Skip to main content
x

የተረሳው ሸማች

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) ሰሞኑን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ፊት ቀርበው፣ በ2011 ዓ.ም. ረቂቅ በጀት ዙሪያ ማብራሪያ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡ ማብራሪያቸውን ተከትሎም ከእንደራሴዎቹ ጥያቄዎች ቀርበውላቸው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በውጭ ምንዛሪ አጠቃቀም ችግር ከገበያ እየወጡ ያሉ የንግድ ሰዎች የብሔራዊ ባንክ ገዥ ይድረሱልን አሉ

በውጭ ምንዛሪ እጥረትና አጠቃቀም ችግር ምክንያት ጥሬ ዕቃ ማግኘት ባለመቻላቸው ከምርት እየወጡ መሆናቸውን የሚናገሩ የፋብሪካ ባለቤቶችና መድኃኒትን የመሳሰሉ አስፈላጊ ዕቃዎች የሚያስመጡ ነጋዴዎች፣ ከገበያ እየወጡ መሆኑን በመጥቀስ አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) እንዲደርሱላቸው ጠየቁ፡፡

የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ አልጋ ወራሽ በአዲስ አበባ

ዓርብ ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ.ም. አዲስ አበባ የገቡትን የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ አልጋ ወራሽ ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አልናህያን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ከተቀበሉ በኋላ ራሳቸው በሚያሽከረክሩት አውቶሞቢል አሳፍረው ወደ ጉብኝት መዳረሻቸው ወስደዋቸዋል፡፡

የገንዘብ እጥረት ቀውስ በኢኮኖሚው ላይ ሥጋት መደቀኑን መንግሥት አመነ

የአገሪቱን ኢኮኖሚ ቀጣይነት ለማረጋገጥ የገንዘብ እጥረት ቀውስ እንደገጠመው፣ እጥረቱ በፍጥነት መፍትሔ ካልተገኘለት ኢኮኖሚውን በመጉዳት ማኅበራዊ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል መንግሥት በይፋ አስታወቀ፡፡ ይህንን የተናገሩት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር)፣ የፌዴራል መንግሥትን የ2011 ዓ.ም. ረቂቅ በጀት ሐሙስ ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ለፓርላማ ባቀረቡበት ወቅት ነው፡፡

ለኢትዮጵያ ችግሮች ኢትዮጵያዊ መፍትሔዎች ይፈለጉ!

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተወሰዱ ያሉ የተለያዩ ዕርምጃዎች፣ ለብሔራዊ መግባባትና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ተስፋ ሰጪ ምልክቶችን እያሳዩ ነው፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች እስር ላይ የነበሩ ወገኖችን በብዛት መፍታት፣ ክሶችን ማቋረጥ፣ አገራቸውን አገልግለው እንደ አልባሌ ዕቃ የተጣሉ ሰዎችን ማስታወስና መደገፍ፣ በጡረታ የሚገለሉትን በክብር መሸኘት፣ ማዕረጋቸው የተገፈፈን መልሶ መስጠትና የጡረታ መብት ማስከበር፣ ኢትዮጵያውያንን በአንድነት ሊያቆሙ የሚችሉ ጥዑም መልክቶችን ማስተላለፍ፣ አገርን ከሌብነትና ከዘረፋ ለመታደግ ቁርጠኛ አቋም ማሳየትና የመሳሰሉ ዕርምጃዎችን ሕዝብ በአንክሮ እየተከታተለ ነው፡፡

የዋጋ ማስተካከያ ባለመደረጉ ለችግር መዳረጋቸውን ዕቃ አቅራቢዎች ገለጹ

በጥቅምት 2010 ዓ.ም. የብር በ15 በመቶ እንዲቀንስ ከተደረገ በኋላ፣ በዕቃዎች ላይ የዋጋ ማስተካከያ ባለመደረጉ መቸገራቸውን የማዕቀፍ ግዥ አቅራቢ ነጋዴዎች አመለከቱ፡፡ የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ሐሙስ ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ከዕቃ አቅራቢዎች ጋር ባጋጠሙ ችግሮች ላይ ውይይት አድርጓል፡፡

ተሟጋቹ ባለሙያ ስለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ይናገራሉ

በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አስተዳደር ላይ የጎላ ትችት በመሰንዘር፣ ሐሳባቸውንም በተባ ብዕራቸው በማስተጋባት ይታወቃሉ፡፡ ለዓመታትም በጋዜጦች ስለአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ከሙያቸው አኳያ ሲጽፉ ኖረዋል፡፡ ቅዳሜ ግንቦት 25 ቀን 2010 ዓ.ም. የዚሁ ትጋታቸው አካል የሆነውንና በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ የተመሠረተ ትንታኔ ያቀረቡበትን መጽሐፍ ይፋ አድርገዋል፡፡ 

የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ለማሳካት ፈተና እንደገጠመው መንግሥት አመነ

ሁለተኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዋና ዋና ግቦችን ለማሳካት አዳጋች ሁኔታ እንደገጠመው መንግሥት አመነ፡፡ የኢትዮጵያ ፕላን ኮሚሽን የዕቅዱን የግማሽ ዘመን አፈጻጸም በመገምገም በሁሉም የመንግሥት መዋቅሮች ውይይት እንዲደረግበት ያቀረበ ሲሆን፣ የዚህ የግምገማ ሰነድ ቅጂን ለማግኘት ተችሏል፡፡

በውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ችግር አዲስ አበባ ከባድ የውኃ እጥረት ያጋጥማታል ተባለ

በውጭ ምንዛሪ አቅርቦትና አመዳደብ ችግር ምክንያት አዲስ አበባ ከተማ ከአንድ ዓመት በኋላ ከበድ ያለ የንፁህ ውኃ አቅርቦት ችግር ሊገጥማት ይችላል ተባለ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 46 ሚሊዮን ዶላርና ስድስት ሚሊዮን ዩሮ ቅድሚያ ተሰጥቶት እንዲቀርብለት በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ምላሽ እንዳልተሰጠው አስታውቋል፡፡