Skip to main content
x

የአማራ ክልል የኦክስጅን ማምረቻና የማከፋፈያ ማዕከል ለመገንባት ወሰነ

የአማራ ክልላዊ መንግሥት የኦክስጅን ማምረቻና ማከፋፈያ ማዕከል ለማቋቋም መወሰኑ ተሰማ። የሚገነባው ማዕከል በዋናነት የሜዲካል ኦክስጅን ምርቶችንና ሌሎች ተዛማጅነት ያላቸው የሕክምና ግብዓቶችን የሚያመርት ሲሆን፣ ለሆስፒታሎች በተመጣጣኝ ዋጋ በሽያጭ በማቅረብ ከሚሰበስበው ገቢም ማዕከሉን ለማስፋፋት እንዲውል የክልሉ ካቢኔ ሰሞኑን መወሰኑን፣ የተገኘው የሰነድ መረጃ ያመለክታል።

ተፈናቃይ አርሶ አደሮች አክሲዮን ማኅበር መሠረቱ

ከአዲስ አበባ ከተማ በተለይም ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በልማት ምክንያት የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች አክሲዮን ማኅበር አቋቋሙ፡፡ ‹‹ፊንፊኔ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችና ዳያስፖራዎች ንግድ›› የሚል ስያሜ ያለው አክሲዮን ማኅበር የተቋቋመው በ180 ሚሊዮን ብር ካፒታል ሲሆን፣ በ40 ሔክታር መሬት ላይ በተለያዩ ዘመናዊ የግብርና ምርቶች ለመሰማራት እየተዘጋጀ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከዘጠኝ ወራት በኋላ የመሬት ሊዝ ጨረታ አወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየወሩ የመሬት ሊዝ ጨረታ እንደሚያወጣ ቢደነግግም፣ የበጀት ዓመቱ ሊጠናቀቅ አንድ ወር ያህል ሲቀረው በጉጉት ሲጠበቅ የቆየውን 29ኛውን የሊዝ ጨረታ አወጣ፡፡ 29ኛው የሊዝ ጨረታ ከዚህ ቀደም የተለመደው ልማዳዊ አሠራር እንደማይኖር፣ ይልቁንም አስተዳደሩ ባበለፀገው አዲስ ሶፍትዌር ጥቅም ላይ እንደሚውል ተገልጿል፡፡

የሃና ማርያም ተፈናቃዮች ከንቲባውን ማግኘት አልቻሉም

በሕገወጥ መንገድ መሬት ወረው መኖርያ ቤት ገንብተዋል በሚል ምክንያት ከሚኖሩበት ቀዬ በኃይል የተፈናቀሉ በሺዎች የሚቆጠሩ የሃና ማርያም ነዋሪዎች፣ ሰኞ ግንቦት 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ከንቲባ ድሪባ ኩማ እንደሚያናግሯቸው ተገልጾላቸው ማዘጋጃ ቤቱን ቢያጥለቀልቁም ከንቲባው ሳያነጋግሯቸው ቀሩ፡፡ ተፈናቃዮች  ላቀረቡት ተደጋጋሚ ቅሬታ ምላሽ ባለማግኘታቸው ባለፈው ረቡዕና ሐሙስ ከንቲባውን ለማግኘት ተሰብስበው ማዘጋጃ ቤት ደርሰው ነበር፡፡ ነገር ግን ከንቲባውን ማግኘት ባለመቻላቸው እንደተሰበሰቡ ወደ አሜሪካ ኤምባሲ ሄደው ነበር፡፡

በቦሌ ክፍለ ከተማ የሰሚት አካባቢ ነዋሪዎች ሕገወጦች መግቢያ መውጫ አሳጡን አሉ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ሰሚት ማዞሪያ ከተባበሩት ነዳጅ ማደያ ወደ ሰሚት ለስላሳ ማምረቻ ፋብሪካ መውረጃ መንገድ መጋጠሚያ ላይ ‹‹ተደራጅተናል›› የሚሉ ግለሰቦች አካባቢውን መኪና ማሳደሪያና መፀዳጃ ከማድረጋቸውም በተጨማሪ፣ መሸት ሲል ሰርቆ መደበቂያ በማድረጋቸው የአካባቢው ነዋሪዎች መውጫ መግቢያ ማጣታቸውን ገለጹ፡፡ የአካባቢው ወረዳ 8 ሥራ አስፈጻሚ ደግሞ ድርጊቱ ከአቅም በላይ በመሆኑ ለሚመለከተው አካል አሳውቀናል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች ለግንባታ ፈቃድ ባለሥልጣን ፈተና ሆነዋል

ከጥቂት ዓመት ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች እየተገነቡ ቢሆንም፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ለሕንፃዎቹ ራሱን ችሎ ፈቃድ የሚሰጥበትም ሆነ የሚቆጣጠርበት ደረጃ ላይ እንዳልደረሰ ተመለከተ፡፡ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ 26 ሺሕ ሕንፃዎች በግንባታ ላይ መሆናቸውን፣ በዚህ ዓመት በማዕከል ደረጃ ለ500 ፕሮጀክቶች የግንባታ ፈቃድ መሰጠቱ ታውቋል፡፡

በውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ችግር አዲስ አበባ ከባድ የውኃ እጥረት ያጋጥማታል ተባለ

በውጭ ምንዛሪ አቅርቦትና አመዳደብ ችግር ምክንያት አዲስ አበባ ከተማ ከአንድ ዓመት በኋላ ከበድ ያለ የንፁህ ውኃ አቅርቦት ችግር ሊገጥማት ይችላል ተባለ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 46 ሚሊዮን ዶላርና ስድስት ሚሊዮን ዩሮ ቅድሚያ ተሰጥቶት እንዲቀርብለት በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ምላሽ እንዳልተሰጠው አስታውቋል፡፡

ለገርቢ ግድብ ፕሮጀክት መሬት ማስረከብ ባለመቻሉ ከቻይና የተገኘ 146 ሚሊዮን ዶላር ጥቅም ላይ ሳይውል ቀረ

ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ንፁህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋል ተብሎ ለታሰበው የገርቢ ወንዝ ግድብ ፕሮጀክት፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስፈላጊውን መሬት በወቅቱ ባለማቅረቡ ከቻይና መንግሥት የተገኘው ብድር መጠቀሚያ ጊዜ አለፈበት፡፡ ይህ ገንዘብ ከአንድ ዓመት በፊት ሥራ ላይ መዋል የነበረበት ቢሆንም፣ መሬቱን ማግኘት ባለመቻሉ ተመላሽ ሆኗል ተብሏል፡፡

በኦሮሚያ አርሶ አደሮች ተቃውሞ ሥራ ያቆመውን የሰንዳፋ ቆሻሻ ማስወገጃ ሥራ ለማስጀመር ውይይት ሊካሄድ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኦሮሚያ አርሶ አደሮች ተቃውሞ ሥራ ያቆመውን የሰንዳፋ ቆሻሻ ማስወገጃ ሥራ ለማስጀመር፣ ከኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናትና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ያቋረጠውን ውይይት ሊጀምር መሆኑ ታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአንድ ቢሊዮን ብር ወጪ የከተማውን ደረቅ ቆሻሻ በዘመናዊ መንገድ ለማስወገድ የገነባው የሰንዳፋ ቆሻሻ ማስወገጃ፣ በአካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞ ምክንያት ሥራ በጀመረ በሰባት ወሩ ሐምሌ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. አገልግሎት መስጠት ማቆሙ ይታወሳል፡፡