Skip to main content
x

የአጣዬ ከተማ ነዋሪዎች ለደረሰባቸው ግድያና ዝርፊያ የክልሉንና የፌዴራል መንግሥትን ተጠያቂ አደረጉ

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በአጣዬ ከተማና ዙሪያው ከመጋቢት 28 ቀን 2011 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ ጀምሮ በታጣቂዎች ለደረሰባቸው ግድያ፣ ዘረፋና መፈናቀል ተጠያቂዎቹ የአማራ ክልል መንግሥትና የፌዴራል መንግሥት መሆናቸውን ተናገሩ፡፡

ያልተፈታው የምዕራብ ኢትዮጵያ ቋጠሮ

ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በፊት በነበሩት ሦስት ተከታታይ ዓመታት አገሪቱን ሲያውካት የቆዩት አመፅ፣ ብጥብጥ፣ ግጭትና የእምቢተኝነት ሠልፍና ሁከቶች ረገብ ለማለታቸው ጅማሮ የሆነው የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በጠቅላይ ሚኒስትርነት መሾም ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከእነ ትጥቃቸው በመግባታቸው የተፈረደባቸው የመከላከያ ሠራዊት አባላት በይግባኝ ፍርዳቸው ተቀነሰላቸው

በቡራዩና አካባቢው የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር ለማረጋጋት በግዳጅ ላይ ቆይተው ሲመለሱ፣ መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድን (ዶ/ር) ካላነጋገርን በማለት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከእነ ትጥቃቸው የገቡ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ፍርዳቸው በይግባኝ ተቀነሰላቸው፡፡

ፈረንሣይ ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ የሚያደርግ ጦር ወደ ኢትዮጵያ እንደምትልክ ፕሬዚዳንት ማክሮን ተናገሩ

ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ማክሰኞ መጋቢት 3 ቀን 2011 ዓ.ም. አዲስ አበባ የገቡት የፈረንሣይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ ‹‹በሥልጠና ላይ ያተኮረ ሕጋዊ የፈረንሣይ ጦር ወደ ኢትዮጵያ እንልካለን፤›› ሲሉ አስታወቁ፡፡ ፕሬዚዳንቱ ይኼን ያሉት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በመሆን፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡

መንግሥት ያረቀቀው የጦር መሣሪያ ቁጥጥር አዋጅ ፖለቲካዊ ፋይዳ

ዓለም አቀፉ የኢኮኖሚና የሰላም ኢንስቲትዩት እ.ኤ.አ. በ2018 ይፋ ባደረገው ዓለም አቀፍ የሰላም ኢንዴክስ መረጃ መሠረት፣ የሰላም ሁኔታቸውን በመተንተን ከተመዘኑ 163 አገሮች መካከል ኢትዮጵያ 139ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። በዚሁ መረጃ መሠረት የኢትዮጵያ የሰላም ሁኔታ ከሰሃራ በታች ከሚገኙ 44 የአፍሪካ አገሮች ሲመዘን ደግሞ 38ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ከእነ ትጥቃቸው በመግባታቸው የተፈረደባቸው የመከላከያ አባላት ይግባኝ አሉ

በቡራዩና አካባቢው በግዳጅ ላይ ቆይተው ወደ ካምፕ ሲመለሱ መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትሩን ካላነጋገርን በማለት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በማቅናታቸው፣ ከአሥር እስከ አምስት ዓመት ጽኑ እሥራት የተቀጡት የመከላከያ ኮማንዶ አባላት ይግባኝ አሉ፡፡

ከመከላከያ ሠራዊቱ ውጪ የሆኑ ሕግ አስከባሪ አካላት መታጠቅ የሚችሉትን የጦር መሣሪያ ዓይነት የሚወሰን ሕግ ተረቀቀ

ከአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በስተቀር ሌሎች በክልል መንግሥታትና በፈዴራል መንግሥት የተደራጁ ሕግ አስከባሪ አካላት፣ መታጠቅ የሚችሉትን የጦር መሣሪያ ዓይነት የሚወስን ረቂቅ ሕግ ተጠናቆ ለውይይት ቀረበ።

የፌዴራል ፖሊስ ሪፎርም ምን ይዟል?

ከፌዴራል መንግሥት የደኅንነትና የፀጥታ አካላት መካከል በሪፎርም ሒደት ውስጥ እንዲሆኑ በተደጋጋሚ ሲነገርላቸው ከሚሰሙት መካከል፣ የአገር መከላከያ ሠራዊትና የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ የአገር መከላከያ ሠራዊት ሪፎርም በቅርፅም በአቅምም የሚያመጣው ለውጥ ምን እንደሚመስል ከአንዴም ሁለት ሦስቴ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡

በጎንደር የተሰማራው የመከላከያ ኃይል አምስት ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አዋለ

ከእሑድ የካቲት 10 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በአማራ ክልል በምዕራብና በማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች የተፈጠረውን የፀጥታ ችግርና ግጭት ለማረጋጋት በአካባቢው የተሰማራው የመከላከያ ሠራዊት፣ አምስት ግለሰቦችን ከእነ ትጥቃቸው በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ታወቀ፡፡