Skip to main content
x

ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች ኤርትራን እየጎበኙ ነው

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ20 ዓመታት አቋርጦ የነበረውን የአስመራ በረራ ረቡዕ ሐምሌ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ሲጀምር፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች በኤርትራ ያሉ የኢንቨስትመንትና የንግድ ዕድሎችን ለመመልከት በኤርትራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡

ብሔራዊ ባንክ ከንግዱ ማኅበረሰብ አባላት ጋር በፋይናንስ ችግሮች ላይ ሊወያይ ነው

የንግድ ማኅበረሰቡ በፋይናንስ ተቋማት የብድር አሰጣጥና ሌሎች ችግሮች ላይ ቅሬታዎችና አቤቱታዎች በማቅረባቸው፣ ከብሔራዊ ባንክ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ምክክር ሊያደርጉ ነው፡፡

ሚያዚያ 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በሰጡት መመርያ፣ በፋይናንስ ተቋማት ላይ በቀረቡት አቤቱታዎች ላይ የብሔራዊ ባንክና የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ምላሽ እንዲሰጡበት አሳስበው ነበር፡፡

ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማሳሰቢያ ተፈጻሚ እንዲሆን የተሰጠው የጊዜ ገደብ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ቢሆንም፣ እስካሁን ሳይካሄድ ቆይቷል፡፡

ጆሮ ያጡ የኢኮኖሚው ሰንኮፎች በምሁራኑ አንደበት

በሳምንቱ መጀመርያ ‹‹የግሉ ዘርፍና ወቅታዊ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ፈተናዎቹና ዕደሎቹ›› በሚል ርዕስ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር፡፡ አንጋፋ የኢኮኖሚ ባለሙያዎችም ይህንኑ ሐሳብ በመንተራስ ሙያዊ ዕይታቸውን ለታዳሚው አካፍለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከዓለም ንግድ ምክር ቤቶች ጉባዔ አስተናጋጅነት ውጪ ሆነች

ኢትዮጵያ 22ኛውን የዓለም ንግድ ምክር ቤቶች ጉባዔ ለማስተናገድ ከአራት አገሮች ጋር ያደረገችው ውድድር ሳይሳካላት በመቅረቱ ጉባዔውን ለማዘጋጀት ዱባይ መመረጧ ታወቀ፡፡ ጉባዔው በአፍሪካ ይስተናገዳል ቢባልም ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ከሦስት ሺሕ ያላነሱ ተሳታፊዎች ይገኙበታል ተብሎ የሚጠበቀውን ይህንን ጉባዔ ለማዘጋጀት ኢትዮጵያን ጨምሮ አምስት አገሮች በተፎካካሪነት ቀርበው ነበር፡፡ ከተፎካካሪዎቹ ውስጥ ዕድሉን ያገኛሉ ተብለው ሲጠበቁ የነበሩት ኢትዮጵያና ኬንያ ነበሩ፡፡

የዓለም ንግድ ምክር ቤቶች ጉባዔ አዘጋጅነት ለተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ተሰጠ

ብዙ ተስፋ የተጣለበትና ኢትዮጵያና ኬንያ ተፋጥጠውበት የነበረው የዓለም ንግድ ምክር ቤቶች ጉባዔን የማዘጋጀት ዕድል ለተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ተሰጠ፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ ኬንያ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች፣ ጆርዳን፣ ኦማንና ኢራን ሲፎካከሩበት የነበረው የንግድ ምክር ቤቶች ጉባዔ ኢትዮጵያ እንዴት ልታሰናዳ እንደተዘጋጀች የሚያመለክተው ሰነድ ለዓለም ንግድ ምክር ቤቶች ጉባዔ ተልኮ እንደነበር ይታወሳል፡፡

የአማራ ንግድ ምክር ቤት ለወጪና ገቢ ንግድ የሱዳን ወደብን ለመጠቀም የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሊመክር ነው

ንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በክልሉ የሚደረገውን የወጪና ገቢ ንግድ እንቅስቃሴ የሚቃኝ የምክክር መድረክ በመጪው ቅዳሜ ግንቦት 4 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደሚያካሄድ አስታወቀ፡፡ ‹‹ገቢና ወጪ ንግድ በአማራ ክልል ዕድሎች፣ ተግዳሮቶችና የመፍትሔ ሐሳቦች›› በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሑፍ እንደሚቀርብና በዚሁ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ምክክር እንደሚደረግ ከክልሉ የንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡

የንግዱ ማኅበረሰብ አንገብጋቢ ያላቸውን ችግሮችና ቅሬታዎችን በማሰባሰብ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት መላክ ጀመረ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሚያዝያ 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት፣ የንግዱ ማኅበረሰብ ዋነኛ ችግሮች እንደሆኑ ተለይተው ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ይቻል ዘንድ መመርያና  ማሳሰቢያ ሰጥተው ነበር፡፡ በዚህ መሠረትም እስካሁን ከተሰባሰቡ ጥያቄዎች ውስጥ በርከት ያሉት ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መላካቸውን የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙስናን ተጠይፈው የመንግሥትን ነጋዴነት እንደሚያስቀጥሉ ያስታወቁበት የምክክር መድረክ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከንግዱ ማኅበረሰብ የመተዋወቂያ የምክክር መድረክ ሰኞ መጋቢት 9 ቀን 2010 ዓ.ም. አካሂደዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነጋዴዎቹን በተዋወቁበት የመጀመርያው ንግግራቸው ‹‹ከሀብታሞች ጋር ትገናኛለህ ስላሉኝና ደሃ መንግሥት እንዳልሆንኩ እንድታውቁ በማለት ሽክ ብዬ ነው የመጣሁት፤›› በማለት ለፈገግታና ለተግባቦት እንዲያዋዛላቸው በማድረግ መድረኩን አስጀምረዋል፡፡