Skip to main content
x

ከኃላፊነት የሚነሱ ባለሥልጣናትን በአምባሳደርነት መሾም በፓርላማ ጥያቄ አስነሳ

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሥልጣን ጊዜያቸውን ጨርሰውም ሆነ ሳይጨርሱ ከኃላፊነት የሚነሱ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ ባለሥልጣናት በአምባሳደርነት የሚሾሙበትን አሠራርና የፍትሐዊነት ችግር በተመለከተ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ ተነሳ፡፡ ጥያቄው የተነሳው ሐሙስ ግንቦት 8 ቀን 2010 ዓ.ም. የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) የመሥሪያ ቤታቸውን የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ሲያቀርቡ ነው፡፡

ቻይና ለኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ዕቅዶች ድጋፌ ይቀጥላል አለች

የቻይና ሕዝባዊ ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ ሊቀመንበርና የኮንግረሱ አፈ ጉባዔ ሊ ዣንሹ፣ በኢትዮጵያና በቻይና መካከል ላለው ዲፕሎማሲዊ ግንኙነትና ለኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ የልማት ዕቅዶች ቻይና የምታደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቁ፡፡

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገንቢ ያልሆኑ አስተያየቶችን እየሰጡ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ወቀሱ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሽኩሪ ከስምምነት ውጭ የሆኑና ገንቢ ያልሆኑ አስተያየቶችን እየሰጡ ነው ሲሉ ወቀሱ፡፡ ቃል አቀባዩ ይኼንን ያሉት ዛሬ ግንቦት 2 ቀን 2010 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡

ካርቱም ሱዳን መጋቢት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. የተካሄደው ድርድር ውጤታማ ሳይሆን ከቀረ በኋላ፣ ሚኒስቴሩ ለሌላ ውይይት ካይሮ ላይ ሚያዝያ 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ሚኒስትሮቹ እንዲሰበሰቡ አሳስበው ነበር፡፡

‹‹አሜሪካ ለኢትዮጵያ ልዩ ትኩረት ትሰጣለች›› አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ

ሐሙስ ሚያዝያ 18 ቀን 2010 ዓ.ም. አዲስ አበባ የገቡት በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ጋር በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊና በአኅጉሪቱ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡ ያማሞቶ አገራቸው ለኢትዮጵያ ልዩ ትኩረት እንደምትሰጥ አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኤምባሲዎችን ካርታ ለማምከን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ተነጋገረ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለተለያዩ ግንባታዎች መሬት ከሊዝ ነፃ ወስደው ሳያለሙ ለዓመታት አጥረው ያስቀመጡ 18 ኤምባሲዎችና ዓለም አቀፍ ተቋማት ይዞታ ላይ በሚወሰደው ዕርምጃ ላይ፣ ባለፈው ሳምንት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ተነጋገረ፡፡

በህዳሴ ግድቡ ላይ የሚደረገው ውይይት በተያዘለት ቀነ ቀጠሮ ይካሄዳል

ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በህዳሴ ግድቡ ላይ የሚያደርጉት ውይይት በተያዘለት ቀነ ቀጠሮ እንደሚካሄድ ታወቀ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ሦስቱ አገሮች በህዳሴ ግድቡ ላይ በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ከመጋቢት 26 እስከ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ውይይት ለማድረግ ቀነ ቀጠሮ ይዘዋል፡፡ ሦስቱ አገሮች የሚያደርጉት ውይይትም በተያዘለት ቀን እንደሚካሄድ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አለው የተባለው ተከሳሽ የመከላከያ ምስክሮቹን አሰማ

ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ድርጅት ጋር ግንኙነት እንዳለውና ከድርጅቱ መሪ ብርሃኑ ነጋ (ዶ/ር) ጋር በመገናኘት የተሰጠውን ተልዕኮ ለመፈጸም ሲንቀሳቀስ ተደርሶበታል ተብሎ ክስ የተመሠረተበት ተጠርጣሪ፣ ሦስት የመከላከያ ምስክሮቹን አሰማ፡፡

ሦስቱ አገሮች ተቋርጦ በነበረው የህዳሴ ግድብ ላይ በካርቱም ሊወያዩ ነው

ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን ተቋርጦ በነበረው የህዳሴ ግድብ ላይ በካርቱም ውይይት ሊያደርጉ እንደሆነ ታወቀ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ሐሙስ መጋቢት 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ እንደተናገሩት፣ ሦስቱ አገሮች በህዳሴ ግድቡ ላይ የሚያደርጉት ውይይት ከመጋቢት 26 እስከ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. በካርቱም ይካሄዳል፡፡ 

‹‹ኢትዮጵያ ላጋጠማት ችግር መፍትሔው ለሕዝቡ ሰፋ ያለ ነፃነት መስጠት እንደሆነ ፅኑ እምነታችን ነው››

በአወዛጋቢ ንግግራቸው የሚታወቁትና ለአፍሪካ ግልጽ ፖሊሲ የላቸውም ተብለው የሚነገርላቸው ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ከተሾሙ በኋላ፣ ለመጀመርያ ጊዜ በከፍተኛ ኃላፊነት ደረጃ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን የካቲት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ኢትዮጵያ መጥተው ነበር፡፡ ሚኒስትሩ አዲስ አበባ የቆዩት ለ38 ሰዓታት ቢሆንም፣ በቆይታቸው ኢትዮጵያና አሜሪካ ስላላቸው የሁለትዮሽ ግንኙነት በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግሥት ኃላፊዎች ጋር ከመነጋገራቸውም በላይ፣ ኢትዮጵያ ስላለችበት ወቅታዊ ሁኔታ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ኢትዮጵያና ሩሲያ የኑክሌር ኢነርጂ ለመገንባት ተስማሙ

ኢትዮጵያና ሩሲያ የኑክሌር ኢነርጂ ለመገንባት ተስማሙ፡፡ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከሐሙስ የካቲት 29 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ቀናት ይፋ የሥራ ጉብኝት ወቅት እንደተናገሩት፣ ሁለቱ አገሮች በኑክሌር ኢነርጂ ተባብረው ለመሥራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ ሁለቱ አገሮች ከኑክሌር ኢነርጂ በተጨማሪ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ እንዲሁም በትምህርት ዘርፍ በትብብር ለመሥራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡