Skip to main content
x

ኢትዮጵያ የአሰብ ወደብን ለመጠቀም እንቅስቃሴ ጀመረች

ግንኙነታቸውን ዳግም እያደሱ የሚገኙት የኢትዮጵያና የኤርትራ መሪዎች ከሃያ ዓመታት በኋላ የአሰብ ወደብ ሥራ እንዲጀምር ትዕዛዝ ሰጡ፡፡ሁለቱ መሪዎች በሰጡት ትዕዛዝ መሠረት በኢትዮጵያ በኩል የትራንስፖርት ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ማሪታይም ጉዳይ ባለሥልጣንና የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በጋራ ግብረ ኃይል አቋቁመዋል፡፡

ሶማሌላንድ በበርበራ ወደብ የምታካሂደውን የማስፋፊያ ግንባታ በመስከረም ወር እንደምትጀምር ታወቀ

ራሷን እንደቻለች ሉዓላዊት አገር ዕውቅና ለማግኘት በመጣጣር ላይ የምትገኘው ሶማሌላንድ፣ ኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስን በባለድርሻነት ያካተተውን የበርበራ ወደብ የማስፋፊያ ግንባታ በመጪው መስከረም ወር እንደምትጀምር አስታወቀች፡፡ የበርበራ ወደብ የኦፕሬሽን ሥራዎችን የሚመሩ ኃላፊዎች ሰሞኑን በወደቡ ጉብኝት ላደረጉ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ወቅት እንደታስወቁት፣ በሰኔ ወር የወደብ ግንባታውን ለሚያካሂዱ ኩባንያዎች ሥራው እንደሚሰጣቸውና በመስከረም ወርም  ግንባታ እንደሚጀምሩ ይጠበቃል፡፡

የኢትዮ ጂቡቲ ኮሪደር መንገድ በመበላሸቱ የተሽከርካሪዎች ምልልስ እየተስተጓጎለ ነው

ከሌሎች ጎረቤት አገሮች አንፃር ሲታይ ለመሀል ኢትዮጵያ ቅርብ የሆነው የጂቡቲ ወደብ ቢሆንም፣ በተለይ ከወደቡ እስከ ጋላፊ ድረስ ያለው 200 ኪሎ ሜትር መንገድ በመበላሸቱ፣ የተሽከርካሪዎችን ምልልስ ከማስተጓጎሉም በላይ፣ ለአላስፈላጊ የመለዋወጫ ዕቃዎች ወጪ እያደረጋቸው መሆኑን ባለንብረቶች አስታወቁ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመጀመሪያዎቹ የውጭ አገር ጉዞዎችና ውጤታቸው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከተሰየሙ ረቡዕ ሚያዚያ 24 ቀን 2010 ዓ.ም. አንድ ወር አስቆጥረዋል፡፡ በዚህ አንድ ወር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአገር ውስጥ ካሉ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ከመወያየት ባለፈ፣ ሥልጣን ከያዙ በጂቡቲ የመጀመርያቸውን፣ በሱዳን ደግሞ ሁለተኛቸው የሆነውን የሥራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

ኢትዮጵያ በጂቡቲ ወደብ በጋራ እንድታለማ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠየቁ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ኢትዮጵያ በጂቡቲ ወደብ በጋራ ለማልማት ዕድል እንዲሰጣት ለጂቡቲ መንግሥት ጥያቄ አቀረቡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄውን ያቀረቡት በጂቡቲ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሲያደርጉ፣ በሁለቱ አገሮችና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ከፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ ጋር ባደረጉት ውይይት መሆኑ ታውቋል፡፡

በጂቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጥያቄ

ከአንድ ሚሊዮን በታች (እንደ ዓለም ባንክ የዓምና ትንበያ ለ940 ሺሕ በላይ) የሚቆጠር ሕዝብ እንዳላት የሚነገርላት የጂቡቲ ሪፐብሊክ፣ ለበርካታ ኢትዮጵያውያን መኖሪያ እንደሆነች ይታወቃል፡፡ እርግጥ ነው የሁለቱ አገር ሕዝቦች በቋንቋ፣ በባህል፣ በአኗኗር፣ በሃይማኖትና በሌላም አኳኋን በደም የሚዛመዱ ብሔር ብሔረሰቦች የሚኖሩባት አገር ነች፡፡

የዶራሌ ሁለገብ ወደብ ከነባሩ ይልቅ በርካታ የተሻሻሉ አሠራሮችን እንዳመጣ አስታወቀ

ሥራ በጀመረ በወራት ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ የዋጋ ቅናሽ ማደረጉን ገልጿል ከወራት በፊት የተመረቀውና 580 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደጠየቀ የሚነገርለት የጂቡቲ የዶራሌ ሁለገብ ወደብ፣ 100 ሺሕ ቶን የጫኑ መርከቦችን ለማስተናገድና ዓመታዊ አቅሙም ከስምንት ሚሊዮን ቶን በላይ በመሆኑ ከነባሩ የተሻሻሉ አገልግሎቶችንና አሠራሮችን ይዞ መምጣቱን የወደብ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የጂቡቲ መንግሥት 70 በመቶውን የኢትዮጵያ የገቢና ወጪ ዕቃ የማስተናገድ ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ

ኢትዮጵያ በሌሎች አገሮች የወደብ አማራጮችን መፈለጓን እንደማይቃወም ገልጿል የጂቡቲ መንግሥት በዓመቱ የሚያስተናግደውን የኢትዮጵያ ወጪና ገቢ ዕቃዎች እስከ 70 በመቶ ለማስተናገድ የሚያስችሉትን መሠረተ ልማቶች በማሟላት ላይ እንደሚገኝ አስታውቆ፣ ከ60 እስከ 70 በመቶ የሚሆነውን የኢትዮጵያ ዕቃ ለማስተናገድ አቅም እየገነባ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡