Skip to main content
x

መካሪ አያሳጣን!

ሰላም! ሰላም! እንደምን ሰነበታችሁ የተወደዳችሁ ኢትዮጵያዊያን! እኔ ደላላው አንበርብር ምንተስኖት እናቷ ማንጠግቦሽ ብለው ከሰየሟት እኔም ዘወትር ከማልጠግባት ውዷ ባለቤቴ ጋር 100 ቁጥር ያለበት ሻማ ለኩሰን በማብራት፣ ቡናችንን ፉት እያልን እያከበርን ነው፡፡

እንመራረቅ እንጂ!

ሰላም! ሰላም! እንደምን ከርማችኋል የተወደዳችሁ የዚህ ዘመን ዕንቁዎች! ቤት ሠፈር ቀዬው ሰላም እንደሆነ ሳላበስራችሁ አላልፍም፡፡ ሰሞኑን ባሻዬ፣ ‹‹እንግዲህ ለአገር የሚበጅ፣ ለትውልድ የሚጠቅም ሲከናወን እኛም ዕገዛ ማድረግ አለብን፤›› ያሉትን አድንቄያለሁ፡፡

ዓረሙ ይነቀል!

ሰላም! ሰላም! የተወደዳችሁ ወገኖች! በያላችሁበት አንዳንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ይድረስልኝ፡፡ ባሻዬ ልጃቸውን፣ ‹‹አሁንስ ህልም እያየሁ እየመሰለኝ ነው፡፡ ህልምም ከሆነ እባክህ እንዳትቀሰቅሰኝ፤›› በማለት ደስታቸውን ሲገልጹ ነበር፡፡

የቁልፉን ነገር አደራ!

ሰላም! ሰላም! የተወደዳችሁና የተመረጣችሁ ወዳጆቼ እንደምን ከርማችኋል? እኔ ደህናም ነኝ! ደህናም አይደለሁም፡፡ ደህናውን በመናገር ጀምር ካላችሁኝ መቼም የደስታዬ ምንጭ ይጠፋችኋል ብዬ አልጠረጥርም፡፡

ለሁሉም ጊዜ አለው!

ሰላም! ሰላም! እንደምን ቆያችሁልኝ የተወደዳችሁ? እኔማ ናፍቆት እያብሰከሰከኝ ከረምኩ፡፡ መቼም ደላላ ፍቅር አያውቅም የሚል ስንት አለ መሰላችሁ? ፍቅር ለመስጠት ምን ያንሰንና ነው? ወዳጆቼ ዘመን ተቀይሯል፡፡ ፍቅራችንንም ለመግለጽ መሬትና መኪና ካጋዛችኋቸው ሰዎች ጋር ‘ሰልፊ’ ተነስቶ መልቀቅ የተለመደ ነገር ሆኗል፡፡

‹ያዋከቡት ነገር ምዕራፍ አያገኝም . . . !›

ሰላም! ሰላም! እንዴት ከርማችኋል? ባሻዬ በጠዋት ከዚህ ዓለም የተለዩዋቸውን ጓደኞቻቸውን አስታውሰው፣ ‹‹ያላደለው በአየር ሳይበር በመኪና ብቻ ተጓጉዞ ያልፋል፤›› ብለው ተመስጦ ውስጥ ሲገቡ፣ ልጃቸው፣ ‹‹ያደለውንስ ምን ልትል ነው?›› ቢላቸው፣ አቅርቅረው ትንሽ አሰብ አደረጉና፣ ‹‹ያደለውማ የታላቁ አየር መንገድ ባለቤት ይሆናል፤›› ብለው ወደ ተመስጧቸው ተመልሰው ገቡ፡፡

መገኘትስ ቀድሞ ነው!

ሰላም! ሰላም! በምርጡ ዘመን ላይ ለተፈጠራችሁ ሁሉ፡፡ ጮማ ዘመን ይሏል ይኼ ነው፡፡ አሸዋ ዘርተው ወርቅ የሚበቅልበት፣ ትንሽ ሠርተው ብዙ የሚያጭዱበት ምርጥ ዘመን፡፡ የባሻዬ ልጅ፣ ‹‹ቅዠት ነው ወይስ ሕልም ነው? እንደ እውነቱ ተምታትቶብኛል፡፡ ያየሁትን ፎቶ ማመን አልቻልኩም ነበር . . . ›› በማለት ሲደመም ነበር፡፡

‹እንጫወት እንጂ ገሩን ገራገሩን . . .!›

ሰላም!  ሰላም! የተወደዳችሁ ወዳጆቼ እንደምን ከርማችኋል? እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ እኔ እንዳማረብኝ፣ ጠላቴም እንደቀናብኝ አለሁ፡፡ ባሻዬ ‹ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም› ብሎ ሰለሞን ጠቢቡ ቀድሞ ተናግሮታል ያሉትን ነገር መጠራጠር ጀምሬያለሁ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የማየውና የምሰማው ሁሉ አዲስ እየሆነብኝ ነው፡፡

‹ማን ነህ ባለ ተራ?›

ሰላም! ሰላም! እንደምን ከረማችሁ የተወደዳችሁ ወዳጆቼ? ‹‹እየታገልን አለን፡፡ እየተሯሯጥን አለን፡፡ እያሸነፍን አለን፡፡ ከማሸነፍ ውጪ ምንም አማራጭ የለንም ብለን አምነን፡፡ ከመቅደም ውጪ መቀደም ፍፁም አማራጭ ሊሆነን አይችልም ብለን፡፡ ከመግዛት ውጪ መገዛት ለእኛ አልተሰጠንም፡፡

‹ማን ነህ ባለ ተራ?›

ሰላም! ሰላም! እንደምን ከረማችሁ የተወደዳችሁ ወዳጆቼ? ‹‹እየታገልን አለን፡፡ እየተሯሯጥን አለን፡፡ እያሸነፍን አለን፡፡ ከማሸነፍ ውጪ ምንም አማራጭ የለንም ብለን አምነን፡፡ ከመቅደም ውጪ መቀደም ፍፁም አማራጭ ሊሆነን አይችልም ብለን፡፡ ከመግዛት ውጪ መገዛት ለእኛ አልተሰጠንም፡፡