Skip to main content
x

ኢትዮጵያ በ2018 የአፍሪካ ወጣት ጨዋታዎች 56 አትሌቶችን ታሳትፋለች

ኢትዮጵያ በአልጄሪያ መዲና አልጀርስ በሚከናወነው 3ኛው የአፍሪካ ወጣት ጨዋታዎች በስድስት ስፖርቶች 56 አትሌቶችን ታሳትፋለች፡፡ ጨዋታዎቹ በ20 ስፖርቶች በተለያዩ የውድድር ዓይነቶች የሚካሄዱት ከሐምሌ 11 ቀን እስከ 21፣ 2010 ዓ.ም. ድረስ ነው፡፡

ብሔራዊ ፀረ አበረታች ቅመሞች ቢሮ በአትሌቶችና በመድኃኒት መደብር ላይ የቅጣት ውሳኔ አሳለፈ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ አበረታች ቅመሞች ጽሕፈት ቤት፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመቆጣጠር እያደረገ ካለው ጥረት ጎን ለጎን ከሰሞኑ በስፖርት የፀረ አበረታች ቅመሞች የሕግ ጥሰት በፈጸሙ አትሌቶችና የመድኃኒት መደብር ላይ የቅጣትና ዕገዳ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ ጽሕፈት ቤቱ ሰኔ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ ውሳኔውን  ዝርዝርና ሒደት አስመልክቶ ማብራሪያም ሰጥቷል፡፡

ንግድ ባንክ 75ኛ ዓመት ኢዩቤልዩ ክብረ በዓሉን በሩጫ አጠናቀቀ  

በቅርቡ የወንዶች የእግር ኳስ ቡድኑን በይፋ ያፈረሰው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የተመሠረተበትን 75ኛ ኢዮቤልዩ በዓሉን በሩጫ ውድድር አክብሯል፡፡ ተቋሙ ለአሸናፊ አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው 75 ሺሕ ብር የገንዘብ ሽልማት አበርክቷል፡፡ እሑድ ግንቦት 5 ቀን 2010 ዓ.ም. መነሻና መድረሻው አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ባደረገውና በግንባታ ላይ በሚገኘው የባንኩ ዘመናዊ ሕንፃ ዙሪያ በተደረገው የሩጫ ውድድር 13ሺሕ ተወዳዳሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

ትንሣኤን በሩጫ

በርካታ ዓለም አቀፍ የጎዳና የሩጫ ውድድሮች በበዓለ ትንሣኤው ዋዜማና በዕለቱ ተከናውነዋል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶችም ድል ቀንቷቸዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ከተከናወኑት የማራቶንና ግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድሮች በተለያ የአውሮፓ ከተሞች የተደረጉት ይጠቀሳሉ፡፡

ጊዜና ቦታ ያልገደበው የኢትዮጵያውያን አትሌቶች ስኬት

የአትሌቲክስ ግንዛቤው እንዲህ እንደ አሁኑ ብዙም በማይባልበት በ1950ዎቹ ከምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኢትዮጵያ ወደ ሮም ያቀናው አትሌት ያውም በባዶ እግሩ ያንን ታሪክ ይሠራል ብሎ ለመገመት በወቅቱ እርግጠኛ መሆን ባይቻልም የኋላ ኋላ ግን ታሪኩ ዕውን ሆኗል፡፡

የአትሌቶቹ ሽኝት

​​​​​​​ታላላቅና ወጣት አፍሪካውያን የሚሳተፉበት አምስተኛው የአፍሪካ አገር አቋራጭ የአትሌቲክስ ውድድር ቅዳሜ መጋቢት 8 ቀን 2010 ዓ.ም. በአልጄሪያ ይካሄዳል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አትሌቲክስ ልዑካን ባለፈው ሰኞ ምሽት ወደ ሥፍራው አምርተዋል፡፡

የአትሌቲክሱ ተስፋና ሥጋት

የተለያዩ ስፖርቶችን የሚያስተዳድሩ 26 ብሔራዊ ፌዴሬሽኖችና አሶሴሽኖች ይገኛሉ፡፡ ይሁንና ብሔራዊ ተቋማቱ በኃላፊነት የሚያስተዳድሯቸው ስፖርቶች የታሰበውን ያህል ውጤታማ ሲሆኑ አይስተዋልም፡፡ የየዘርፉ ባለሙያተኞች ለዚህ እንደ ምክንያት የሚያቀርቡት ደግሞ፣ ስፖርት እንደሌሎች የሙያ ተቋማት ከኃላፊዎች ሹመት ጀምሮ በከፍተኛ የመዋቅር ችግር ውስጥ ተዘፍቆ መቆየቱ ዋነኛው ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን ከፍ ያሉበት የበርሚንግሃም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና

ኢትዮጵያ በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሠለፈችባቸውን ወርቃማ ድሎች ያጎናጸፏት ጥቂት አትሌቶች መሆናቸው መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ ከተመሠረተ ከሦስት አሠርታት በላይ ባስቆጠረው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና፣ ስማቸው የሚጎላው አትሌቶች ኃይሌ ገብረ ሥላሴ፣ መሠረት ደፋር፣ ገለቴ ቡርቃ  እንዲሁም የአሁኖቹ ገንዘቤ ዲባባ፣ ዮሚፍ ቀጀልቻና ሳሙኤል ተፈራ ዋነኞቹ ናቸው፡፡

የተፎካካሪነት መንፈሱ እየጨመረ የመጣው የጃንሜዳ አገር አቋራጭ ውድድር

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በውድድር ዓመቱ ከሚያከናውናቸው የሩጫ መርሐ ግብሮች መካከል ዓለም አቀፍ ይዘት ያለው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ይጠቀሳል፡፡ ዘንድሮ ለ35ኛ ጊዜ የተከናወነው ይኼው የሩጫ ውድድር፣ ባለፈው እሑድ በጥሩ የተፎካካሪነት መንፈስ በጃንሜዳ ውድድሩን አድርጓል፡፡