Skip to main content
x

በሶማሌ ክልል የደረሰው ሰብዓዊና ፖለቲካዊ ቀውስ

በሶማሌ ክልል ሕዝቦችና ነዋሪዎች ላይ የሚፈጸም የሰብዓዊ መብት ጥሰትና በክልሉ የሚስተዋሉ ፖለቲካዊ ችግሮችን ለመፍታት ሐምሌ 26 ቀን 2010 ዓ.ም. በድሬዳዋ የተጀመረውን ጉባዔ ተከትሎ በጅግጅጋ የተቀሰቀሰው ግጭት የበርካታ ሰዎችን ሕይወት በማጥፋት፣ ንብረት በማውደምና ከፍተኛ ሥጋት በክልሉ ከፈጠረ በኋላ ወደ አንፃራዊ መረጋጋት ተመልሷል፡፡

ኢትዮጵያ የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ፖሊሲ እንድታወጣ ተጠየቀ

በኢትዮጵያ የሚስተዋለው የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም በችግሮች የተተበተበ ስለሆነ፣ ችግሮቹን ለመፍታት መንግሥት የአጠቃቀም ፖሊሲ እንዲያወጣ ተጠየቀ፡፡ ይህ ጥያቄ የቀረበው ከሁሉም የአገሪቱ ክልሎች ከተውጣጡ ወጣቶች ሐሙስ መጋቢት 20 ቀን 2010 ዓ.ም. በጁፒተር ሆቴል የፓናል ውይይት በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡

የችግሮችን ምንጭ ያለመረዳት እያስከፈለ ያለው ዋጋ

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከአንድ ወር በፊት ለአሥራ ሰባት ቀናት አድርጎት የነበረውን ዝግ ስብሰባ ሲያጠናቅቅ ባወጣው መግለጫ፣ በአገሪቱ ለተከሰቱ ግጭቶችና በግጭቶቹ ምክንያት ለጠፋው የሰው ሕይወትና ለወደመው ንብረት ሙሉ ኃላፊነት እንደሚወስድ መግለጹ ይታወሳል፡፡ በዚህም የአገሪቱን ሕዝብ በይፋ ይቅርታ ጠይቋል፡፡ በአገሪቱ እየተከሰተ ያለውን ግጭት ለማስቆምና አገራዊ መግባባት ለመፍጠር ሲባልም፣ በወንጀል ተጠርጥረውና ተፈርዶባቸው በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎች ከእስር እንደሚፈቱ ቃል ተገብቷል፡፡ በተገባው ቃል መሠረት በፌዴራልና በክልል ደረጃ እስካሁን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከእስር መለቀቃቸውን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ዓርብ ጥር 25 ቀን 2010 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል፡፡

መንግሥት ከድርቅ ይልቅ በኮሙዩኒኬሽን ቀውስ መቸገሩን አስታወቀ

በአገሪቱ ተከስቶ የነበረውን ቀውስ መቋቋም ቢቻልም መንግሥት በኮሙዩኒኬሽን ቀውስ መቸገሩን አስታወቀ፡፡ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ነገሪ ሌንጮ  (ዶ/ር) ዓርብ ጥር 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ እንደተናገሩት፣ ተከስቶ የነበረውን ድርቅ መቋቋም ቢቻልም እንኳ፣ አገሪቷ በኮሙዩኒኬሽን ቀውስ ሳቢያ ተቸግራለች፡፡ በድርቅ ምክንያት ያጋጠሙ ችግሮችን መንግሥት በብቃት እየተወጣ ነው ብለዋል፡፡

‹‹መንግሥት እንኳን የሰው ሕይወት ይቅርና የውሻ ደም መፍሰስ የለበትም ብሎ ነው እየሠራ ያለው›› ነገሪ  ሌንጮ (ዶ/ር)፣  የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች  ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ቅዳሜ ኅዳር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር፡፡ ኅዳር 29 ቀን 2010 ዓ.ም. የሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን፣ ስለህዳሴ ግድቡና አገሪቱ ስላለችበት የፀጥታ ሁኔታ የመግለጫቸው የትኩረት ነጥቦች ነበሩ፡፡

የሶማሌና የኦሮሚያ ክልሎችን ግጭት ሲከታተል የነበረው ግብረ ኃይል አዲስ ውሳኔ ማስተላለፉ ታወቀ

ከወራት በፊት በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተውን ግጭት ሲከታተል የነበረው ግብረ ኃይል፣ አዲስ ውሳኔ ማስተላለፉ ታወቀ፡፡ የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራው የፌዴራል ግብረ ኃይል ቅዳሜ ኅዳር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የሶማሌ ክልል በግጭቱ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ማዋል ባለመቻሉ፣ ተባባሪ ያልነበሩ አመራሮች ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ ውሳኔ ማስተላለፉ ታውቋል፡፡

‹‹በስም ማጥፋት ተግባር ውስጥም ሆነ በሌሎች አላስፈላጊ ጉዳዮች እየተሳተፉ የሚገኙ ዕድሜያቸውን ለማሳጠር እየጣሩ ያሉ አካላት ናቸው››

ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር)፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤትና በሚኒስትሩ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ የከፈቱ ባለሥልጣናትም ሆኑ ግለሰቦች፣ ዕድሜያቸውን ማሳጠር የፈለጉ ናቸው ሲሉ ሚኒስትሩ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ተናገሩ። ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት ሰኞ ኅዳር 11 ቀን 2010 ዓ.ም. የበጀት ዓመቱን የሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸምና ቀጣይ ዕቅድ ለምክር ቤቱ የባህል፣ ቱሪዝምና መገናኛ ብዙኃን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሲያቀርቡ ነው።

በብሮድካስት ሚዲያዎች መካከል የአጥቂና የተከላካይነት አዝማሚያ መኖሩ ተገለጸ

በኢትዮጵያ የብሮድካስት ባለሥልጣን ፈቃድ ተሰጥቷቸው እየሠሩ ያሉ ብሮድካስት ሚዲያዎች፣ በመካከላቸው የአጥቂና የተከላካይነት አዝማሚያ መኖሩ ተገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘርዓይ አስገዶም ረቡዕ ጥቅምት 15 ቀን 2010 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት፣ በሚዲያዎች መካከል የመከላከልና የማጥቃት ዘመቻ ተጀምሯል፡፡

የብሮድካስት ባለሥልጣን ሚዲያው አደገኛ አዝማሚያዎች ይታዩበታል አለ

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘርዓይ አስገዶም በብሮድካስት ሚዲያው የሚታይ አሳሳቢ ሁኔታ አለ አሉ፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ይህንን ያሉት በአገሪቱ እየታየ ያሉ ግጭቶችን ሚዲያው የሚዘግብብትን መንገድ በተመለከተ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነው፡፡