Skip to main content
x

ሥርዓተ አልበኝነት ይቁም!

አገር በለውጥ ማዕበል ውስጥ ሆና ወጣ ገባ የሚሉ ችግሮች ማጋጠማቸው ያለ ነው፡፡ ነገር ግን ሕገወጥነት ነግሦ ሥርዓተ አልበኝነት ሲሰፍን ደግሞ ቆም ብሎ ማሰብ ይገባል፡፡ መንግሥት ባለበት አገር ውስጥ ሕግ ማስከበር ካልተቻለ፣ ወዴት እየሄድን ነው በማለት አጥብቆ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል፡፡

በንፁኃን ሕይወት የሚቆምሩ ለፍርድ ይቅረቡ!

መሰንበቻውን በምሥራቁ የአገሪቱ ክፍል እየተስተዋለ ያለው አሳዛኝ ድርጊት የአገር ህልውናን እየተፈታተነ ነው፡፡ በሶማሌ ክልል በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው ግድያ፣ ዘረፋና ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ከባድ ጊዜ ውስጥ እንዳለን ያሳያል፡፡

የጥላቻና የቂም በቀል ምዕራፍ ይዘጋ!

የኢትዮጵያ የግማሽ ክፍለ ዘመን ፖለቲካ እጅግ በጣም ከመወሳሰቡ የተነሳ፣ በወንድማማቾች መካከል የጥላቻና የቂም በቀል አጥር አበጅቷል፡፡ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ችግርን ፈቶ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ከማካሄድ ይልቅ፣ በጥላቻና በቂም በቀል በመመራረዝ ለአገር የሚጠቅሙ መልካም አጋጣሚዎች መክነው ቀርተዋል፡፡

ሕግና ሥርዓት ሲጠፋ አገር በረት ይሆናል!

በሕግና በሥርዓት የማይተዳደር አገር የሥርዓተ አልበኞች መፈንጫ ይሆናል፡፡ በተለይ አገር የፖለቲካ ሽግግር ውስጥ ስትሆን ሕግና ሥርዓት ካልኖረ ለትርምስ በር ይከፈታል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ ሥፍራዎች የሚሰሙት የግጭት፣ የሞትና የውድመት ዜናዎች እረፍት ይነሳሉ፡፡

ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በታሪክና በትውልድ ይዘከራሉ!

ሐሙስ ሰኔ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ማለዳ የተሰማው መርዶ ለመላ ኢትዮጵያውያን እጅግ በጣም አስደንጋጭ ነበር፡፡ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ የኢንጂነር ስመኘው በቀለ ድንገተኛ ሕልፈት ሲሰማ የሚሊዮኖች ልብ ተሰብሯል፡፡

ለበጎ የታሰበው ክፋት እንዳያበላሸው!

በመላ አገሪቷ አንፃራዊ ሰላምና መረጋጋት ሰፍኖ ኢትዮጵያውያን በተስፋ ተሞልተው የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን እያከናወኑ መሆናቸው፣ አገሩን ለሚወድ ማንኛውም ሰው ዕፎይታ ይሰጣል፡፡ ኢትዮጵያውያን ለጋራ ዓላማ አብረው ለመሠለፍ የሚያስችላቸው ጅማሬ እየታየ በመሆኑ፣ ብዙዎች መጪውን ጊዜ በብሩህ ተስፋ ተሞልተው ቢጠብቁ አይገርምም፡፡

ኢትዮጵያ የምትደምቀው በልጆቿ አንድነት ነው!

ኢትዮጵያ ታሪካዊ አገር ናት ሲባል ያለፈችባቸው ዘመናት ውስብስብ እንደነበሩም መዘንጋት አይቻልም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ የአገሩን ነፃነት ለማስከበር ያደረጋቸው ተጋድሎዎች፣ ለመብቱና ለነፃነቱ ያደረጋቸው ፍልሚያዎች፣ የማንነትና የሐሳብ ብዝኃነት ባለመስተናገዳቸው ሳቢያ የተፈጠሩ ግጭቶች፣ እንዲሁም ኢትዮጵያ ከሥልጣኔዋ ተለያይታ ለድህነትና ለተመፅዋችነት የተጋለጠችበት አሳፋሪ ውርደት የታሪኳ አካል ናቸው፡፡

የአመራር ለውጡ በስኬት እንዲታጀብ የድርሻን ማዋጣት ይገባል!

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢፌዴሪ) መንግሥት ከተመሠረተ ከ23 ዓመታት በኋላ፣ ሦስተኛው ጠቅላይ ሚኒስትር በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ተሰይመዋል፡፡ የመጀመርያው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሞት፣ ሁለተኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ መልቀቂያ በማቅረብ ሲሰናበቱ፣ ሦስተኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ለመጪዎቹ ሁለት ዓመታት ተተክተዋል፡፡ አገሪቱን ነውጥ ውስጥ በመክተት ቀውስ በፈጠረው የሦስት ዓመታት ያህል ተቃውሞ ምክንያት የመጡት የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ከፊታቸው ብዙ ሥራ ይጠብቃቸዋል፡፡

አዲስ የታሪክ ምዕራፍ እንዲጀመር ከማደናቀፍ መደጋገፍ ይቅደም!

ኢትዮጵያ ከአንድ የታሪክ ምዕራፍ ወደ ሌላው እየተሸጋገረች ዘመናትን ያስቆጠረች ባለታሪክ አገር ናት፡፡ ሌላው ቀርቶ ከዘመነ መሳፍንት ወደ ማዕከላዊ መንግሥት ምሥረታ፣ ከአሀዳዊ ወደ ፌዴራላዊ ሥርዓት የተሸጋገረችባቸው ታሪካዊ ሒደቶች በበርካታ ውጣ ውረዶች ታጅበው እዚህ ዘመን ላይ ተደርሷል፡፡

መሪ ከመተካት በላይ የተመሪው ሕዝብ ጉዳይ ያሳስባል!

ኢሕአዴግ ሊቀመንበሩን ለመምረጥ አንድ ሳምንት ስብሰባ ላይ ከርሟል፡፡ ተመራጩ ሊቀመንበር በፓርላማ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ ይሰየማል፡፡ ይህ የኢሕአዴግ አሠራር ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከኃላፊነት የመልቀቂያ ጥያቄ ካቀረቡበት ጊዜ ጀምሮ፣ ከአንድ ወር በላይ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አንዱ አነጋጋሪ ጉዳይ ተተኪውን መሰየም ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት የተተኪው ማንነት በተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ቢያነጋግር አይገርምም፡፡