Skip to main content
x

በውጭ ምንዛሪ አጠቃቀም ችግር ከገበያ እየወጡ ያሉ የንግድ ሰዎች የብሔራዊ ባንክ ገዥ ይድረሱልን አሉ

በውጭ ምንዛሪ እጥረትና አጠቃቀም ችግር ምክንያት ጥሬ ዕቃ ማግኘት ባለመቻላቸው ከምርት እየወጡ መሆናቸውን የሚናገሩ የፋብሪካ ባለቤቶችና መድኃኒትን የመሳሰሉ አስፈላጊ ዕቃዎች የሚያስመጡ ነጋዴዎች፣ ከገበያ እየወጡ መሆኑን በመጥቀስ አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) እንዲደርሱላቸው ጠየቁ፡፡

የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ የማምጣት ፈተናና የተደቀነው ማኅበራዊ ቀውስ ሥጋት

የ2011 ዓ.ም. የፌዴራል መንግሥት ረቂቅ በጀት ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ይዘው የቀረቡት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) ያደረጉት የበጀት መግለጫ ንግግርን የአገሪቱን ኢኮኖሚ ጠፍረው ያሰሩ ችግሮችንና ለችግሮቹ ፈጣን መፍትሔ ካልተገኘ ሊፈጠር የሚችለውን ማኅበራዊ ቀውስ ያመላከተ ነበር፡፡

የዘጠኝ ወራት የወጪ ንግድ ገቢ 2.1 ቢሊዮን ዶላር ሆነ

ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከወጪ ንግድ 2.1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ፡፡ ይህ ገቢ በዕቅድ ተይዞ ከነበረው 3.6 ቢሊዮን ዶላር ጋር ሲነፃፀር 57 በመቶው ብቻ እንደተሳካ ታውቋል፡፡ በተጨማሪም ካለፈው ዓመት የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ጋር ሲነፃፀር የ4.3 በመቶ (100 ሚሊዮን ዶላር) ብቻ ጭማሪ ተመዝግቧል፡፡ አብዛኛው ገቢ ከዚህ ቀደም እንደተለመደው ከግብርናው ዘርፍ የተገኘ ሲሆን፣ ቀሪው ከማኑፋክቸሪንግና ከማዕድን ዘርፍ ነው፡፡

በፀጥታ መደፍረስ የተጎዳውን የንግድ እንቅስቃሴ የሚገመግም ጉባዔ ተጠራ

በአገሪቱ አጋጥሞ የነበረው የፀጥታ መደፍረስ በንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ ያሳደረውን ተፅዕኖ በመገምገም፣ መፍትሔ የሚያመላክት ጉባዔ በአማራ ክልል ርዕሰ ከተማ በባህር ዳር ከተማ ሊካሄድ ነው፡፡ የንግድ ሚኒስቴር ከግንቦት 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ቀናት በጠራው ‹‹የክልሎች መድረክ›› ጉባዔ ላይ፣ ዘጠኙ ክልሎችና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል፡፡

በውጭ ምንዛሪ የሚታዩ ብልሹ አሠራሮች ይወገዱ!

የአገሪቱ ኢኮኖሚ ከመቼውም ጊዜ በላይ ፈተናዎች ተጋርጠውበታል፡፡ ለዓመታት ነዳጅ ከሌላቸው አገሮች በላቀ ሁኔታ ዕድገት እያስመዘገበ የመጣው ኢኮኖሚ፣ በተለይ ባለፉት ሦስት ዓመታት ከባድ ችግር ገጥሞታል፡፡ ለኢኮኖሚው መቀዛቀዝና መዳከም በዋነኛነት ከሚነሱ ችግሮች መካከል አንዱ ሥር የሰደደ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ነው፡፡ የአገሪቱ ዋነኛ የውጭ ምንዛሪ ምንጮች ኤክስፖርት፣ ሐዋላ፣ ብድርና ዕርዳታ፣ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትና ከፕራይቬታይዜሽን የሚገኙ ገቢዎች እንደሆኑ ይታወቃል፡፡

በቆሎ ወደ ውጭ ኤክስፖርት እንዲደረግ የመንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ ነው

በተያዘው የ2009/2010 ምርት ዘመን ትርፍ በቆሎ በመመረቱ፣ ወደ ውጭ ኤክስፖርት ለማድረግ የመንግሥት ፈቃድ እየተጠበቀ መሆኑን መረጃዎች አመለከቱ፡፡በ2008/2009 ዓ.ም. በተወሰነ ደረጃ ትርፍ በቆሎ ተገኝቶ ስለነበር 620 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ወደ ጎረቤት ኬንያ መላኩ ይታወቃል፡፡ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትሩ ኢያሱ አብርሃ (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በተያዘው ምርት ዘመን በርካታ በቆሎ በመመረቱ ለመንግሥት ውሳኔ አቅርበዋል፡፡

የኢኮኖሚ ዕድገቱን ለማስቀጠል ከ700 ቢሊዮን ብር በላይ ኢንቨስትመንቶች እንደሚያስፈልጉ የብሔራዊ ባንክ ገዥ አስታወቁ

የአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት እንዳይገታ ከ700 ቢሊዮን ብር በላይ ኢንቨስትመንቶች በኤክስፖርት ተኮር ዘርፎች እንደሚያስፈልጉ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ገለጹ፡፡ የባንኩ ገዥ አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰኞ ጥቅምት 27 ቀን 2010 ዓ.ም. እንዳስታወቁት፣ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን ያህል አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን በተለይ ኤክስፖርት ተኮር በሆኑ ዘርፎች ማከናወን ስላልተቻለ የኢኮኖሚው ዕድገት ሊገታ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

የሞያሌ ድንበርን ማለፍ ያልቻለው የኤክስፖርት ስኳር ውዝግብ አስነሳ

የኬንያ መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ ተጠይቋል መፍትሔ ካልተገኘ ስኳሩ ወደ ወንጂ ሊመለስ ይችላል ከአንድ ወር በፊት ወደ ኬንያ ኤክስፖርት ተደረገ የተባለው ስኳር የኢትዮጵያ ሞያሌ ድንበርን አለማለፉን፣ የስኳር ምርቱን የገዛው መቀመጫውን በዱባይ ያደረገው ኩባንያ ችግሩን መፍታት አለመቻሉን ሪፖርተር ያገኛቸው መረጃዎች አመለከቱ፡፡