Skip to main content
x

ዳግም የተከሰተው ኢቦላን ለመከላከል የተቋቋመው ግብረ ኃይል ሥራ ጀመረ

አደገኛ ከሚባሉ ወረርሽኞች ተርታ የሚሠለፈው ኢቦላ በተለያዩ ጊዜያት በአፍሪካ ተከስቶ በርካቶችን ለስቃይና እልቂት ዳርጓል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2014 በጊኒ፣ በሴራሊዮንና በላይቤሪያ ተቀስቅሶ በነበረው የኢቦላ ወረርሽኝ የ11 ሺሕ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል፡፡

መመርያ የሚጥሱ የግል ጤና ትምህርት ተቋማት ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የግል የጤና ትምህርት ተቋማት ከ2005 ዓ.ም. ጀምሮ በመደበኛው የቀን ፕሮግራም ብቻ እንዲሰጡ መመርያ ቢያስተላለፍም፣ በርካታ የግል የጤና ትምህርት ተቋማት መመርያውን እየጣሱ እንደሆነ ተገለጸ፡፡ በዚህም ምክንያት ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምራት ሞታ ሰኞ ግንቦት 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ተፈርሞ የወጣ ደብዳቤ እንደሚያመለክተው፣ መመርያውን የጣሱ በርካታ የግል የጤና ትምህርት ተቋማት በማታ ክፍለ ጊዜ ተማሪዎችን መዝግበው አሁንም እያስተማሩ ናቸው፡፡

በሥርዓተ ምግብ ላይ አትኩሮ የሚሠራ ኃይለማርያም ሮማን ፋውንዴሽን ሊቋቋም ነው

ኅብረተሰቡ በሥርዓተ ምግብ ዙሪያ አመጣጥኖ የመመገብ ልምዱ እንዲዳብር የሚደረገውን ጥረት አጠናክሮ ለመቀጠል ‹‹ኃይለማርያም ሮማን›› ተብሎ በሚቋቋመው ፋውንዴሽን ትኩረት ሰጥተው እንደሚሠሩ የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ሮማን ተስፋዬ አስታወቁ፡፡ የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ሮማን ይህን የተናገሩት የዓለም አቀፍ ሥርዓተ ምግብ መሻሻልን በሚያሰፋው የብሔራዊ ሥርዓተ ምግብ ፕሮግራም ላበረከቱት አስተዋጽዖ ከወራት በፊት በአይቮሪኮስት አቢጃን በይፋ የተገለጸውን ሽልማታቸውን ሐሙስ ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ.ም. በተረከቡበት አጋጣሚ ነው፡፡

በወሊድ የሚሞቱ እናቶችን ለመታደግ

እናታቸው ነርስ የመሆን ፍላጎት የነበራቸው ቢሆንም አልተሳካላቸውም፡፡ በትዳር ዘመናቸውም አራት ሴት ልጆችን አፍርተዋል፡፡ የሕክምና ባለሙያ የመሆን ህልማቸውንም በልጆቻቸው ለማሳካት ያልሙ ነበር፡፡ ስለ ሕክምና ሙያ ጥሩነት ለልጆቻቸው በየአጋጣሚው ሁሉ ከመናገር የቦዘኑበት ጊዜም አልነበረም፡፡ በስተመጨረሻም ህልማቸው ዕውን ሆኖ ሦስቱ ልጆቻቸው ሐኪሞች ሆኑ፡፡

ሱስ ያደበዘዛቸው የሕይወት መስመሮች

በአፍሪካ ትልቁ ገበያ እንደሆነ በሚነገርለት በመርካቶ እንኳንስ ነጋዴው ተላልኮ የሚኖረው ምስኪን እንኳ ገንዘብ አይቸግረውም፡፡ ሌላው ቢቀር የዕለት ጉርስ ጉዳይ አያሳስበውም፡፡ የወላጆቹን የንግድ ሥራ ድርጅት ገና በልጅነቱ ለተቀላቀለው ለካሳሁን ኪሮስ ዓይነቱ ደግሞ ገንዘብ ቁም ነገሩ አይሆንም፡፡

በሰባት የዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች የካንሰር ማዕከላት ግንባታ እየተካሄደ ነው

ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ያደጉ አገሮች በሽታዎች ናቸው ተብለው ሲወሰዱ የቆዩ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት እነዚህ በሽታዎች በከፍተኛ ደረጃ ኅብረተሰቡን እያጠቁ ነው፡፡ የሥርጭት መጠናቸውም በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል፡፡ ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች ዋና ዋናዎቹ መካከል አንዱ ካንሰር ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ከፍተኛውን ቁጥር የያዘው የጡት ካንሰር ነው፡፡ ይህም ሴቶችን በከፍተኛ ደረጃ እያጠቃ ያለ በሽታ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የደረሱለት ታዳጊ

ከደቂቃዎች በፊት ሲቦርቅ ሲጫወት የነበረ ሕፃን ከአፍታ በኋላ እንደዋዛ መናገርም ሆነ መንቀሳቀስ የማይችልበት ከእርሶ የራቀ የዝምታ ዓለም ውስጥ ሆኖ ቢያገኙት ምናልባት ቅዠት ይሆን ብለው ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ እውነታውን አምኖ መቀበል እንኳንስ ለወላጅ ለሌላም ከባድ ይሆናል፡፡ ችግሩ የተፈጠረው ደግሞ ብዙም አስጊ ያልነበረን ነገር ግን ምቾት የነሳውን የጤና እክል አክመው ያድኑታል ብለው ባመኑባቸው ሐኪሞች ሲሆን፣ ሐዘኑም ቁጭቱም ድርብ ይሆናል፡፡

ከመስማት እክል የመታደግ ጅማሮ

አፎሚያ ዳንኤል የ12 ዓመት ታዳጊ ነች፡፡ የመስማት ችግር ያጋጠማት በአንድ ዓመት ከሁለት ወር ዕድሜዋ ቤት ውስጥ ድክ ድክ ስትል በወደቀችበት አጋጣሚ ነበር፡፡ መውደቋን ተከትሎ ቀስ በቀስ የቅርብ እንጂ የርቀት ድምፅ መስማት ተሳናት፡፡ አንደበቷም ይይዛት፣ ትኮላተፍ ጀመረ፡፡

የተቀናጀ ደጂታል የሕክምና አገልግሎት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተጀመረ

የታካሚዎችን ሙሉ መረጃ አያያዝና መስተንግዶ ወደ ማዕከላዊ የመረጃ ቋት ሥርዓት የሚያስገባ የተቀናጀ ዲጂታል የሕክምና አገልግሎት ሥርዓት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በትግበራ ላይ ዋለ፡፡ ቴክኖሎጂው በካርድ ላይ የተመሠረተ የሕክምና አሠራርን የሚያስቀር፣ ሐኪሞች አጠቃላይ የሕክምና ሒደትና የታካሚዎችን ሙሉ መረጃ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የሚያስገቡበት፣ የሚቀባበሉበት እንደሚሆን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር፣ ኢንጂነር) ገልፀዋል፡፡

የመድኃኒት አቅርቦትን የሚያሳልጠው ስምምነት

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ልዩ ልዩ መድኃኒቶችን ከመድኃኒት ፈንድ አቅርቦት ኤጀንሲ በቋሚነት ማግኘት የሚያስችለውን ውል ተፈራርሟል፡፡ ማኅበሩ ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች የሚያገለግሉ የስኳር፣ የካንሰር፣ የደም ብዛትና የመሳሰሉትን መድኃኒቶች እንዲሁም በኤጀንሲው መጋዘኖች በብዛት ተከማችተው የሚገኙ መድኃኒቶችን ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡