Skip to main content
x

ብስልና ጥሬው ተቀላቀሉ እኮ?

እነሆ መንገድ! ከቦሌ ጫፍ ወደ ካዛንቺስ ልንጓዝ ነው። ያ ትናንት የነጎድንበት መንገድ ዛሬም ይዞናል። በመዳህ ዘመናችን በመዳፋችን አፍሰን የቃምነው አፈር ዛሬ በዕውቀትና በዕድሜ እንደ ባዳ ፊቱን እያዞረብን፣ ያ ያመነው ጎዳና በሠፈር ቀዬያችን በቀና መንፈስ የተሯሯጥንበት መንገድ ዛሬ በአደባባይ እየጎረበጠን፣ እያናከሰን፣ እያስነከሰን፣ እያንከራተተን ከታክሲ ወርደን ታክሲ እንሳፈራለን።

የባከኑ ወርቃማ ዕድሎቻችን አያስቆጩም ወይ?

‹‹ይኼኛው ተራራ ያን እየጋረደው፣ የት ይታይ አካልህ ርቆ የሄደው?›› ትላለች ዘፋኟ ለዛ ባለው ድምጿ። ከሜክሲኮ ወደ ቄራ ለመሄድ እየተሳፈርን ነው። ትዝታ የታክሲዋን የውስጥ ድባብ ለስለስ አድርጎታል። የማለዳ ፀሐይ ሙቀት በመስኮቱ እየሰረገ የሚያገኘንን ብቻ ይዳስሳል።

ከከባድ ማርሽ ጋር ምን ያታግለናል?

እነሆ ነግቶ መንገድ ሊጀመር ነው። ከመገናኛ ወደ ስታዲዮም ልንጓዝ ነው። አያ ትርምስ የውጥንቅጥ አባት ጎዳናውን ዛሬም አልለቅ እንዳለ ነው። ያም ያስኬዳል። ይኼም ያስኬዳል። እግሩ የዛለው ሐሳቡ ተምታቶ መሀል መንገድ ላይ ቆሟል።

ወይ ነዶ?

እነሆ ጉዞ ከኮተቤ ወደ መገናኛ። ምን እንደገጠማቸው ያልታወቀ ሁለት ሴቶች ፊት ለፊት ተላተሙ። “አንችዬ! ምነው ዓይንሽ ቢያይ?” ብላ ግንባሯን እያሸች አንደኛዋ ቆመች። አንዱ ከአንዱ እያረፈደ ታክሲያችን ውስጥ የሚሞላው ተሳፋሪ ገሚሱ ሲስቅ ገሚሱ እንዳፈጠጠ ነው።

ከይቅርታ በላይ ምን ይምጣ?

እነሆ መንገድ! ከመገናኛ ወደ ሲኤምሲ ልናቀና ነው። የሰሞኑ ውርጅብኝ ያደረሰበትን ሰቆቃ በውስጡ ታቅፎ ነገውን በሥጋት የሚጠባበቅ ባተሌ ነዋሪ ወደ ቤቱ ሊገባ ይጣደፋል። ተማሪው፣ ሠራተኛው፣ ወዲያ ወዲህ የሚለው ሳይቀር መንገዱን ሞልቶታል። ለትራንስፖርት ጥበቃ ብዙኃኑ የሠልፍ አጥር ሠርተው ቆመዋል።

መንገድን ማሳጠር ወይስ ማስረዘም?

‹‹አንዳንድ ተሳፋሪዎች ‘ሙድ’ ይሰርቃሉ፡፡ ‘ሙድ’ ከሚሰረቅ ደግሞ ገንዘብ ቢዘረፍ ይሻላል፡፡ በእርግጥ ገንዘብ ቢዘረፍ ፖሊስ ዘንድ መክሰስ ይቻላል፡፡ ‘ሙዴን ሰረቀኝ’ ብሎ መክሰስ ገና አልተቻለም፡፡ ሙድ ይበልጣል ከፉድ. . . ›› እያለ ወያላው ወሬውን ያስነካዋል፡፡

እንሳቅ ወይስ እናልቅስ?

ጊዜው በፈጣን ለውጥ ታጅቦ እየከነፈ ነው፡፡ ትናንት ሰገነቱ ላይ የነበሩ ዛሬ የዳር ተመልካች ሆነዋል፣ ወይም በሕግ ሊዳኙ እጃችሁ ከምን እየተባሉ ይመስላል፡፡ የአገሬው ብሂልስ ‹‹በሰፈሩት ቁና መስፈር አይቀርም›› አይደል የሚለው? ሒደት ነውና ጉዞ ጀምረናል፡፡

ወንዝ መሀል ፈረስ አይቀየርም!

ከቦሌ ወደ ሃያ ሁለት ነው የምንጓዘው። ታክሲው ለመሙላት እየተቸገረ አይደለም። የሰው ብዛት ከሆነ በየቀኑ ለዓይናችን እስኪታክተን ድረስ እንዳየን ነው፡፡ ‹‹እንዴት ነው የሰው ልጅም እንደ ዶሮ በሙቀት ኃይል በአንድ ቀን መፈጠር ጀመረ?›› ብዬ ራሴን እጠይቃለሁ። ነገሩ ሳይገባኝ ቀርቶ አይደለም፡፡

ችግራችን መቶ መፍትሔያችን አሥር!

‹‹ይኼኛው ተራራ ያን እየጋረደው፣ የት ይታይ አካልህ ርቆ የሄደው?›› ትላለች ዘፋኟ ለዛ ባለው ድምጿ። ከሜክሲኮ ወደ ቄራ ልንጓዝ እየተሣፈርን ነው። ትዝታ የታክሲዋን የውስጥ ድባብ ለስለስ አድርጎታል።

ከሸረኛ ይሰውረን!

በሥራም ሆነ በትምህርት ምክንያት በቀን ቢያንስ አንድ ጊዜ ታክሲ ውስጥ ገባ ብሎ መውረድ አይቀርም፡፡ ይህ ዓረፍተ ነገር የሚመለከተው መኪና የሌላቸውን ብቻ ነው፡፡ ታዲያ በታክሲ ሲሄዱ አፌ ቁርጥ ይበልላችሁ የሚባሉ፣ ወይም ደግሞ አፋችሁ ይቆረጥ መባል የሚገባቸው ወያላና ሾፌር ሊያጋጥሙን ይችላሉ፡፡