Skip to main content
x

የዩኔስኮን ግብረ መልስ የሚጠብቀው የአክሱም ቅርሶች ጥገና

በካቦ የታሰረው የአክሱም ሐውልትን ጨምሮ በተለያዩ ቅርሶች ላይ የተደረገው ጥናት መጠናቀቁና ጥገና ለማከናወን የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ግብረ መልስ እየተጠበቀ መሆኑን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን (ቅጥጥባ) አስታውቋል፡፡

‹‹ፊቼ - ጫምባላላ›› የአዲስ ዘመን ብሥራት በሲዳማ

ትውፊታዊውና ኦሪታዊው መጽሐፍ ስለ ብርሃናት ተፈጥሮ ይገልጻል፡፡ ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ በሰማያት ብርሃናት ተደረጉ ይለናል፡፡ ታላቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፣ ታናሹ ብርሃን በማታ እንዲገዛ ከዋክብትንም ፈጠረ ሲል ያክልበታል፡፡ ብርሃናቱ ፀሓይና ጨረቃ ከዋክብትም የተፈጠሩት ስለ አራት ነገሮች መሆኑንም ኦሪቱ ያብራራል፡፡ ለምልክቶችና ለዘመኖች፣ ለዕለታትና ለዓመታት በማለት፡፡

ታሪካዊው የኢትዮጵያ የዘመን ቆጠራ ሲፈተሽ

ክብረ ነገሥት የሚባል በ13ኛው መቶ ዘመን እንደተጻፈ/እንደተተረጐመ የሚነገር መጽሐፍ አለ፡፡ ክብረ ነገሥት በኢትዮጵያ ለ700 ዓመታት ያህል ብሔራዊ መተዳደሪያ ሆኖ ሲያገለግል የኖረ መጽሐፍ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የቤተ ሰለሞን ሥርወ መንግሥት (ሰሎሞናይክ ዳይናስቲ) ምንጭ ለመጀመሪያ ጊዜም የተገኘው በክብረ ነገሥት ውስጥ ነው፡፡

በብሔራዊ ሙዚየም የሚቀመጡት ቅርሶች የትኞቹ ናቸው?

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ቅጥር ውስጥ ከሚገኙ ሐውልቶች መካከል በአንድ ጥግ አፄ ኃይለ ሥላሴ ተማሪዎችን ሲያነጋግሩ የሚያሳየው፣ በሌላው ኢትዮጵያዊ የዘር ግንድ እንዳለው የሚነገርለት የአሌክሳንደር ፑሽኪን፣ የአዘቲክስን (ሜክሲኮ) የጥንት ሥልጣኔ የሚያሳየው የኦልማክ ሐውልት ይገኛል፡፡ ወረድ ብሎ ደግሞ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አልባኒያውያንን እንደጨፈጨፈ የሚነገርለት የኮሚኒስቱ ኢንቨር ሆዛ ሐውልት ከአንዱ ግርጌ አለ፡፡

ስለ ዴር ሡልጣን ገዳም አዲሱ የእስራኤል ፕሬዚዳንት የገቡት ቃል ይፈጸም ይሆን?

ኢትዮጵያ ከኢየሩሳሌም ጋር ያላት ግንኙነት ከሦስት ሺሕ ዓመታት በፊት ጀምሮ እንደሆነ ይወሳል፡፡ ንግሥተ ሳባ/ንግሥተ አዜብ የምትባለው ማክዳ ንጉሥ ሰሎሞንን ከጎበኘችበት ዘመን እንደሚያያዝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በዚያን ወቅት ነው “ዴር ሡልጣን ” ተብሎ የሚታወቀው ሥፍራ በርስትነት ለኢትዮጵያ የተሰጠው የሚባለው፡፡

ለአፄ ዮሐንስ ሐውልትና ሙዚየም ሊገነባ ነው

አፄ ዮሐንስ አራተኛ ንጉሠ ጽዮን ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ (1863-1881) በተወለዱበት ዓቢይ ዓዲ ከተማ የመታሰቢያ ሐውልታቸውን ለማቆምና ታሪካቸው የሚዘከርበት ሙዚየም ለመገንባት ታቅዶ ለተግባራዊነቱ ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴ በመከናወን ላይ ነው፡፡ እስካሁንም በተካሄደው እንቅስቃሴ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ ከገባ ውሎ አድሯል፡፡

አነጋጋሪዎቹ የመቅደላ ቅርሶች

መሰንበቻውን ከ150 ዓመታት በፊት በዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ዘመን በእንግሊዝ ሠራዊት ከመቅደላ አምባ የተዘረፉት ቅርሶች ‹‹ኢትዮጵያ ፍላጎቱ ካላት ለረዥም ጊዜ በውሰት ልንሰጥ እንችላለን›› የሚለውን የቪክቶሪያና አልበርት ሙዚየምን መግለጫ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እንደማያውቀው አስታውቋል፡፡

የዲጂታል የምዝገባ ሥርዓት ውስጥ የገባው የቅርስ ጥበቃ

የባህላዊ ቅርሶች የምዝገባና ቁጥጥር ሥርዓት በእንግሊዝኛ አጠራሩ‹‹ ካልቸራል ሔሪቴጅ ኢንቨንተሪ ማኔጅመንት ሲስተም››፣  በቅርቡ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን  ያስመረቀው የመረጃ ቋት (ዳታቤዝ) ሲሆን  ቅርሶች በዲጂታል መንገድ የሚመዘገቡበት ነው፡፡

ምን ይልክ ፖስታ ምንስ ያውጋ?

​​​​​​​‹‹ምን ይልክ፣ ምን ይልክ፣ ምን ይልክ እያሉ በፖስታ ቤት ዙርያ ይጠያየቃሉ፡፡ ዛሬማ ምን አይልክ! ሁሉን በየዓይነቱ ሰፍሮ በልክ በልክ ብቅ ብሎ ባየው መሥራቹ ምን ይልክ›› በአንድ ወቅት በእታጉ በዛብህ የቀረበ ግጥም ነው፡፡

ስለአክሱም ሐውልት ጥገናዊ ሒደት በተዘጋጀው ጥናት ላይ ሊመከር ነው

የጥንታዊት ኢትዮጵያ መዲና የነበረችው አክሱም፣ ተመራማሪዎች እንደሚገልጿት የኃያል መንግሥት ዋና ከተማ፣ ቀጥሎም የሃይማኖት ማዕከል ብሎም ክርስቲያናዊ መንግሥትን በአፍሪካ ውስጥ መመሥረቷ ሰነዶች ያመለክታሉ፡፡ የኢትዮጵያ ክርስትና መለያ የሆነው ታቦተ ሕግ በመያዝም በርካታ ምዕመናንም በማስተናገድ ትታወቃለች፡፡