Skip to main content
x

የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት መታመማቸው ተሰማ

ከተሾሙ ጥቂት ዓመታት ያስቆጠሩት የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት ጋትሉዋክ ቱት የጤና ችግር እንደገጠማቸው ምንጮች ገለጹ፡፡ የሪፖርተር ምንጮች ፕሬዚዳንቱ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የጤና ዕክል እንደገጠማቸው፣ በተደጋጋሚ በአገር ውስጥ ሕክምና ሲከታተሉ መቆየታቸውን ያስረዳሉ፡፡ የገጠማቸውን የጤና እክል ከመናገር የተቆጠቡት የሪፖርተር ምንጮች፣ ፕሬዚዳንቱ በጦር ኃይሎች ሆስፒታል ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ቢቆዩም በጤናቸው ላይ ለውጥ ሊታይ አልቻለም፡፡ ሆስፒታሉ ውጭ አገር ሄደው የተሻለ ሕክምና እንዲያገኙ በመወሰን ሪፊር የጻፈላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የቀድሞ የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነርን ጨምሮ 29 ተከሳሾች ጥፋተኛ ተባሉ

በጋምቤላ ክልል በማዣንግ ዞን ጎደሬ ወረዳ ሜጢ ከተማ ውስጥ በተፈጠረ ግጭት ለ79 ሰዎች ሞት፣ ለ27 ሰዎች ከፍተኛና ዝቅተኛ የአካል መጉደል፣ ለ273 መኖሪያ ቤቶች መቃጠል፣ ከ13,000 በላይ ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው እንዲፈናቀሉ አድርገዋል ተብለው ክስ የተመሠረተባቸው፣ የቀድሞ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነርን ጨምሮ 29 ተከሳሾች ጥፋተኛ ተባሉ፡፡

በድንበር አካባቢ የጠረፍ ንግድ ቢፈቀድም ቤንሻንጉል ጉምዝና ጋምቤላ ተጠቃሚ አይደለንም አሉ

ክልሎች ኢትዮጵያን ከሚያዋስኑ ጎረቤት አገሮች ጋር በ90 ኪሎ ሜትር ክልል ውስጥ የጠረፍ ንግድ እንዲያካሂዱ የፌዴራል መንግሥት ቢፈቅድም፣ በተለይ የቤንሻንጉል ጉምዝና የጋምቤላ ክልሎች ተጠቃሚዎች አይደለንም አሉ፡፡ የፌዴራል መንግሥት በጠረፍ አካባቢ የሚገኙ ክልሎች አገሪቱን ከሚያዋስኑ ክልሎች ጋር እንዲነግዱ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡ ነገር ግን በአንፃራዊነት ሶማሌ፣ አፋርና ቦረና አካባቢ የሚገኙ ሕዝቦች ከሶማሊያና ከሶማሌላንድ፣ ከጂቡቲና ከኬንያ ጋር በተሻለ ደረጃ እየተገበያዩ ነው፡፡

ካሩቱሪ በኢትዮጵያ የነበሩትን እርሻዎች እንደ አዲስ ለማስጀመር መቃረቡን አስታወቀ

የህንድ የግብርና ምርቶች ኩባንያ ካሩቱሪ ግሎባል በኢትዮጵያ ሲንያንቀሳቅሳቸው የነበሩና በመንግሥት የተወረሱበትን እርሻዎች ዳግም እንደ አዲስ ለማስጀመር፣ ከመንግሥት ጋር ዕርቅ ማውረዱን አስታወቀ፡፡ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥም እንደ አዲስ ስምምነት በመፈረም በጋምቤላ እርሻው ሥራ እንደሚጀምር ገለጸ፡፡

የጋምቤላ ከተማ የባጃጅ ሾፌሮች አገልግሎት አቆሙ

በጋምቤላ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባጃጆች ዛሬ የካቲት 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ጠዋት ጀምሮ አገልግሎት ማቆማቸውን የሪፖርተር ምንጮች ከስፍራው አስታውቀዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የአካባቢው ነዋሪዎች በትራንስፖርት እጦት እንደተቸገሩ ተናግረዋል፡፡

የባጃጅ ሾፌሮቹ ሥራ ያቆሙት አላግባብ ከፍተኛ ግብር እንድንከፍል ተጥሎብናል በማለት ሲሆን፣ የከተማው አስተዳደር ከሾፌሮቹ ጋር ውይይት ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ምንጮች ከስፍራው ገልጸዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በተቀሰቀሰ ተቃውሞ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

በኦሮሚያ ክልል ከሰኞ የካቲት 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ እንደ አዲስ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ የንግድና የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች በሙሉ ተገትተው ከመቆየታቸውም በላይ በሰው ሕይወትና በአካል ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ በንብረት ላይም ቀላል የማይባል ጉዳት መድረሱ ታውቋል፡፡

በገቢዎች ጽሕፈት ቤት ቃጠሎ ምክንያት የጋምቤላ ከተማ ከንቲባ ከምክትላቸው ጋር ከሥልጣን ተነሱ

ኅዳር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽሕፈት ቤት በእሳት ቃጠሎ ከወደመ በኋላ፣ ተገቢውን ዕርምጃ አልወሰዱም በሚል ምክንያት የከተማው አስተዳደር ከንቲባ አቶ አኬኔ ኦፓዳ እና ምክትላቸው አቶ ጀምስ ኬች ከሥልጣናቸው ተነሱ፡፡ የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋሕዴን) ለሳምንት ያህል ግምገማ ሲያካሂድ ቆይቶ፣ ጥር 10 ቀን 2010 ዓ.ም. የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና ምክትላቸው ጥፋተኞች ናቸው በማለት ከሥልጣናቸው ማንሳቱ ታውቋል፡፡

የዓለም ባንክ የ13 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ባላቸው ፕሮጀክቶች አማካይነት ድጋፍ እየሰጠ እንደሚገኝ አስታወቀ

የዓለም ባንክ በቅርቡ ይፋ ያደረገውን የኢትዮጵያ የአጋርነት ማዕቀፍ የድጋፍ ሰነድን በማስመልከት ባለፈው ሳምንት እንዳስታወቀው፣ በኢትዮጵያ የ13 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ባላቸው ፕሮጀክቶች አማካይነት ለአገሪቱ ድጋፍ እያደረገ ነው፡፡

ላቀረቡት ምርት ክፍያ ያጡ አገር በቀል ኩባንያዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አቤቱታ አቀረቡ

ለቱርክ ኩባንያ ኤልሲ አዲስ ኢንዱስትሪያል ዴቨሎፕመንት ጥጥ በብድር ሲያቀርቡ የቆዩ 12 አገር በቀል ኩባንያዎች ክፍያ ስላልተፈጸመላቸው ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን በመግለጽ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የኢኮኖሚ ዕቅድ ውጤታማነት ክትትልና ድጋፍ ዘርፍ ኃላፊ አርከበ ዕቁባይ (ዶ/ር) መፍትሔ እንዲሰጧቸው ጠየቁ፡፡