Skip to main content
x

የዘንድሮው ፓርላማ

አምስተኛው የምርጫ ዘመን ሦስተኛ ዓመት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዓመቱን ሥራ የጀመረው በመደናገር ውስጥ ሆኖ ነበር፡፡ የመደናገሩ ምክንያትም የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ የአገሪቱ ከፍተኛ የሆነውን ሥልጣን አልፈልግም በማለት መልቀቂያ በማቅረባቸው ነው፡፡

‹‹በባለሀብቶች ቤት ውስጥ ተከማችቶ የሚገኝ ሀብት ችግር ቢኖርበትም በሕግ አግባብ ምሕረት እናደርጋለን››

ዓርብ ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረገው ስብሰባ የ2011 ዓ.ም. በጀት ፀድቋል፡፡ ለሚቀጥለው ዓመት ሥራ ላይ የሚውለው 346.9 ቢሊዮን ብር በጀት ከመፅደቁ በፊት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው የተለያዩ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

መንግሥት ያቀረበው የምሕረት መስጫ አዋጅ ሳይፀድቅ ፓርላማው ለእረፍት ተበተነ

በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥረው ለተያዙ፣ ለተፈረደባቸውና ሳይያዙ በውጭ አገር በስደት ለሚኖሩ ግለሰቦችና የሕግ ሰውነት ላላቸው አካላት ምሕረት ለመስጠት መንግሥት ያቀረበው የምሕረት መስጫ አዋጅ ሳይፀድቅ፣ ፓርላማው የዓመቱን የሥራ ጊዜውን አጠናቆ ለእረፍት ተበተነ፡፡

ዶ/ር መረራ ጉዲና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ቦርድ አባል ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሰየሙ

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የተጓደሉ ቦርድ አባላት እንዲሟሉ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መረራ ጉዲናን (ዶ/ር) የቦርድ አባል፣ እንዲሁም የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትሩን አቶ አህመድ ሺዴ ደግሞ የቦርድ ሰብሳቢ አድርገው ሰየሙ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዶ/ር መረራ ጉዲናን የኢቢሲ ቦርድ አባል አድርገው ሰየሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሐሙስ ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ.ም. በርሳቸው ተፈርሞ በወጣ ደብዳቤ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር መረራ ጉዲናን (ዶ/ር) ከሌሎች ሦስት ግለሰቦች ጋር የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የቦርድ አባል አድርገው ሰየሙ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሽብርተኝነት የተፈረጁ ድርጅቶችን ፍረጃ ለማስነሳትና ምሕረት ለማሰጠት በፓርላማ እንደሚገኙ ታወቀ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጁ ድርጅቶች ፍረጃው ተነስቶላቸው በነፃነት መንቀሳቀስ እንዲችሉና ለአገራዊ መግባባት ሲባል በወንጀል ለሚፈለጉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ምሕረት እንዲደረግላቸው ባሳለፋቸው ውሳኔዎች ላይ፣ ፓርላማው ሐሙስ ሰኔ 28 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደሚወያይና ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ተገኝተው ማብራሪያ እንደሚሰጡ ታወቀ።

በኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ መካከል የሚደረገው የቤት ሠራተኞች ቅጥር ስምምነት አዋጅ ፀደቀ

በኢትዮጵያና በሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥታት መካከል የቤት ሠራተኞችን ቅጥር አስመልክቶ፣ ከአንድ ዓመት በፊት የተደረገው ስምምነት ረቂቅ አዋጅ በፓርላማ ፀደቀ፡፡ በተለይ በሳዑዲ ዓረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ ከአራት ዓመታት በፊት ደርሶ በነበረው የሞት፣ አካል መጉደልና እንግልት ምክንያት የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮች የሚደረጉ ጉዞዎችን ማስቆሙ ይታወሳል፡፡

የስኳር ኮርፖሬሽን ቦርድ ሜቴክ እጅ የቀሩ ሦስት የስኳር ፕሮጀክቶች ኮንትራት እንዲቋረጥ ወሰነ

የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ለዓመታት ሊያጠናቅቃቸው ያልቻላቸው ሦስት ግዙፍ የስኳር ፕሮጀክቶች የግንባታ ውሎች እንዲቋረጡ መወሰኑን፣ የፕሮጀክቶቹ ባለቤት የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡ ይኼንኑ ውሳኔም ኮርፖሬሽኑን የሚመራው ቦርድ እንዳፀደቀው ተገልጿል፡፡