Skip to main content
x

ኅብረት ባንክ በትውልደ ኢትዮጵያዊያን የተያዙ አክሲዮኖችን በከፍተኛ ዋጋ አገበያየ

በተለያዩ ባንኮችና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ውስጥ የአክሲዮን ባለድርሻ በመሆን የቆዩ የውጭ ዜጎች ኢትዮጵያዊያን ይዞታ ሥር የነበሩ አክሲዮኖች እንዲመለሱላቸው ቢወሰንም፣ አሁንም ግን ድርሻዎቻቸው ለጨረታ እየቀረቡ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

በውጭ የሚኖሩ ዜጎች በአገር ቤት ለዘመዶቻቸው የሕክምና ሽፋን መግዛት የሚችሉበት አሠራር ተዘረጋ

ከኢትዮጵያ ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በርካታ በመሆኑ ጭምር ባንኮች ከዳያስፖራው ጋር የተገናኙ አዳዲስ አገልግሎቶች ስለመጀመራቸው እያስተዋወቁ ነው፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳያስፖራ የቤት መገንቢያ ብድር በማመቻቸት ሥራ መጀመሩ በምሳሌነት ሊጠቀስ ይችላል፡፡

ዳያስፖራዎች ለቤተሰቦች የጤናና አደጋ ኢንሹራንስ የሚገቡበት አሠራር ይፋ ተደረገ

በውጭ አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአገር ቤት ለሚኖሩ ቤተሰቦቻቸው የጤናና የአደጋ መድን ሽፋን የሚሰጥ አዲስ የኢንሹራንስ አገልግሎት መጀመሩን ፀሐይ ኢንሹራንስ አስታወቀ፡፡

የዳያስፖራ ኤጀንሲ ሥራ ሊጀምር ነው

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ በይፋ ሥራ ሊጀምር መሆኑን የኤጀንሲው የሥራ ኃላፊዎች አስታወቁ፡፡ አዲስ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ አንድሪስና የኤጀንሲው የማኅበረሰብ ልማት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ወልዴ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ ኤጅንሲው የሰው ኃይልና የአደረጃጀት ሥራዎችን ላለፉት ሁለት ወራት ሲያካሂድ ቆይቶ አሁን ሙሉ በሙሉ ሥራውን ማከናወን የሚችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል፡፡

የፋይናንስ ዘርፉን ለዳያስፖራዎች ክፍት የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ ተዘጋጀ

ለዓመታት በአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ እንዳይሳተፉ በሕግ ተከልክለው የቆዩት ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን በዘርፉ ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚፈቅድ ረቂቅ ሕግ መዘጋጀቱ ተገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ዛሬ የካቲት 13 ቀን 2011 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ፣ በፋይናንስ ዘርፉ ውስጥ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዳይሳተፉ የሚያግደውን ሕግ በማሻሻል ተሳታፊ የሚሆኑበት መንገድ መመቻቸቱን ገልጸዋል፡፡

ድክ ድክ የሚለው የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ ያገኙት የሕዝብ ድጋፍ አገሪቱን ወደፊት ለማራመድ እንደ መልካም ዕድል የሚወሰድ ስለመሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ይህ ድጋፍ በተለያዩ መንገዶች የተገለጸ ሲሆን፣ በተለይ ዳያስፖራው ለእርሳቸው የሰጠው ግምት ከፍተኛ ነው፡፡ ለዚህም ዳያስፖራው ከአንድ ማኪያቶው በቀን አንድ ዶላር አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ያደረጉትን ጥሪ በደስታ ነበር የተቀበለው፡፡

የኢትዮጵያ ሸማቾች መብትና አተገባበሩ

ሸማቾች በአንድ የኢኮኖሚ ሥርዓት ካሉ የተለያዩ ተዋናዮች ውስጥ የሚመደቡ ናቸው፡፡ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ‹‹ፍላጎት›› (Demand) በማለት የሚገልጹትን ሐሳብ ከሚወክሉት ውስጥም ይመደባሉ፡፡ ይህም ማለት ሸማቾች በንግድ ድርጅቶችም ሆነ ግለሰቦች ወደ ገበያ የሚቀርቡትን የተለያዩ ዕቃዎችና አግልግሎቶች የሚገዙ ናቸው፡፡

ዜግነትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ

ጥቅምት 26 ቀን 2011 ዓ.ም. የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪ በመሆን የተሾሙት ወ/ሮ ቢልለኔ ሥዩም ካናዳዊ ዜግነት ኖሯቸው የአገሪቱ ሕግ ከሚፈቅደው አግባብ ውጪ እንዴት ተሾሙ ተብሎ፣ የማኅበራዊ ሚዲያና የተለያዩ መድረኮች ከፍተኛ መወያያ ጉዳይ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ በወ/ሮ ቢልለኔ ሹመት የተነሳም የተለያዩ አስተያየቶች ሲንፀባረቁ ተስተውሏል፡፡

አዋሽ ባንክ ለዳያስፖራዎች እጥፍ ወለድ የሚያስገኝ አገልግሎት ጀመረ

አዋሽ ባንክ ለዳያስፖራው ማኅበረሰብ የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ግዥን ጨምሮ ለሌሎች ቢዝነስ እንቅስቃሴዎቻቸው ሊውል የሚችል የተለያዩ የብድር አማራጮችን ሊያገኙ የሚችሉበትን የባንክ አገልግሎቶችን ማመቻቸቱን አስታወቀ፡፡ ከመደበኛ የወሊድ ምጣኔ በእጥፍ ወለድ የሚከፈልበት አገልግሎትም አለኝ ብሏል፡፡

ንግድ ባንክ ለዳያስፖራው የቤት መሥሪያ ብድር ማዘጋጀቱን አስታወቀ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲገቡ ባደረጉት ጥሪ መሠረት፣ በርካቶች ወደ አገር ቤት እንደመጡ መታዘብ ተችሏል፡፡ ከፖለቲከኞችና ከመብት ተሟጋቾች ባሻገር በርካታ የዳያስፖራው አባላት አዲሱን ዓመት በኢትዮጵያ ለማክበር ከያሉበት መጥተዋል፡፡