Skip to main content
x

ኬኬ ድርጅት በጣና ሐይቅ ላይ የተንሰራፋውን እምቦጭ አረም ለማስወገድ 20 ሚሊዮን ብር ዕርዳታ ሰጠ

ኬኬ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ከስድስት ዓመታት በፊት ጀምሮ፣ በጣና ሐይቅ ላይ የተንሰራፋውንና በርካታ ኢትዮጵያውያን ለማጥፋት እየተረባረቡ የሚገኙትን እምቦጭ አረም፣ ሙሉ በሙሉ እንዲወገድ የ20 ሚሊዮን ብር ዕርዳታ ሰጠ፡፡

በፖለቲካ  አለመረጋጋት ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ፕሮጀክቶች ግማሽ ቢሊዮን ብር ካሳ ተሰጠ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በአንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ በተቀሰቀሰው አለመረጋጋት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ከ200 በላይ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች፣ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ካሳ መክፈሉን አስታወቀ፡፡

‹‹የፖለቲካ ቀውሱ በውጭ ኃይሎች እንዳይጠለፍ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል››

በአገሪቱ የተፈጠረው የፖለቲካ ቀውስ በውጭ ኃይሎች እንዳይጠለፍ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ሲል፣ ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ አስጠነቀቀ፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን የተቃወሙት ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆኑ የተለያዩ አገሮችና ሌሎች የውጭ ኃይሎችም ናቸው ያለው አትሌቱ፣ አዋጁ የሚጎዳው እንደ እሱ ዓይነቱን ኢትዮጵያዊ እንጂ የውጭ ኃይሎችን ባለመሆኑ፣ የፖለቲካ ቀውሱ በሌሎች ሊጠለፍ እንደሚችል ሥጋት እንዳለው ገልጿል፡፡

የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ኢትዮጵያ የተከተለችውን የቱሪስቶች የቆይታ ጊዜና የገቢ ስሌት ውድቅ አደረገ

በዚህ ዓመት የመጀመርያዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ መንግሥት ከቱሪዝም ዘርፍ ከ1.8 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታውቆ ነበር፡፡ ይሁንና ይህ ገቢ የተሰላበትን መንገድ ውድቅ የሚያደርጉ ትንታኔዎች ከዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ብቅ ብለዋል፡፡

በአማራ ክልል ውስን ከተሞች የንግድ ተቋማት ተዘግተው ነበር

በአማራ ክልል በሚገኙ ውስን ከተሞች ለሁለት ቀናት የንግድ ተቋማት ተዘግተው እንደነበር ታወቀ፡፡ በማኅበራዊ ሚዲያ በተጠራው ቤት ውስጥ የመዋል አድማ በአማራ ክልል በተለይም በጎንደርና በባህር ዳር ከተሞች የንግድ ተቋማት ተዘግተው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡

የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱና የንግሥት ይርጋ ክስ ተቋረጠ

በወልቃይት ምክንያት በተፈጠረ ውዝግብና ግጭት የሽብር ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው በሒደት ላይ የነበሩት ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱና ንግሥት ይርጋ ክሳቸው ተቋረጠ፡፡ ከስምንት ዓመታት በፊት የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤት የሚገኙት ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ፣ ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ፣ ኮሎኔል ደምሰው አንተነህና ሌሎች ፍርደኞች በይቅርታ እንዲፈቱ፣ የፌዴራል ይቅርታ ቦርድ ወስኖ ለአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ተላለፈ፡፡

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ለየት ያሉ ውሳኔዎችን እንደሚያስተላልፍ ተጠቆመ

የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ከዚህ በፊት ከነበሩት ለየት ያሉ ውሳኔዎች እንደሚያስተላልፍ ተጠቆመ፡፡ የብአዴን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዓለምነው መኮንን፣ የክልሉን ሕዝብ ችግሮች በዘላቂነት ሊፈታ የሚያስችልና ከዚህ በፊት ይተላለፉ ከነበሩት ለየት ያሉና ጠንካራ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የአማራ ክልል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በመከላከያ ምስክርነት ተቆጠሩ

በአማራ ክልል በጎንደር ከተማና ሰሜን ጎንደር በተለያዩ ወረዳዎች ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ከግንቦት ሰባት አመራሮች ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ አመፅ በማስነሳትና በመምራት በግልና በመንግሥት ንብረት ላይ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው ክስ የተመሠረተባቸው እነ ንግሥት ይርጋ፣ የክልሉን ፕሬዚዳንት ጨምሮ በርካታ ባለሥልጣናትን በመከላከያ ምስክርነት ቆጠሩ፡፡