Skip to main content
x

ሦስት ክልሎች የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑን ውሳኔ አወገዙ

ጉባዔውም የፊፋን የውሳኔ ሐሳብ እንዲያከብር ጠይቀዋል በአፋር ክልል ሊካሄድ ቀን ተቆርጦለት የነበረውና ሐሙስ ጥቅምት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሒልተን የሚካሄደው ጉባዔ ሦስት ክልሎች ተቃወሙ፡፡ የአፋር ክልል ሊያስተናግደው የነበረው ጉባዔ ወደ አዲስ አበባ መቀየሩን በመቃወም ከሕግም ከሞራልም አኳያ ተገቢነት የሌለው ድርጊት በማለት የፌዴሬሽኑን ውሳኔ አውግዘዋል፡፡