Skip to main content
x

የሳምንቱ ገጠመኝ

ከዓመታት በፊት በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ለረዥም ጊዜ የታየ ድንቅ ቴአትር ነበር፡፡ በሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድኅን ተተርጉሞ የተዘጋጀው ‹‹ኦቴሎ›› ቴአትር በተዋንያኑ ድንቅ ብቃት በወረፋ ነበር የሚታየው፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

በቀደም ዕለት እንዲህ ሆነላችሁ፡፡ በከተማችን ከሚገኙ ሲኒማ ቤቶች ወደ አንዱ አዲስ የወጣ ፊልም ለማየት እሄዳለሁ፡፡ የዚህን ፊልም ‹‹እንከን የለሽነት›› በተለያዩ ማስታወቂያዎች ስለሰማሁ እስኪ ልየው ደግሞ በማለት ነው እዚህ ሲኒማ ቤት የተገኘሁት፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ወደ ስታዲዮም ስጓዝ ታክሲ ውስጥ የሰማሁት ወግ ነው መነሻዬ፡፡ ወያላና ሾፌር የታክሲው መጨረሻ ስታዲዮም መሆኑን ወስነው ተሳፋሪን የሚጭኑት ስታዲዮም ብቻ እንደሆነ ቀጭን ትዕዛዝ ሰጡን፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

በቀደም ዕለት ከወዳጆቼ ጋር የምሣ ግብዣ ነበረን፡፡ የምሣ ላይ ጨዋታ ከሚያስደስቱኝ ነገሮች መካከል በዋነኝነት ይመደባል፡፡ አጠር ባለ ሰዓት ውስጥ ወዝ ያለው ጨዋታ እየተጨዋወቱ ምሣን ማጣጣም ደስ ይላል፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

የሰሞኑ ገጠመኛችን እኔን ወደኋላ ሃያ ዓመታት መልሶኛል፡፡ ከዚያ ትውስታ ተነስቼ ወደ ሰሞኑ ጉዳይ እመለሳለሁ፡፡ ፈረንጆቹ ‹‹ማርጀትህን የምታውቀው በተስፋ መኖር ትተህ በትዝታ መኖር ስትጀምር ነው፤›› የሚሉት ብሂል ለጊዜው ባይመለከተኝም፣ አንዳንድ ትዝታዎች ግን የግድ መነሳት አለባቸው እላለሁ፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

በዚህ የ‹‹ኮሜዲ›› ዘመን ብዙ ሰዎች ቀልደኛ የሆኑ ይመስላሉ፡፡ ለዛሬው ገጠመኜ መነሻ የሆኑኝን አንዳንድ ትውስታዎችን አቅርቤ ወደ ጉዳዬ አመራለሁ፡፡ ዘመኑ የቀልድ አይደል? አንድ ጊዜ ጫማዬን የሚያሳምርልኝ ታዳጊ ከሊስትሮ ሳጥኑ አጠገብ ሁለት ደብተሮች አስቀምጧል፡፡ የልጁ ብልህነት አስደስቶኝ፣ ‹‹ጎበዝ ልጅ በርታ፡፡ ማታ ማታ ትማራለህ እንዴ?›› ስለው በመገረም እያየኝ፣ ‹‹ኧረ እኔ አልማርም፤›› አለኝ፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

ግርምና ድንቅ የሚያደርግ አጋጣሚዬን ወገኖቼ ብትሰሙት ብዬ ነው ይኼንን የጻፍኩላችሁ፡፡ እኔና ሌሎች ዘጠኝ የሥራ ባልደረቦቼ በተለያዩ የምህንድስና መስኮች ለረዥም ዓመታት ከመሥራታችንም በተጨማሪ ሁላችንም የማስተርስ ዲግሪ አለን፡፡ በአንድ ትልቅ መሥሪያ ቤት ውስጥ በሚካሄድ ፕሮጀክት በአማካሪነትና በአስፈጻሚነት ሙያዊ አገልግሎታችንን እያበረከትን፣ ጥሩ ደመወዝና ጥቅማ ጥቅሞችንም እናገኛለን፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

ሁሌም ጥሎብኝ የሴቶችን መማር፣ ማደግና ስኬት በእጅጉ እከታተላለሁ፡፡ በዚህ ዘመን ዓለም አቀፍ ተቀባይነት እያገኘ የመጣ አባባልም እየተፈጠረ ነው፡፡ ‹‹ሴትን ልጅ በማስተማር ታላቅ የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገብ ይቻላል፤›› ነው የሚባለው፡፡ በእርግጥም እኔም ይኼንን ውብ አባባል እጋራዋለሁ፡፡ በተለይ ድህነት የሰፈነባት አገር ውስጥ ሴት ልጅ ለውጤት የሚያበቃት ድጋፍ ሊደረግላት ይገባል፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

‹‹ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም›› የሚለው የቆየ ምሳሌ ትዝ ያለኝ በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ ነው፡፡ አንዳንድ አግራሞት የሚያጭሩብን ጉዳዮች ከመብዛታቸው የተነሳ ስንት ቁምነገር የሚሠራበት ጊዜ በዋዛ ፈዛዛ ማለፉ ያንገበግበኛል፡፡ እዚህ አገራችን ውስጥ ጊዜ ተፈብርኮ ለዓለም እየተቆነጠረ የሚታደል ይመስል፣ ለታላላቅ ተግባሮች የምናውላቸው እጅግ በጣም ውድ የሆኑ ጊዜዎቻችን የሌሎችን እንቶ ፈንቶ ስንሰማባቸው ይባክናሉ፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ እየተጓዝኩ ነበርኩ፡፡ ድሬዳዋ የሄድኩበትን ጉዳይ ቶሎ አከናውኜ ወደ አዲስ አበባ የማደርገው ጉዞ የፈጠነው፣ በነጋታው ለሌላ አስቸኳይ ጉዳይ ወደ ጎንደር ስለምሄድ ነበር፡፡ ከድሬዳዋ የጀመርነውን ጉዞ እያገባደድን አዋሽ አካባቢ ስንደርስ የተሳፈርንበት አውቶቡስ ጎማ ፈንድቶ ቆምን፡፡