕጋዊ ሰነድ መያዝ እንዲቻል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እየሠራ እንደሆነ ታወቀ፡፡ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ዕርቅ ከተደረገ በኋላ የሁለቱ አገሮች ዜጎች እንዳሻቸው ድንበር እየተሻገሩ ዘመድ ሲጠይቁ፣ ሲጎበኙና ሲነግዱ የነበረ ቢሆንም፣ ይኼንን ግንኙነት ፈር ለማስያዝ ሁለቱ አገሮች ለሚፈራረሟቸው ስምምነቶች በመዘጋጀት ላይ መሆናቸውን ሪፖርተር ከምንጮች ለማረጋገጥ ችሏል፡፡

የአገር ጉዳይ የልጆች ጨዋታ አይደለም!

በዚህ ዘመን ምራቃቸውን የዋጡ ሰዎች የወጣቶች መካሪ፣ የአገር ሽማግሌ፣ የትውልድ አርዓያና የተጣመመውን የሚያቀና መሆን ሲገባቸው፣ እንደ ሠፈር ጎረምሳ የብጥብጥና የሁከት ምንጭ ሲሆኑ ያሳዝናል፡፡ በፖለቲካው መስክ ከ40 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠሩ ፖለቲከኞችና የሚመሩዋቸው ድርጅቶች አድረው ቃሪያ ሲሆኑ ያሳፍራል፡፡ ለዓመታት በመሣሪያ ያልተሳካላቸውንና በሰላማዊ ጥሪ ያገኙትን መልካም አጋጣሚ የሚያበላሹ ያሳቅቃሉ፡፡

አቶ ንጉሡ ጥላሁን የጠቅላይ ሚኒስትሩን የፕሬስ ሴክሬታርያት ኃላፊነት ተረከቡ

የቀድሞ የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን፣ የፈረሰውን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤትን በመተካት የተቋቋመውን የጠቅላይ ሚኒስትሩን የፕሬስ ሴክሬታርያት ኃላፊነት ተረከቡ፡፡