Skip to main content
x

በቦምብ ጥቃቱ የተጠረጠሩ 26 ታሳሪዎች ላይ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደ

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳን ጨምሮ በ26 ተጠርጣሪዎች ላይ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ቅዳሜ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድን (ዶ/ር) ለመደገፍ በተደረገ ሰልፍ ላይ ከፈነዳው ቦምብ ጋር በተገናኘ ነበር፡፡

ከተጠርጣሪዎቹ መካከል አምስቱ ኮማንደሮች፣ አንድ ምክትል ኮማንደር፣ አንድ ምክትል ኢንስፔክተር፣ ሁለት ሳጅኖች ሲሆኑ፣ 16ቱ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ናቸው፡፡

የኦሮሚያ ክልል ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆኑ

የኦሮሚያ ክልል ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ደመላሽ ገብረ ሚካኤል፣ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በምክትል ዋና ዳይሬክተርነት የአገር ውስጥ ደኅንነት ኃላፊ ሆነው ተሾሙ፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል ከኃላፊነታቸው ተነስተው በሌላ ኃላፊ ተተኩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አዲስ ካቢኔ ሲያዋቅሩ፣ የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል አድርገው ሾመዋቸው የነበሩት ኃላፊ ተነስተው ሌላ ኃላፊ መሾሙ ተጠቆመ፡፡ በቅርቡ ተሹመው የነበሩትና ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በሌላ ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል የተተኩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን ናቸው፡፡ አቶ ያሬድን በመተካት የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል ሆነው የተሾሙት ደግሞ አቶ ዘይኑ ጀማል መሆናቸውን የሪፖርተር ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

አቢሲንያ ባንክን ለመዝረፍ የሞከሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ

ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ የሚገኘው የኢቢሲንያ ባንክ ቅርንጫፍ በስለት በማስፈራራት ዘረፋ ለመፈጸም የሞከሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ፡፡ ሪፖርተር በቅርንጫፍ ባንኩ ተገኝቶ ከዓይን እማኞችና ከመርማሪ ፖሊሶች ለመረዳት እንደቻለው፣ ማክሰኞ ሰኔ 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ገደማ ወደ ባንኩ የገቡ ዘራፊዎች በስለት በማስፈራራት በባለ 50 ኪሎ ግራም ሁለት የማዳበሪያ ከረጢቶች አንደኛው ውስጥ ከ2.7 ሚሊዮን ብር በላይ በማጨቅ ዘርፈው ለመወሰር ሙከራ ቢያደርጉም፣ በአካባቢው በነበሩ ሰዎች ርብርብና በትራፊክ መጨናነቅ ሳቢያ ሊያዙ መቻላቸው ታውቋል፡፡

ቻይናዊው የኦሞ ኩራዝ አምስት ስኳር ፕሮጀክት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሳቸው በገለልተኛ አካል እንዲታይ ጥያቄ አቀረቡ  

በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው እ.ኤ.አ. ጁላይ 25 ቀን 2017 በቁጥጥር ሥር የዋሉትና ክስ ተመሥርቶባቸው በእስር ላይ የሚገኙት የኦሞ ኩራዝ አምስት ስኳር ፕሮጀክት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሚኒተር ዩዋን ጂያሊን፣ የተመሠረተባቸው ክስ በገለልተኛ አካል እንዲታይላቸው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በደብዳቤ ጥያቄ አቀረቡ፡፡

በቦሌ ክፍለ ከተማ የሰሚት አካባቢ ነዋሪዎች ሕገወጦች መግቢያ መውጫ አሳጡን አሉ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ሰሚት ማዞሪያ ከተባበሩት ነዳጅ ማደያ ወደ ሰሚት ለስላሳ ማምረቻ ፋብሪካ መውረጃ መንገድ መጋጠሚያ ላይ ‹‹ተደራጅተናል›› የሚሉ ግለሰቦች አካባቢውን መኪና ማሳደሪያና መፀዳጃ ከማድረጋቸውም በተጨማሪ፣ መሸት ሲል ሰርቆ መደበቂያ በማድረጋቸው የአካባቢው ነዋሪዎች መውጫ መግቢያ ማጣታቸውን ገለጹ፡፡ የአካባቢው ወረዳ 8 ሥራ አስፈጻሚ ደግሞ ድርጊቱ ከአቅም በላይ በመሆኑ ለሚመለከተው አካል አሳውቀናል ብለዋል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ሠራተኞች ለተመሳሳይ ሥራ የተለያየ ክፍያ መፈጸሙን ተቃወሙ

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በአዋጅ ቁጥር 943/2008 እንደገና በመቋቋሙ ምክንያት አራት የተለያዩ ተቋማት የወንጀል ምርመራ ሠራተኞች ወደ አንድ የምርመራ ሥርዓት እንዲጠቃለሉ የተደረጉ ቢሆንም፣ ለተመሳሳይ ሥራ የተለያየ ክፍያ መፈጸሙን ተቃወሙ፡፡ በተለያየ ስያሜና ተቋም ይሠሩ የነበሩት የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን፣ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣንና የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ሠራተኞች ናቸው፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለፖሊስ ተቋማትና ለችሎቶች ማሳሰቢያ ሰጠ

የፍትሕ አካላት በጋራ ባስጠኑት የመግባቢያ ሰነድ ማለትም ቢፒአር መሠረት የሚከሰሱ ሰዎች በፖሊስ የተያዙበት ቀንና ቦታ፣ በእስር ላይ የቆዩበትና የተፈቱበት ቀናት ተጠቅሰው እንዲጻፉ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለፖሊስ ተቋማትና ለፍርድ ቤቶች ማሳሰቢያ ሰጠ፡፡ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ በላቸው አንሺሶ ተፈርሞ ለፌዴራል ፖሊስ፣ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንና ለሁሉም ችሎቶችና ምድብ ችሎቶች የተላለፈው የማሳሰቢያ ደብዳቤ፣ በሕገ መንግሥቱ የሰዎች መብት ማክበርና ማስከበር ኃላፊነትና ግዴታ በቀዳሚነት የፍትሕ ተቋማት መሆኑ ይታወቃል ይላል፡፡

ሲኖትራክ ለመግዛት የከፈሉትን ገንዘብ የተጭበረበሩ 98 ሰዎች የፍትሕ ያለህ እያሉ ነው

ከሁለት ዓመታት በፊት ዙና ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ በሦስት ወራት ውስጥ ሲኖትራክ ገልባጭ መኪና ገዝቶ እንዲያስረክባቸው ተስማምተው ሙሉና ግማሽ ክፍያ ከከፈሉት በኋላ፣ መጭበርበራቸውን ያወቁ 98 ግለሰቦች የፍትሕ ያለህ እያሉ ነው፡፡ ግለሰቦቹ ግማሽ ክፍያና ሙሉ ክፍያ ፈጽመው ተሽከርካሪያቸውን ለመረከብ በመጠባበቅ ላይ እያሉ የማኅበሩ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ጌታሰው ከአገር መውጣታቸውን እንደሰሙ፣ ያለውን ንብረትና ተሽከርካሪዎች እንዳይሸጡ፣ እንዳይለወጡና ለሦስተኛ ወገን እንዳይዘዋወሩ ክስ መሥርተው አሳግደው እንደነበር ይናገራሉ፡፡