Skip to main content
x

በቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንትና ሌሎች ባለሥልጣናት ላይ ምርመራ ተጠናቀቀ

በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማና በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ የዞንና የወረዳ ከተሞች በተፈጸመ ወንጀል ተጠርጥረው በምርመራ ላይ በነበሩት፣ የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ በአራት ባለሥልጣናት ላይ ምርመራ መጠናቀቁን የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን አስታወቀ፡፡

ፖሊስ በእነ አቶ አብዲ መሐመድ ላይ ሲያደርግ የቆየውን ምርመራ ማጠናቀቁን አስታወቀ

ፖሊስ በቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድ (አብዲ ኢሌ)፣ ራሕማ መሐመድና ፈርሃን ጣሂር ላይ ሲያደርግ የቆየውን ምርመራ አጠናቅቆ መዝገቡን ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ማስተላለፉን ዛሬ ዓርብ ጥር 10 ቀን 2011 ዓ.ም. ለፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

የኢትዮ ጂቡቲ ዋና መንገድ ቢከፈትም ሥጋቶች እንዳሉ ተጠቆመ

ከቀናት በፊት በአፋር ክልል በሚገኙ ቀበሌዎች ባገረሸው ግጭት ሳቢያ የኢትዮ ጂቡቲ ዋና መንገድን ጨምሮ፣ ከክልሉ ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚያቀኑ መንገዶች ለቀናት ተዘግተው ቢከፈቱም አሁንም ሥጋቶች እንዳሉ ታወቀ፡፡

ፍርድ ቤቶች ነፃና ገለልተኛ ሆነው መሥራት አለመቻላቸውን ፕሬዚዳንቷ ተናገሩ

የፌዴራልም ሆኑ የክልል ዳኞች የሕግ የበላይነትን ለማስከበር በሕገ መንግሥቱ ከፍተኛ ኃላፊነት የተጣለባቸው ቢሆንም፣ የዳኝነት ነፃነታቸው በአስፈጻሚውና በሌሎች አካላት ጣልቃ ገብነት ምክንያት በመገደቡ ገለልተኛ እንዳልነበሩ፣ ዜጎችም በዳኝነት አካሉ ላይ አመኔታ እንዳይኖራቸው ማድረጉን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ተናገሩ፡፡

በሞያሌ የተቀሰቀሰው ግጭት እየተባባሰ ነው

ሰሞኑን በሞያሌ ከተማ ለዘመናት አብረው በኖሩት የኦሮሞና የሶማሌ ተወላጆች መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት ከመረጋጋት ይልቅ እየባሰበት መምጣቱን፣ የሁለቱም ተወላጆች ወደ አጎራባች ኬንያ መሰደድ መቀጠላቸውን ሪፖርተር ያነጋገራቸው ምንጮች ገለጹ።

ሰሞኑን በሞያሌ ባገረሸ የእርስ በርስ ግጭት በርካቶች ተገደሉ

ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ሞያሌ ከተማ በኦሮሞዎችና በሶማሌዎች መካከል ዳግሞ ያገረሸው ግጭት ለተከታታይ ሦስት ቀናት መብረድ ባለመቻሉ፣ የበርካቶችን ሕይወት ቀጥፏል፡፡ የሶማሌ ክልል ዓርብ ታኅሳስ 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ በግጭቱ ከሶማሌ ወገን ብቻ 21 ሰዎች መገደላቸውንና በ66 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን አስታውቋል።  

በጅግጅጋና አካባቢው በእምነት ተቋማት ላይ የደረሰው ውድመት ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑ ተገለጸ

ከሐምሌ 26 እስከ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማና በአካባቢው በተፈጸመ የእሳት ቃጠሎ የወደሙት የኦርቶዶክስ የእምነት ተቋማት ግምት ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ መርማሪ ቡድን አስታወቀ፡፡

የታሰሩት የሶማሌ ክልል ባለሥልጣናት ልዩ ኃይል በማሰማራት በኦሮሚያና ሶማሌ አዋሳኝ ላይ 200 ሰዎች ማስገደላቸው ተገለጸ

የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙት ሌሎች ባለሥልጣናት፣ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ቦታዎች ልዩ የፖሊስ ኃይል በማሰማራት ከ200 በላይ ሰዎችን አስገድለው በጅምላ እንዲቀበሩ ማድረጋቸውን፣ የፌዴራል ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስረዳ፡፡

በሶማሌ ክልል በተፈጸሙ የወንጀል ድርጊቶች የተጠረጠሩት ግለሰብ ከፕሬዚዳንቱ ጋር ግንኙነት እንደነበራቸው ተነገረ

በሶማሌ ክልል ከሐምሌ 26 እስከ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ተፈጥሮ በነበረው  ሁከትና ብጥብጥ ምክንያት ከተፈጸመ ግድያ፣ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት፣ ዘርን መሠረት ያደረገ ጥቃትና ማፈናቀል፣ የሃይማኖት ተቋማት ቃጠሎና ንብረት ዘረፋ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው የታሰሩት አቶ ቴዎድሮስ አዲሱ (ቴዲ ማንጁስ)፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት ከነበሩት አቶ አብዲ መሐመድና ከሌሎች ባለሥልጣናት ጋር ግንኙነት እንደነበራቸው ለፍርድ ቤት ተነገረ፡፡

በጅግጅጋ ከተማ በተፈጠረ ግጭት ሦስት ሰዎች ተገደሉ

በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በሳምንቱ በተፈጠረ ግጭት የሦስት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ አራት ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት ደረሰባቸው፡፡ ሰኞ ጥቅምት 19 ቀን 2011 ዓ.ም. የተወሰኑ ወጣቶች በከተማው ቀበሌ 04 በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ በቅርቡ ከተማዋ ላይ ብጥብጥ ለማስነሳት አስባችኋል በሚል ተጠርጥረው የታሰሩ ጓደኞቻቸውን በኃይል ለማስፈታት ሞክረው እንደነበር፣ በዚህም ፖሊስ ስድስት ወጣቶችን በማሰር ችግሩን ለማረጋጋት እንደቻለ የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጉሌድ አውሎ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡